Wolaita Tube

Directions

Wolaita Tube YouTube :- Saro Tube

✨ ጊፋታ ፋሽን ሾው 2026 | Kana Pictures በመስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም. ከ8፡00 ሰዓት ጀምሮ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ግቢ የተካሄደው ጊፋታ ፋሽን ሾው የተለያዩ ዲዛይነሮችን...
21/09/2026

✨ ጊፋታ ፋሽን ሾው 2026 | Kana Pictures

በመስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም. ከ8፡00 ሰዓት ጀምሮ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ግቢ የተካሄደው ጊፋታ ፋሽን ሾው የተለያዩ ዲዛይነሮችን፣ ሞዴሎችን፣ ሜካፕ አርቲስቶችን፣ ፎቶግራፈሮችን፣ ቪዲዮግራፈሮችን እና የሚዲያ ኢንፍሉዌንሰሮችን በአንድ ራዕይ ሰብስቧል።

#ዲዛይነር ብሩክ ለማ ይህንን አስደናቂ የፋሽን ሾው በማስተባበር፣ የተለያዩ የፈጠራ ባለሙያዎችን በአንድ ራዕይ ለማገናኘት፣ የሞዴሎችን ዝግጅትና የመድረክ ሂደት ለማስተባበር እና ሀሳባችንን ወደ ተጨባጭ አድርጓል

👗 የተሳተፉ ዲዛይነሮችና ፈጣሪ ድርጅቶች

• Boss Grand Garment
• Design by Serk
• Gize Design
• Selamwit Garment
• Misgana Design — ቦርሳና አክሰሰሪዎች

💄 ሜካፕ እና ሞዴሊንግ

Model Meron እና Touch by Rediet ጨምሮ ብዙ ተሰጥኦ ያላቸው ሞዴሎችና የሜካፕ ባለሙያዎች በመሳተፍ የዲዛይነሮቹን ስራ በመድረክ ላይ ህያው አድርገዋል።

📸🎥 ፎቶ፣ ቪዲዮ እና ሚዲያ

Kana Pictures የዚህን የፈጠራ ጉዞ በፎቶ፣ በቪዲዮ እና በሚዲያ ምርት በመመዝገብ የተለየ ሚና ተጫውቷል።

🌿 ከፋሽን ሾው በላይ — አንድ ራዕይ

ጊፋታ ለእኛ በቀላሉ አንድ የፋሽን ዝግጅት አይደለም። ጊፋታ አዲስ ጅማሬን፣ ከአሮጌው ወደ አዲሱ መሻገርን እና ባህላችንን በአዲስ ትውልድ ፈጠራ ማብራትን ይወክላል።

እኛ የምንፈልገው ባህላችንን በቀድሞው መልኩ ብቻ ማስቀመጥ ሳይሆን፣ በአዲስ ሀሳብ፣ በፋሽን፣ በሙዚቃ፣ በሚዲያ እና በፈጠራ ለአለም ማሳየት ነው። 🌍

🔥 የወደፊቱ ትልቅ ህልማችን

ይህ የመጀመሪያው እርምጃችን ነው።

ህልማችን ጊፋታ ፋሽንን በየዓመቱ የሚካሄድ ትልቅ የፋሽንና የባህል መድረክ ማድረግ ነው።

በየዓመቱ ከወላይታም ሆነ ከሌሎች አካባቢዎች የሚመጡ ወጣት ዲዛይነሮች፣ ሞዴሎች፣ ሜካፕ አርቲስቶች፣ ፎቶግራፈሮች፣ ቪዲዮግራፈሮች፣ ሙዚቀኞች እና ሚዲያ ኢንፍሉዌንሰሮች በአንድ መድረክ ተሰባስበው ችሎታቸውን የሚያሳዩበት፣ የሚተባበሩበት እና አዲስ እድሎችን የሚፈጥሩበት የጊፋታ ፋሽን ፌስቲቫል መፍጠር ነው።

የወጣቶች ፈጠራ የሚገናኝበት፣ የወላይታ ባህል የሚታይበት፣ አዲስ ችሎታ የሚወጣበት እና የWolaita fashion ወደ ዓለም የሚደርስበት መድረክ። 🌍🔥

