Ambassador media

Ambassador media ኢትዮጵያ ለዘእላለም ትኑር እውነት ያሸንፍል

ብልግናን መገለጫችን ባናደርግስ?"ቤቲዬ የወሰንሽውን ውሳኔ እቃወማለሁ" እያሉ የሚያለቅሱ አባት ቪድዮ እዚህ መንደር ሲዘዋወር ቪድዮው ላይ ባለው ቲክቶክ አካውንታቸው ፈልጌ አገኘኋቸው። እሳቸው...
30/12/2023

ብልግናን መገለጫችን ባናደርግስ?

"ቤቲዬ የወሰንሽውን ውሳኔ እቃወማለሁ" እያሉ የሚያለቅሱ አባት ቪድዮ እዚህ መንደር ሲዘዋወር ቪድዮው ላይ ባለው ቲክቶክ አካውንታቸው ፈልጌ አገኘኋቸው። እሳቸው duet ያደረጉበትን ቤተልሄም ግርማ የምትባል እህት ቪድዮም ገብቼ አየሁት ። ልጅቷ ከዚህ በፊት በቲክቶክ ላይቭ እየገባች ለተለያዩ ታማሚ ወገኖች ገቢ ማሰባሰብ ስትሰራ የቆየች እህት ነች። እሷ ባሰባሰበችው ብር ብዙዎች ታክመው ድነዋል መድሀኒያለም ይስጣት። መጨረሻ ላይ በለቀቀችው ቪድዮ ግን እያለቀሰች በግልፅ ምክንያቱን መናገር ባትፈልግም "ከዚህ በኋላ በቲክቶክ የማደርገው እንቅስቃሴ በቃኝ" ብላለች። ስሜታዊ ያረጋትና ሞራሏን የነካው የመንደሩ ሰዎች ስድብና ጋጠወጥነት ይመስለኛል። ስርአተ ማህበራችን መልካሞችን የሚሰብር ባለጌን የሚያገን እየሆነ መጥቷል።

እኝህ አባት ቀድሞ በሷ እርዳታ ቤተሰባቸውን ያተረፉ ናቸው አለያም ደግሞ በመልካም ተግባሯ የሚደሰቱ ናቸው። አሁን በሞራሏ መሰበር አዝነው "እባክሽ መልካም ተግባርሽን አታቁሚ" እያሉ አለቀሱ። ጥቂት ማጣራትም የማያረጉ የዚህ መንደር ባለጌዎች ደግሞ የሳቸውን ቪድዮ ብቻ አምጥተው በመለጠፍ "ቤቲ የምትባል ሴት አፍቅሮ ሲያለቅስ" በማለት መዘባበቻ አድርገዋቸዋል። በተለይም ያሣፈረኝ ይኼን ቪድዮ ከለጠፉት ውስጥ ብዙዎቹ ሴቶች መሆናቸው ነው።

እኝህ አባት የቴክኖሎጂውን አደገኛ መልክ አልተረዱት ይሆናል በቀናነት ስሜታቸውን ገለፁ። እንዲ መዘባበቻ ስታደርጓቸው ግን ቤተሰብ ፣ ስብእና ና ልጆች እንዳላቸው ራሱ ማስተዋል አቅቷችኋል።

በአባታችሁ ላይ እንዲህ ቢደረግ እንዲህ የመሣቅ ሞራል አላችሁ ይሆን ?

Tesfa.G.neda

የደስታ ምንጭ ከወዴት ነው?     ደስታ በዲግሪያችንችን ምክንያት በምናገኘው ስራ፣ ባፈራነው ሀብት ወይም በተሾምነው የስልጣን እርከን፣ አሊያም በፈጠርናቸው ግንኙነቶች ውስጥ አለመኖሩን  እና...
28/12/2023

የደስታ ምንጭ ከወዴት ነው?

