03/09/2026
በሕዝብ ተሳትፎ የተገነባው የጊምቢቹ ዲጂታል ቤተ-መጽሐፍት ተመረቀ።
ዲጂታል ቤተ-መጽሐፍቱ ከጊምቢቹ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተወሰደ 900 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን፤ ግንባታው ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት አራት ዓመታት ከሕዝብ በተሰበሰበ ሀብት ሲከናወን መቆየቱ ተገልጿል።
ከተማዋ ለተለያዩ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ማዕከል በመሆኗም ቤተ-መጽሐፍቱ በርካታ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ እንደሆነ ታምኖበታል።
በምረቃ መርሃ-ግብሩ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የመንግሥት ዋና ተጠሪ ድላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር)፣
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ፣ ምክትል ርዕሰ-መስተዳደርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
https://www.facebook.com/hadiyyooma