Dana Tube

Dana Tube ዳና የብዕር ቀለማት!

🌼ይ 🌼ታ 🌼የ 🌼ኛ 🌼ል 🌼ልጆችሽ ተዋደው ዕርቅ ሆኖ መንደሩለእኔ ይታየኛል ፍቅርን ሲዘምሩበአድሱ አመት መንፈስ አድስ እንደገናፈጣሪ አብዝቶልን ሲሳይና መናሰላማችን በዝቶ በሁሉ ሰው ጉያዕሴታች...
11/09/2020

🌼ይ 🌼ታ 🌼የ 🌼ኛ 🌼ል 🌼

ልጆችሽ ተዋደው ዕርቅ ሆኖ መንደሩ
ለእኔ ይታየኛል ፍቅርን ሲዘምሩ
በአድሱ አመት መንፈስ አድስ እንደገና
ፈጣሪ አብዝቶልን ሲሳይና መና

ሰላማችን በዝቶ በሁሉ ሰው ጉያ
ዕሴታችን ሆኖ ዘመን መሻገሪያ
እንደ አደይ አበባ ይፈካል ፊታችን
የይቅርታን ካባ ደርቦ ልባችን

በረከት ሲሳዩ ተርፎ ተትረፍርፎ
ማጀቱ ሞልቶልን ከጎረቤት አልፎ

ይህን ዘር የሚሉት የልክፍት በሽታ
ከውስጣችን ነቅሎ አርቆልን ጌታ
አለም ሲቀናብን ተዋደን አምሮብን
የጥበብ ልብሳችን ሲያንጸባርቅብን
ሙሉ ኢትዮጺያ ሆኖ ዳር እሰከዳር ጰንቶ
የእፎይታ ሳቅ ስቀን ልባችን እረክቶ
ይህ ሁሉ ይታየኛል እልፍ ስንሻገር
በአድሱ አመት መንፈስ በሰላም በፍቅር
ተስፋን የሰነቀ ምህረት የበዛበት
በቃ ይታየኛል ይሄ አድድሱ አመት

ሀዘን ተወግዶ ደስታ ተተክቶ
ሰላም እና ፍቅር ከሁሉ ቤት ገብቶ
ወንድምአማች ሁነን
እህት አማች ሁነን
መልካምን አንግበን
ሰው በመሆን አመነን

ዘር ብሄር ሳይከፍለን ድንበር ሳይገድበን
ሀይማኖት ሳይለየን ከልብ ተዋደን
ዳግም በዚህ አመት በአድሱ ተስፋችን
ኢትዮጲያዊ እንሁን ለሁሉ ወገናችን
ያኔ ኢትዮጲያዬ

ኢትዮጵያ ተብለሽ ሀበሻ ተብለሽ
በሁሉም ልብ ውስጥ ላጠፊ ተጽፈሽ
ጨላማው ብርሀን ደመናው ይጠራል
ስምሽ እጅግ ገኖ አለም ላይ ይጠራል

🌼🍃🌼🍃🌼🍃🌼🍃🌼🍃🌼🍃🌼🍃🌼🍃🌼🍃🌼🍃🌼🍃🌼🍃🌼🍃

✍ አብዲ ዳና
http://t.me/danatibeb
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

26/07/2020

ዳና የብዕር ቀለማት !
የተለያዩ የጥበብ ስራዎችን እና ስነ-ጽሁፎችን የሚያገኙበት የሚከታተሉበት ቻናል ነው!

• በዩቲዩብ ለመከታተል ቻናልችንን subscribe አድርጋችሁ ቤተሰብ መሆን ትችላላችሁ '

https://www.youtube.com/channel/UCva_awvx1rEoBVJCjqIZGRA

ደና ቲዩብ

Address

شارع منيع عبدالله
Riyadh
12797

Opening Hours

9am - 5pm

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dana Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share