ደስታ በዲግሪያችንችን ምክንያት በምናገኘው ስራ፣ ባፈራነው ሀብት ወይም በተሾምነው የስልጣን እርከን፣ አሊያም በፈጠርናቸው ግንኙነቶች ውስጥ አለመኖሩን እናውቅ ይሆን?

ታዲያ .......እውነተኛወ፣ ሰለሙ የሰፈነ፣ የኑሮ ወጀብ የማይናወጠው፣ እንደሰማይ የጠራ፣ እንደፀሀይ የፈካ እና የደመቀው ደስታ ምንጩ ከወዴት ነው?

ደስታ ምንጊዜም ቢሆን በተስፋ፣ ልባችን በማዳመጥ እና መሄድ እና መድረስ በምንፈልግበት ስኬት ውስጥ ነው ያለው!

ደስታ ለራሳችን ደግ በመሆን ፣ በመፈቀር ሳይሆን በማፍቀር፣ በህይወት እና የኑሮን ፈይዳ ውስጥ መክሊትን በማግኘት፣ በመታቀፍ ሳይሆን በማቀፍ፣ በመቀበል ሳይሆን በመስጠት ውስጥ ነው የሚፀናው።

ደስታ ምንጊዜም ቢሆን ከራሳችን ጋር እንዴት መኖርን እንዳለብን በመማር ውስጥ እንጂ በጭራሽ በሌሎች ሰዎች እጅ ውስጥ አይደለም።

ደስታ ከውስጣችን የሚመነጭ የስበት ሀይል እንጂ ከሌሎች የምንቀበለው ምፅዋት አይደለም!

የደስታ ምንጭ ሌሎች ሳይሆኑ እኛ እና እኛ ብቻ ነን!

🙏 የደስታ ሰንበት ይሁንልን!

!
- ሣሙኤል ተክለየሱስ
(የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)
=====================
©️Sammy 𝐊. Tekle™

በድብቅ የተቀረፀ በአዲስ አበባ የአህያ ስጋ ነጋዴ እርስ ሲያከናውም ተያዘ " ሰው ከበላ  ፣እንኳን አይደለም የአህያ ስጋ  የጂብ ስጋ እንሸጣለን ። ሼር በማድረግ እናስቁም
03/12/2023

በድብቅ የተቀረፀ
በአዲስ አበባ የአህያ ስጋ ነጋዴ እርስ ሲያከናውም ተያዘ " ሰው ከበላ ፣እንኳን አይደለም የአህያ ስጋ የጂብ ስጋ እንሸጣለን ። ሼር በማድረግ እናስቁም

It is difficult to predict the best job in 2023 as it depends on various factors such as technological advancements, economic conditions, and market t...

የሊያ እና የሲሚ ምርጥ የሰርግ ቪዲዮ
02/12/2023

የሊያ እና የሲሚ ምርጥ የሰርግ ቪዲዮ

1. Create a Wedding Party: - Bride and Groom - Maid/Matron of Honor - Best Man - Bridesmaids - Groomsmen - Flower Girl(s) - Ring Bearer(s) 2. Select a...

 ከተንደላቀቀ ህይወት ወደ ጫማ መጥረግ! ያልተጠበቀ የህይወት ጉዞ እና ፅናት!
20/11/2023


ከተንደላቀቀ ህይወት ወደ ጫማ መጥረግ!
ያልተጠበቀ የህይወት ጉዞ እና ፅናት!

Ethiopian film refers to the film industry and productions originating from Ethiopia. The Ethiopian film industry has a long and rich history, with it...