ይህን ራዕይ በአንድ ሰው ብቻ ማሳካት አይቻልም። ይህ የሁላችንም ራዕይ ነው።

🙏 ለተሳተፋችሁ፣ ለሰራችሁ፣ ለደገፋችሁ እና በዚህ ራዕይ ስላመናችሁ ሁላችሁንም ከልብ እናመሰግናለን።

ይህ መጨረሻ አይደለም።
ይህ የታላቅ ጉዞ ጅማሬ ነው።

🔥 GIFАATA — አዲስ ጅማሬ
👗 FASHION — የፈጠራ ቋንቋ
🌿 WOLAITA — ባህላችን
🌍 ዓለም — መድረካችን

የጊፋታ ፋሽን ሾው አስተባባሪ — ዲዛይነር ብሩክ ለማ
Production & Media — Kana Pictures 📸🎥

#የጊፋታፋሽንሾው #ወላይታ #ወላይታሶዶ

ቅዳሜ ምሽት . . .  Nahom records inc 🔥🔥በበርካታ ነጠላ ዜማዎቹ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው በተለይም  #ዎዜ እና   #ዶስዶሬ የተሠኙት ስራዎቹ በሚልየኖች የታዩለት ድምጻዊ ...
18/09/2026

ቅዳሜ ምሽት . . . Nahom records inc 🔥🔥
በበርካታ ነጠላ ዜማዎቹ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው በተለይም #ዎዜ እና #ዶስዶሬ የተሠኙት ስራዎቹ በሚልየኖች የታዩለት ድምጻዊ አዲስ የሙዚቃ ቪድዮ ቅዳሜ ምሽት ወደ እናንተ ይደርሳል።

Yoo Yoo Gifaata 🌻🌼🌼
17/09/2026

Yoo Yoo Gifaata 🌻🌼🌼

ቅዳሜ ምሽት...በ Nahom records inc 🔥 ከዚህ ቀደም ለህዝብ ባደረሳቸው ድንቅ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎቹ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያተረፈው ድምጻዊ Didi Gaga  አዲስ የሙዚቃ ስራ  #አር...
17/09/2026

ቅዳሜ ምሽት...በ Nahom records inc 🔥
ከዚህ ቀደም ለህዝብ ባደረሳቸው ድንቅ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎቹ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያተረፈው ድምጻዊ Didi Gaga አዲስ የሙዚቃ ስራ #አርሴ ቅዳሜ ምሽት ወደ እናንተ ይደርሳል!!

ጊፋታ የፋሽን ሾው |Gifaata Fashion Show 2026 የወላይታን ባህል፣ ውበትና ማንነት ለዓለም እናሳያለን! ❤️💛🖤በዚህ ልዩ የጊፋታ ፋሽን ሾው ውስጥ የተለያዩ የፈጠራ ዲዛይነሮች፣ ...
17/09/2026

ጊፋታ የፋሽን ሾው |Gifaata Fashion Show 2026

የወላይታን ባህል፣ ውበትና ማንነት ለዓለም እናሳያለን! ❤️💛🖤

በዚህ ልዩ የጊፋታ ፋሽን ሾው ውስጥ የተለያዩ የፈጠራ ዲዛይነሮች፣ ሞዴሎች፣ ሜካፕ አርቲስቶች፣ ፎቶግራፊና ቪዲዮ ፕሮዳክሽን ባለሙያዎች በመተባበር የወላይታን ባህልና ታሪክ በአዲስ የፈጠራ መንገድ ለዓለም ለማስተዋወቅ ተሳትፈዋል።

👗 ፋሽን • ፈጠራ • ባህል • ውበት •

📅 መስከረም 9፣ 2019 ዓ.ም.
⏰ 8:00 ሰዓት
📍 ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ

ከትውፊት ወደ ዘመናዊ ፋሽን — የወላይታ ታሪክን በአዲስ ትውልድ እንጽፋለን።

📸 KANA PICTURE

የወላይታን ውበት እንመልከት፣ ባህሉን እንሰማ፣ ታሪኩን ለዓለም እናቅርብ! 🌍

#ወላይታ #ጊፋታ #የወላይታባህል #የኢትዮጵያፋሽን

በሙዚቃው የስሙ መጠሪያ ያገኘው ወጣት ድምፃዊ ከዎዜ ጋር በአለም ሁሉ የተደመጠው አርቲስት !በጅማሮ የሙዚቃ ምኞቱን በማጀብና በዜማ ስራ አሀዱ አለ ሳይቆይ ባህላዊ ሙዚቃ ይዞ መጣ ከህዝብም ጋ...
16/09/2026

በሙዚቃው የስሙ መጠሪያ ያገኘው ወጣት ድምፃዊ ከዎዜ ጋር በአለም ሁሉ የተደመጠው አርቲስት !

