29/12/2021
#አይዞሽ እራሴ💪👸
ባንቺ ብቻ አይደለም.....
የሂወትን ጉዞ የመኖርን መንገድ
ማን ቀጥ ብሎ ሄደ ማን ሳይወላገድ
ማንስ ነው የኖረ ሁሌ እንደሳቀ
ለአፍታም ሳይከፋው ሰርክ እንደቦረቀ
ማንስ ይሆን ከቶ በንባ ምንጭ ያልራሰ
ሀዘን ሳይዳስሰው ብሶት ሳይጎበኘው
በአልጋ ባልጋ ድሎት ዛሬን የደረሰ?
💁 #ማንም🙌
አየሽ አይደል እኔ
ይብዛም ይነስ እንጂ
በመኖር እንቅፋት ሁሉም ተደናቅፏል
የግዜን አቀበት በማቃሰት አልፏል
የተፃፈለትን የእጣ ፋንታ ድርሻ
የማሩን የሬቱን የ'ሰው'ነት ቅምሻ
መራራ ጣፋጩን
ውጧል የድርሻውን
እናም እልሻለው........
አሁንሽ ቢጨልም ባይሆን እንዳሰብሽው
#አይዞሽ እራሴ💪
ባንቺ ብቻ አይደለም እስኪነጋ ድረስ በትግስት እለፊው
ቢለያይ ነው እንጂ ስፋቱ ጥበቱ
ሽንቁር አልባ ኗሪ የለም በምድሪቱ🙌
Kiya
Send a message to learn more