07/09/2023

አሳዛኝ ዜና !
ከሁለት ሳምንታት ፍለጋ በኋላ ፖሊስ የዮሐንስ ኪዳኔን አስክሬን በሳንፍራንሲስኮ የባህር ወሽመጥ ውሀ ላይ ተንሳፎ ማግኘቱን አስታውቋል😭😭😭😭
*******************************************************
ማክሰኞ ነሐሴ 29/2023 ቀን ከሳን ፍራንሲስኮ የባህር ወሽመጥ ላይ በውሃ ውስጥ ምላሽ የማይሰጥ ሰው መታየቱን ጥቆማ ለመርማሪዎች ከደረሳቸው በኋላ አስክሬኑን ከውሀ ውስጥ ያወጡት ሲሆን የአስከሬን ምርመራው ውጤት አስከሬኑ የዮሐንስ ኪዳኔ መሆኑን አረጋግጧል።

የሞቱን መንስኤ ራስን ማጥፋት መሆኑን የማሪን ካውንቲ የሸሪፍ ጽህፈት ቤት ዛሬ ያስታወቀ ሲሆን የ22 አመቱ ወጣት የከባድ ጉልበት ጉዳት እና ውሀ ውስጥ መስጠም ለህይወቱ ማለፍ አስተዋፅኦ አድርጓል።

ዮሐንስ በቅርቡ ከኮርኔል ዩኒቨርስቲ ተመርቆ በታዋቂው ኔትፍሌክስ የሶፍትዌር ኢንጂነርነት ተቀጥሮ ለመስራት ከመጥፋቱ ሁለት ሳምንት በፊት ከኒውዮርክ መሄዱ ይታወቃል። ስልኮቹ እና የኪስ ቦርሳው ጎልደን ጌት ድልድይ አካባቢ ከጠፋ በኋላ ተገኝተው የነበረ ሲሆን ለመጨረሻ ግዜ የታየው ከሁለት ሳምንታት በፊት በኡበር ታክሲ ሲሳፈር ነው።

በትልቅ ተስፋ እና ፅናት ሲያፈላልጉት ለነበሩት ቤተሰቦቹ ፈጣሪ መፅናናቱን ይስጥ።

አምባሳደር ሚዲያ

አቶ በቀለ ገርባ በአሜሪካን ጥገኝነት ጠየቁ ለረዥም ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በግል እና በፓርቲ ደረጃ ተሳታፊ የነበሩት አቶ በቀለ ገርባ ከፓርቲያቸው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦ...
28/08/2023

አቶ በቀለ ገርባ በአሜሪካን ጥገኝነት ጠየቁ

ለረዥም ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በግል እና በፓርቲ ደረጃ ተሳታፊ የነበሩት አቶ በቀለ ገርባ ከፓርቲያቸው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በመልቀቅ በአሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።

አቶ በቀለ ለቢቢሲ እንዳሉት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ “በሰላማዊ መንገድ ለመታገልም ሆነ በግል በነጻነት መኖር” አሳሳቢ በመሆኑ በሄዱበት በአሜሪካ ለመኖር ጥገኝነት መጠየቃቸውን ገልጸዋል።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል የሆኑት አቶ በቀለ፣ በውጭ አገር ሆነው ሥልጣኑን ይዘው መቀጠለቸው ጠቃሚ ስላልሆነ እራሳቸውን ከፓርቲው ለማግለል መወሰናቸውንም ተናግረዋል።

አቶ በቀለ ገርባ ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ተፈጥሮ የነበረውን ሁከት ተከትሎ በቁጥጥር ሥር ውለው ለ18 ወራት በእስር ላይ ቆይተው ከተለቀቁ በኋላ ወደ አሜሪካ ተጉዘዋል።

አቶ በቀለ ከእስር ከወጡ በኋላ ወደ አሜሪካ ሲጓዙ ዓላማቸው የእርሳቸውን ከእስር መለቀቅ ሲጠይቅ ለነበረው የዳያስፖራ ማኅብረሰብ ምስጋና ለማቅረብ እንጂ በዚያው የመቅረት ዕቅድ እንዳልነበራቸው ጨምረው ተናግረዋል።