በጅማሮ የሙዚቃ ምኞቱን በማጀብና በዜማ ስራ አሀዱ አለ ሳይቆይ ባህላዊ ሙዚቃ ይዞ መጣ ከህዝብም ጋር ተዋወቀ ።

ከ''Lachchiyaw'' ጀምሮ ''Aymalee Saro'' ተወዳጅ መዚቃ ከዲዲ ጋር አሰምቶን ስሙን ከስዩም ጋጋ ወደ ዲዲ ጋጋ አሰቀይሮታል ።

ወጣት ድምፃዊ ዲዲ ጋጋ የወላይታን ህዝብ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ከታሪክ መነሻ ጋር እያዋሄድ ከዳር እሰከ ዳር አስደምሞታል ።

ከህብሬ ዜማው መለያ የድል ሙዚቃ ዎዜን ደግሞ ከወላይታ አንስቶ በኢትዮጵያ አፍርካ እና በመላው አለም ተደስቶበታል ።

''La wozee''

ከባሮ ባሮ ልዩ ስራ በኦሌጄ ደምቆ ከ''oo Sorry '' ጋር ዳግም ከፍ አለ ሳይቆይም የጋንጌ ዜማ ዘመኑን በዋጄ ሁኔታ ተሰርቶ ለተወዳጆች አድርሷል ።

ዲዲ ብቻውን ቢሆን በህብረት እጅግ መሳጭ የህዝብ አደበት በሆነ መንገድ በምርጥ ቃላቶች የተጨበጨበለት እንቁ የወላይታ ዘመናዊ ድምፃዊ ነዉ ።

ከነጠላ ዜማ ባሻገር በአልቤም ደረጃ ''Doshkore ''Xoona na'aa, Maahelaanna Hammma yettiyo የመሳሰሉ ድንቅ ሙዚቃዎችን የያዘውን ስራ አቅርቦ አቅሙን ያሳየ ተስፈኛ ወጣት ሙዚቀኛ ነው።

ዲዲ ለጊፋታ በዓል በዩኔስኮ መመዝገብ ትልቅ አስተዋጽኦ ካደረጉ ወጣት አርቲስቶች ቀዳሚ መሆኑን ላለፉት ረጅም አመታት የወላይታ ህዝብ ይመሰክራል ።

አሁድ በዚህ ደማቅ ደግሞም በዩኔስኮ ከተመዘገበ የመጀመሪያ በዓሉን ስናከብር የወላይታ ህዝብ ማህበራዊ ኤኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በስፋት የያዘውን ''Arsee ''የተሰኘውን አድስ ሙዚቃ ይዞ ብቅ ብሏል ።

ከኑሮ ዘይቤ ዉሎ አዳሩን የህዝቡን እስትንፋስ የልማትና ኤኮኖሚ ተስፋና የአስተዳዳር አድሎዎ ፀድቶ ነፃ ወላይታ እንዲትፈጠር ከታገሉ ምርጦች መካከል አንዱ ነው ።

''Arsee ''Did Gaga (Maahiyaw )

ዚካ (Ziikaa )  የወላይታ ባህላዊ ሙዚቃ በልዩነት ጠንካራ ሠራተኛና ወኔ ያላቸውን ድንቅ ወላይታዊያንን የሚያወድስ ሙዚቃ ነው !የወላይታ ባህል ቋንቋ እና ታሪክ እንዲሁም ቅርስና ወግ ከሙ...
16/09/2026

ዚካ (Ziikaa ) የወላይታ ባህላዊ ሙዚቃ በልዩነት ጠንካራ ሠራተኛና ወኔ ያላቸውን ድንቅ ወላይታዊያንን የሚያወድስ ሙዚቃ ነው !