“ወደዚህ አገር ከመጣሁ አንድ ዓመት ከሦስት ወር ሆኖኛል። መጀመሪያ ስንመጣ የነበረኝ ዕቅድ በውጭ ከሚኖረው ሕዝባችን ጋር ተገናኝተን፣ አንደኛ ከእስር እንድንለቀቅ ላደረጉት ትግል ለማመስገን ሁለተኛ ደግሞ ወደፊት ምን ማድረግ አለብን የሚለው ላይ ለመወያየት ነበር” ብለዋል።

አቶ በቀለ አሜሪካ በቆዩባቸው 15 ወራት በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ በመቀየሩ “ወደዚያ አገር መመለሱ አስፈላጊ መስሎ አልታየኝም” ብለዋል።

ወደ አገር እንዳይመለሱ ያደረገቸው በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ሁኔታን ሲያስረዱም “በኢትዮጵያ የፖለቲካ ለውጥ ከመጣበት ወዲህ በተለይ ደግሞ ያለፈው ዓመት እጅግ አደገኛ ነው” ብለዋል።

“ከአንድ ዓመት ወዲህ ያለው በጣም የሚያሳዝን ነው። ሰዎች ከእስር ቤት እየተወሰዱ ይገደላሉ፣ የፈለገ አካል ሰው ይዞ ያስራል፣ የሰዎች አድራሻ ይጠፋል፣ ሰው ከመሬቱ ይፈናቀላል፣ ኦሮሞ ድንበሩ ተሰብሮ ቤቱ ይቃጠላል፣ በሕይወት እያለ በቁሙ በእሳት ይቃጠላል፣ እራሱ በቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ ተገድሎ እንዲቀበር የሚደረግም አለ።”

የፖለቲካ ፓርቲዎች ጽሕፈት ቤት ሙሉ ለሙሉ ማለት በሚባልበት መልኩ ተዘግተዋል የሚሉት አቶ በቀለ፤ በዚህ ምክንያት በአገሪቱ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም ብለዋል።

“በዚህ ሁኔታ ውስጥ በሕይወት እንኳ መቆየት አሳሳቢ የሆነ ደረጃ ላይ ተደርሷል። ሁለተኛ ደግሞ ወደዚያ አገር በመመለስ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ስለማይቻል እና የማመጣው ውጤት ስለማይኖር እዚሁ ለመቆየት ወስኛለሁ።”

አቶ በቀለ ከዚህ ቀደም ወደ አገር ቤት በተመለሱበት ጊዜ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ወደነበራቸው የመምህርነት ሥራ መመለስ እንዳልቻሉ ሲያስረዱ፣ “ከእስር ቤት እንደወጣሁ ዩኒቨርሲቲው እድሜህ 60 ዓመት ሞልቷል በማለት ጡረታ አስወጥቶኛል” ብለዋል።

“ከእስር ቤት እንደወጣሁ ደብዳቤ ላኩልኝ። 60 ዓመት ስለሞላህ ጡረታ ወጥተሃል አሉኝ። ጡረታዬን ለማስከበር ያደረኩት ጥረትም ሳይሳካ ቀርቷል። ዕድሜ ልኬን ስለፋበት የነበረውን ሳላገኝ ቀርቻለሁ። በዚህም ባዶ እጄን በሰው አገር ለመቅረት ተገድጃለሁ።”

አቶ በቀለ ገርባ ወደ ኢትዮጵያ ቢመለሱ ለሕይወታቸው አስጊ መሆኑን አሁን ባሉበት አገር ማሳወቃቸውን እና የጥገኝነት ማመልከቻቸውን ማስገባታቸውንም ገልጸዋል

ዮናስ ዝምታውን ሰበረ !"ድምፅ ለሆናችሁኝ በሙሉ አመሰግናለሁ!" ታግቶ የነበረው አቶ ዮናስ የሺጥላ የደረሰበትን ነገር እንዲህ ሲል አብራርቷል።  በመጀመሪያ ከኔ መጥፋት ጋር ተያይዞ ድምፅ ለ...
05/07/2023

ዮናስ ዝምታውን ሰበረ !
"ድምፅ ለሆናችሁኝ በሙሉ አመሰግናለሁ!" ታግቶ የነበረው አቶ ዮናስ የሺጥላ የደረሰበትን ነገር እንዲህ ሲል አብራርቷል።

በመጀመሪያ ከኔ መጥፋት ጋር ተያይዞ ድምፅ ለሆናችሁኝ እና ለተባበራችሁኝ በሙሉ በጣም አመሰግናለሁ :: ውለታችሁን እግዚአብሔር ይክፈል ::

እኔ ላይ የደረሰውን ነገር አጠር አድርጌ ለማስረዳት እሞክራለሁ

አርብ ሰኔ 16 ከጠዋቱ 4 ሰአት ላይ የስራ ቀጠሮ ስለነበረኝ የተቀጣጠርንበት ቦታ ቀደም ብዬ ነበር የደረስኩት:: የቀጠሮ ቦታው ቦሌ ፍሬንድሽፕ አካባቢ ሎፍት የተባለ ሆቴል ስለነበር መኪናዬን ፓርክ አድርጌ እየጠበኩ ነበር :: ከዚያ ቀን በፊት በተደጋጋሚ ለስራ ጉዳይ በተመሳሳይ ቦታ ያገኘሁት በዚህ ሰዓት በስም መጥቀስ የማልችለው ባለሃብት ደውሎ እሱ መኪና ውስጥ ሆነን ብናወራ የተሻለ ስለሚሆን ፓርኪንግ ቦታው ላይ እየጠበኩህ ነው ስላለኝ ወደሱ መኪና ሄድኩኝ :: መኪና ውስጥ ገብቼ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኃላ እዛው አካባቢ ባለቤቱ እንዳለችና ከሷ ጋር በጋራ ስለ ስራው እናውራ ብሎኝ ወደሷ መሄድ ጀመርን:: ትንሽ እንደተንቀሳቀስን ሌሎች ማንነታቸውን የማላውቃቸው የታጠቁ ሰዎች መኪናውን በማስቆምና ውስጥ ገብተው ምንም አይነት ድምፅ እንዳላሰማና እና ከነበርኩበት ጋቢና ወደ ሗላ ወንበር እንድገባ በማስገደድ የሚሉኝን ካላደረኩ እርምጃ እንደሚወስዱብኝ አስፈራርተው ፊቴን ሸፍነው ወደማላውቀው ቦታ በመውሰድ ለተከታታይ 10 ቀናት አግተውኛል::

ከዚህ በላይ ዝርዝር መረጃ መስጠት የማልችለው በአ/አ ፖሊስ ልዩ ልዩ ወንጀል ምርመራ ክፍል ጉዳዩ የተያዘና ምርመራ እየተካሄደበት በመሆኑ እንዲሁም በእኔና በቤተሰቦቼ ላይ የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ነው::

ስለዚህ ማንኛውም በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የሚፈልግ አካል ካለ በአ/አ ፖሊስ ልዩ ልዩ የወንጀል ምርመራ ክፍል ሄዶ ማጣራት ይችላል::

እኔ በጠፋሁ በ 24 ሰአታት ውስጥ ቤተሰቦቼ ከነመኪናዬ መጥፋቴን ለፖሊስ አሳውቀው ስለነበር የፖሊስ ፍለጋም የሶሻል ሚዲያ ድምፅም በጣም ከፍተኛ እንደነበር ከወጣሁ በኃላ ለመረዳት ችያለሁ ::

አፍነው የወሰዱኝ ግለሰቦች ምንም አይነት አካላዊ ጉዳት አላደረሱብኝም:: ነገር ግን የስነ ልቦናው ጉዳት እንዳለ ሆኖ በቂ ምግብና እንቅልፍ ባለማግኘቴ እንቅስቃሴ ለማድረግ አቅም አጥቼ ነበር::