የወላይታ ባህል ቋንቋ እና ታሪክ እንዲሁም ቅርስና ወግ ከሙሉ ክብሩ ተራምዶ ለአለም እንዲደርስ የራሱን አሻራ ለረጅም አመታታ ያኖረ እንቁ ድምፃዊ ።

አርቲስት አለማየሁ ዛሳ በወላይታ ምድር ከዜጠናዎች ማጠናቀቂያ ጀምሮ በወላይትኛ ቋንቋ የህዝቡን ማንነት መገለጫ የሆኑትን በግልፅ ቋንቋ ጥበቡን ተጠቅሞ ገልጿል ።

ከልጆች ጨዋታ እሰከ አዋቂዎች ተግባር ከሴቶች ስራ መነሻ አድርጎ የአማዎራዎችን ተፅዕኖ ፈጣሪነት በግልፅ ለአለም በሙዚቃ መንገድ ተንትኖታል ።

ድምፃዊ አለማየሁ ከአልበም ስራ እሰከ ነጠላ ዜማዎች በየግዜው ደማቅ ስራዎቹን ለህዝቡ ስያቀርብ ቆይቷል።

ከጫዳ ኮሻ ጋይሊያ ዜማ እሰከ ሂዲዲ ተወዳጅ ያስደመመው አባታችን ጊፋታን በተመለከተ ''ዎላይታው ሀሹ'' በሚል ደግሞ ከዩኔስኮ ምዝገባ ጋር በህብረት አሰምቶናል ።

አሁን ደግሞ ከጊፋታ በዓል ማክበሪያ ዋዜማ ሌላ አድስ ስራ #ከቦማንዛ ጋር ይዞ መጥቷል ።

''Zikoo '' የወላይታን ጥንካሬ ወኔ አይበገሬነት ከስራ ወዳድነትና ከጀግንነት ጨ
ጭምር የሚገልፅ ስራ ሰርቷል።

ይህን ስራ ለአለም ማህበረሰብ በማስተዋወቅ ለአባታችን ለታላቃችን ለአንጋፋው ድምፃዊ አለማየሁ ዛሳ ድጋፋችንን እናሳይ ።

" #🇧🇪Ziikaa ''

Gifaatay Wolayttaw Bayrra
Ooratta nu layttaw Xeeraa

መልካም ዕድል !

ዮ ዮ ጊፋታ

ታላቅ የመጽሐፍ ምረቃ ጥሪ ቅዳሜ ጧት በጊፋታ ዋዜማ ላይ   በጉታራ አዳራሽ 📖===========================ለወላይታ ሕዝብ  እና አከባቢ በሙሉ ጊፋታ በዩኔስኮ Gifaatay Yu...
14/09/2026

ታላቅ የመጽሐፍ ምረቃ ጥሪ ቅዳሜ ጧት በጊፋታ ዋዜማ ላይ በጉታራ አዳራሽ 📖
===========================
ለወላይታ ሕዝብ እና አከባቢ በሙሉ ጊፋታ በዩኔስኮ Gifaatay Yunskon የተሰኘው ድንቅ መጽሐፍ በጊፋታ ወር በመስከረም 09/01/2019 ዓ/ም ቅዳሜ ጡዋት ከ2:00--6:00 ሰዓት በወላይታ ጉታራ አዳራሽ ይመረቃል።

"የመጽሐፉ ሂዘት ጊፋታ ከወላይታ ምድር እስከ ዩኔስኮ ዓለም ቅርስነት" ይህ መጽሐፍ የወላይታን ሕዝብ ታሪክ፣ መልክዓ - ምድር፣ ኢኮኖሚና ማኅበራዊ መስተጋብር በጥልቅ ምርምርና ውብ በሆነ የአጻጻፍ ስልት ዳስሶ የሚያቀርብ ድንቅ የብዕር ውጤት ነው።

የጊፋታን በዓልን ጥልቅ ትርጉምና ፍሌስፍና ከመተንተን ባሻገር፤ ከባህላዊ አልባሳት ፣ ከእምነት፣ከአብሮነት እና ከብዙ ባህላዊነት (Multiculturalism) ጋር ጠንካራ ቁርኝት በተዋጣ መንገድ ለማሳየት ሞክረዋል። በተላይም የጊፋታ በዓል ዓለም አቀፍ ዕውቅና አግኝቶ በዩኔስኮ (UNESCO) የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበበትን ሂደቱና ፋይዳ የሚያብራራ ክፍል መጽሐፍ በመሆኑ ልዩ እውቅና እና ክብር ሰጥቶታል ።