በ 10 ኛው ቀን በግምት ወደ 8 ሰአት አካባቢ አይኔን ሸፍነው መኪና ውስጥ ካስገቡኝና ረዘም ካለ ጉዞ በኃላ በአገቱኝ ሰዓት የወሰዱብኝን የግል ንብረቶች የመኪና ቁልፍን ጨምሮ መልሰውልኝ ብስራተ ገብርኤል አካባቢ ከመኪናው አስወርደው ጥለውኝ ሄደዋል ::

ወደቤት እንደተመለስኩም ቤተሰቦቼ ህክምና እንዳገኝ አድርገዋል :: በእለቱም ጉዳዩ ተይዞ ወደነበረበት ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ የደረሰብኝን ጉዳይ አስረድቼ ቃሌን ሰጥቻለሁ ::

መኪናውንም ሰኔ 16 ፓርክ ባደረኩበት ሎፍት ሆቴል ፓርኪንግ ቦታ ለ 10 ቀናት ሳይንቀሳቀስ መቆየቱን ፖሊሶች በአሻራ ምርመራ አረጋግጠው መልሰውልኛል ::

የመጥፋቴን ዜና ከሰማችሁበት እለት ጀምሮ ድምፅ ስትሆኑኝ ለነበራችሁ በፀሎት በሃሳብ ቤተሰቦቼን በማፅናናት በተለያየ መንገድ ለረዳችሁኝ በሙሉ እንዲሁም ለአዲስ አበባ ፖሊስ እና ለየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አመራሮችና አባላት በሙሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ :: ከነበርኩበት ቦታ ለመውጣት የእናንተ ድምፅ መሆን እና የቤተሰቦቼ ጥረት ትልቁን ድርሻ ይወስዳልና ከልብ አመሰግናለሁ ::

ድንገት ለስራ እንደወጡ በዛው የቀሩ የት እንደገቡ ሳይታወቅ ብዙ ጊዜያት ያለፉ ብዙ ዜጎች ይኖራሉና ለኔ ያደረጋችሁትን ትብብር ለነሱም እንድታደርጉ አደራ እላለሁ ::

ምናልባት ዛሬ ላይ እንደቀልድ የሚታዩ ነገሮች ነገ በየቤታችን የሚመጣ ጉዳይ ሊሆን ይችላልና በየትኛውም አጋጣሚ ከቤት ስትወጡ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ አትርሱ ::

አመሰግናለሁ !!

ስዊድን ሀገር ለታዳጊ ሀገራት የተዘጋጀውን ስኮላርሺፕ ለማግኝት ወይም በዝቅተኛ  በክፍያ ለመማር የሚያስፈልጉ ሙሉ መረጃ ቪዛን ጨምሮ ምንም አይነት ክፍያ ለደላላ ሳይከፍሉ ራስዎ ስቴፑን ተከት...
01/07/2023

ስዊድን ሀገር ለታዳጊ ሀገራት የተዘጋጀውን ስኮላርሺፕ ለማግኝት ወይም በዝቅተኛ በክፍያ ለመማር የሚያስፈልጉ ሙሉ መረጃ ቪዛን ጨምሮ ምንም አይነት ክፍያ ለደላላ ሳይከፍሉ ራስዎ ስቴፑን ተከትለው ማመልከት ይችላሉ ።
መረጃውን ለሌሎችም ሼር በማድረግ ያድርሱ

JobsScholarship Study in Sweden for Ethiopian Students: Cost, Eligibility, Visa By admin - July 1, 2023 Share FacebookTwitterPinterestWhatsApp With its education system ranked amongst the best in the world, Sweden has been referred to as the most sustainable nation across the globe and also the happ...