መጽሐፉ የትውልድን ማንነትና ባህላዊ እሴት ጠብቆ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የሚያስተዋውቅ የታሪክና የባህል ሰነድ በመሆኑ፤ የታሪክ ተመራማሪዎች፣ የባህል አፍቃሪያን እና ማንነቱን ማወቅ የሚሻ ማንኛውም አንባቢ ሊያነበው የሚገባ ድንቅ መጽሐፍ ነው።

ዛሬ በባህላችን መሠረት በደቦ (ዳጉዋን) እንሰት እየፋቅን ዳታ እየዳጥን ለጊፋታ በዓል እየተዘጋጀን ነው ።ስለ ደቦ እና እንሰት፦ "እንደምትመለከቱት፣ የባህላችን ዋነኛ መገለጫ የሆነውና በአን...
08/09/2026

ዛሬ በባህላችን መሠረት በደቦ (ዳጉዋን) እንሰት እየፋቅን ዳታ እየዳጥን ለጊፋታ በዓል እየተዘጋጀን ነው ።

ስለ ደቦ እና እንሰት፦ "እንደምትመለከቱት፣ የባህላችን ዋነኛ መገለጫ የሆነውና በአንድነት የምንቆምበት የደቦ (ዳጉዋን) ሥርዓት ተኪዶበታል። እናቶቻችን እና እህቶቻችን በአንድነት ተሰባስበው፣ በደመቀ ባህላዊ ዜማ የታጀበ እንሰት የመፋቅ ሥራ እያከናወኑ ይገኛሉ። ይህ ተግባር ምግብ ማዘጋጀት ብቻ ሳይሆን፣ የማህበረሰቡን ትብብር፣ ፍቅር እና አንድነት በተግባር የሚያሳይበት ትልቅ መድረክ ነው።"
"ይህ ዛሬ የሚፋቀው እንሰት ለጊፋታ በዓል ልዩ ድምቀት የሚሰጡ ባህላዊ ምግቦችን ለማዘጋጀት የሚውል ሲሆን፣ መላው ማህበረሰብ በአዲስ ተስፋ እና በታላቅ ደስታ በዓሉን ለመቀበል ያለውን ዝግጁነት ያሳያል።

አንድነት ኃይል ነው፤ ባህል ደግሞ መታወቂያችን!"

እናቶቻችንና እህቶቻችን በአንድነት ሆነው ለበዓሉ የሚሆን እንሰት እየፋቁ ይገኛሉ። ይህ የጋራ ስራችን ውብ የሆነውን የወላይታን መረዳዳት እና አንድነት በጉልህ የሚያሳይ ነው። ጊፋታን ለመቀበል ቤታችንም ልባችንም ክፍት ነው!

የጊፋታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በማህበረሰቡ ዘንድ ታላቅ ባህላዊ የእንሰት ፋቃ የደቦ (ዳጉዋን) መርሃ-ግብር ተካሄደ። የዘመን መለወጫ በዓሉን በታላቅ ድምቀት ለማክበር የሚደረገው ዝግጅት አንዱ አካል የሆነው ይህ የደቦ ሥርዓት፣ የማህበረሰቡን የቆየ የአንድነትና የመረዳዳት እሴት በተግባር ያሳየ ሆኗል። እናቶችና እህቶች ለበዓሉ የሚሆኑ ባህላዊ ምግቦችን ለማዘጋጀት በጋራ እንሰት የፋቅን ሲሆን፣ ይህም በዓሉ በጋራ የመስራትና በጋራ የመብላት ባህልን የሚያጠናክር መሆኑን አመላካች ነው።"

Gelila Hailu 🙏

Ee bessoos wolaytta woga nu naati laatan gakkagaEe yootos nu aawa minota nu naati laatan gakkagaSaro Entertainment
30/08/2026

Ee bessoos wolaytta woga nu naati laatan gakkaga
Ee yootos nu aawa minota nu naati laatan gakkaga
Saro Entertainment

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

Address

S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolaita Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share