ኑሮውን በስዊድን ስቶክሆልም ያደረገው ተወዳጁ አርቲስት አለምሰገድ የልጅ አባት ሆነ
12/06/2023

ኑሮውን በስዊድን ስቶክሆልም ያደረገው ተወዳጁ አርቲስት አለምሰገድ የልጅ አባት ሆነ

artist teddy Afro in Addis A public monetary administration gathering pointed toward fortifying public area bookkeeping in Africa is in progress in Ad...

ፀጋ ነፃ ወታለች!! ድምፅ የሆናችኋት በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ!! ወይዘሪት ፀጋ ከሳምንት በላይ ተጠልፋ ከቆየችበት ነፃ ወታ በፖሊስ ወደ ሐዋሳ ከተማ ማቅናቷን ስምተም ደስ ብሎናል!!  እን...
01/06/2023

ፀጋ ነፃ ወታለች!!

ድምፅ የሆናችኋት በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ!!
ወይዘሪት ፀጋ ከሳምንት በላይ ተጠልፋ ከቆየችበት ነፃ ወታ በፖሊስ ወደ ሐዋሳ ከተማ ማቅናቷን ስምተም ደስ ብሎናል!! እንኳን ደስ አላችሁ !!

ተጠርጣሪው ከፖሊስ ሸሽቶ ወደ ጫካ በመግባቱ በፖሊስ ክትትል እየተደረገበት ነው።

ለነፃነቷ ከፖሊስ ክትትል እስከ ድምፅ በማሰማት የተባበራችሁ በሙሉ ምስጋና ይድረሳችሁ።

ወ/ሪት ጸጋ ከታገተችበት ነጻ ወጥታ በፖሊስ ወደ ሀዋሳ መመለሷን የሀዋሳ ከተማ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ቢሮ መኒሳ #ለብስራት ሬድዮ አረጋግጠዋል፡፡

ይሁንና ተጠርጣሪው ግለሰብ እስካሁን በቁጥጥር ስር እንዳልዋለም ታውቋል። ለ10 ቀናት ያህል በሐዋሳ ከተማ ከንቲባ የግል ጠባቂ ኮንስታብል የኋላመብራት ወ/ማሪያም ታግታ የቆየችው ፀጋ በላቸው፤ ከአጋቿ ቁጥጥር ነጻ በመውጣት ወደ ሐዋሳ ተመልሳለች ተብሏል።

የፀጋ'ን ነፃ መውጣት የሲዳማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ መግለጫ አውጥቷል!

በመግለጫውም በክልሉ የፀጥታ ግብረ ሀይል አማካኝነት በተደረገ የተቀናጀና በቴክኖሎጂ የታገዘ ጠንካራራ ክትትል ወሪ/ት ፀጋ በላቸውን ከተጠርጣሪ ወንጀለኛ ማስመለጥ መቻሉን ገልፇል፡፡

የፀጥታ ግብረ ሀይሉ ተጠርጣሪ ወንጀለኛ የኃላመብራት ወ/ማሪያምን በቁጥጥር ስር ለማዋል ባደረገው የተቀናጀ ኦፕሬሽን ከትላንት 23/09/2015ዓ.ም ጀምሮ በምስራቅ ጉጂ ዞን ቦሬ ወረዳ ጀምሮ ተጠርጣሪ ወንጀለኛውን በመከታተልና መፈናፈኛ በማሳጣት በዛሬው እለት በሻፋሞ ወረዳ ሹሮ ቀበሌ ወሪ/ት ፀጋ በላቸውን ከግለሰቡ ማስጣል መቻሉንና…

ግለሰቡ ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ ወደጫካ መግባቱን ገልፆ ፣ የፀጥታ ግብረ ሀይሉ ያልተቋረጠ ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪ ወንጀለኛን በመከታተል ላይ እንዳለ አሳውቋል፡፡

የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮና ግብረሃይሉ ለዚህ ስምሪት መሳካት ከፍተኛ አስተወጽኦ ላበረከቱ ለብሔራዊ መረጃ ደህንነት፣ ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ለኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል፣ ለሻፋሞ ወረዳ አስተዳደርና የህብረተሰብ ክፍል ልባዊ ምስጋና አቅርቧል፡፡

ተጠርጣሪ ወንጀለኛውንም በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ ለማቅረብ በጫካው ውስጥ አሰሳ እየተካሄደ እንደሆነና የሚገኙ ውጤቶችን በቀጣይ እንደሚያሳውቁ ገልፀዋል፡፡

አምባሳደር ሚዲያ
Ambassador media

 ?ስለ  #ፀጋ እህቷንና ባለቤቷን አውርቻቸው አንጀት በሚበላ ሁኔታ እንዲህ አሉኝ:-  "ወሬ ስታመላልስ የነበረችው የስራ ባልደረባዋ ህፃን ልጅ አለኝ በሚል ሰበብ ትላንት በዋስ ተፈታ ቤቷ ገ...
30/05/2023

?

ስለ #ፀጋ እህቷንና ባለቤቷን አውርቻቸው አንጀት በሚበላ ሁኔታ እንዲህ አሉኝ:-

"ወሬ ስታመላልስ የነበረችው የስራ ባልደረባዋ ህፃን ልጅ አለኝ በሚል ሰበብ ትላንት በዋስ ተፈታ ቤቷ ገብታለች"

የ23ዓመቷ ፀጋ በላቸው በስራ ምክንያት ከወልቂጤ ወደ ሀዋሳ ሄዳ ተከራይታ ዳሽን ባንክ ስራ ከጀመረች ገና አንድ አመቷ ነው!በስራ ባልደረባዋ አማካኝነት ስልኳን የተቀበለው ይህ ሰው በተደጋጋሚ ያስቸግራት እንደነበርና አግቷት እንደጠፋ መረጃውን መጀመሪያ የሰሙትም ከሷ ነው!

ፀጋ ከመጥፋቷ በፊት ለማናጀሯ "ምንም አይነት አደጋ ህይወቴ ላይ ቢደርስ በሷና በሱ ምክንያት ነው!እወቁልኝ" ብላም ተናግራለች!!

ከአንድ ወር በኋላ ስለሚደረገው ሰርጓ እየተዘጋጁ የነበሩት አባት ታመው አዲስ አበባ ሆስፒታል የሚገኙ ሲሆን መጥፋቷንም እስካሁን አላወቁም!!

አጋቹ ጉልበተኛ ከወር በኋላ ሊያገባት የተዘጋጀውን ሚስቱን ቀምቶ በተደጋጋሚ ባል ጋር እየደወለ ሲያስፈራራውና እገልሀለው ብሎ እየዛተበት ነው!ቤተሰብ ጋርም ለሽምግልና ተዘጋጁ በግድ አገባታለሁ ብሏቸዋል!!

የቤት እቃ እያሟሉ፣ስለጋብቻ የቤተክርስቲያን ትምህርት እየተማረች የነበረችው ፀጋ ሀገረሰላም ይዟት ሄዶ ለማምለጥ ስትሞክር እንደወደቀች ጭምር የአይን እማኞች ተናግረዋል!!

ከዛ በኋላ ግን መረጃ ቀድሞ እየደረሰው ከመድረሳቸው በፊት እየሸሸ ሲሆን ሁላችንም ፀጋን እንደ እህታችን ቆጥረን ያለችበትን ልንጠቁምና ስለፍትህ ልንጮህ ይገባል🙏 እባካችሁን #ሼር በማድረግ የት እንዳሉ በቶሎ እንድረስበት🙏

ሄኖክ ፍቃዱ

Adress

Rosengatan 8
Sundyberg
17270

Aviseringar

Var den första att veta och låt oss skicka ett mail när Ambassador media postar nyheter och kampanjer. Din e-postadress kommer inte att användas för något annat ändamål, och du kan när som helst avbryta prenumerationen.

Kontakta Affären

Skicka ett meddelande till Ambassador media:

Dela

Typ