05/09/2026
የእኔ ሮብንሰን የሕይወቴ ሃሁ
እኔ በ1632 ዓ.ም. በዮርክ ከተማ ተወለድኩኝ። ቤተሰቤ የተከበር ቢሆንም የዚያ አገር ተወላጅ አልነበረም፤ አባቴ ከበርሊን የመጣ የውጭ ዜጋ ነበር። መጀመሪያ በሃል (Hull) ከተማ ላይ ነበር የሚኖረው። በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርቶ ብዙ ሀብት ያፈራ ሰው ነው፤ ከዚያም ንግዱን ትቶ በዮርክ ከተማ ውስጥ መኖር ጀመረ። በዚያ ቆይታው እናቴን አገባ። የእናቴ ዘመዶች ሮቢንሰን ይባሉ ነበር፤ በዚያ አገርም በጣም የተከበሩ ቤተሰቦች ነበሩ። ስለዚህ እኔም ሮቢንሰን ክሮይትስናየር ተብዬ ተጠራሁ።ነገር ግን በእንግሊዝኛ ቃላት ማለትም በተለመደው የአነጋገር ለውጥ ምክንያት፣ በኋላ ክሩሶ (Crusoe) ተባልን። እኛም ራሳችንን በዚያ ስም እንጠራና እንጽፋለን። ጓደኞቼም ሁልጊዜ ክሩሶ ብለው ይጠሩኝ ነበር።ሁለት ታላላቅ ወንድሞች ነበሩኝ። ከእነርሱ አንዱ በፍላንደርስ የእንግሊዝ እግረኛ ጦር ክፍል ውስጥ ሌፍተናንት ኮሎኔል ነበር። ይህ ጦር ቀደም ሲል በታዋቂው ኮሎኔል ሎክሃርት ይመራ ነበር። ወንድሜ በዱንከርክ አቅራቢያ ከስፔናውያን ጋር በተካሄደ ጦርነት ተገደለ።
ሁለተኛው ወንድሜ ምን እንደ ሆነ ግን ፈጽሞ አላወቅም፤ እንዲሁም አባቴና እናቴም ምን እንደ ሆነ አላወቁም ነበር።ከቤተሰቡ ሦስተኛ ልጅ ስለነበርኩ እና ማንኛውም አይነት የሙያ ስልጠና ስላልተሰጠኝ፣ አእምሮዬ ከልጅነቴ ጀምሮ በመዞርና በጀብዱ በመስራት ሀሳብ ተሞልቶ ነበር። አባቴም በጣም ዕድሜው የገፋ ሰው ስለነበር፣ ጥሩ ትምህርት ሰጥቶኝ ነበር።የተማረ ሰው ለመሆን የሚያስፈልገውን መጠነኛ ትምህርት በቤት እና በገጠር ነፃ ትምህርት ቤት አግኝቼ ነበር፤ አባቴም የሕግ ሙያ እንድከተል አቅዶልኝ ነበር። ነገር ግን እኔ በባሕር መጓዝ ካልሆነ ሌላ ነገር አየስደስተኝም። ይህ ፍላጎቴ እጅግ በጣም ጠንካራ ስለነበር የአባቴን ፈቃድና ትእዛዝ፣ እንዲሁም የእናቴንና የሌሎች ወዳጆቼን ምክርና ልመና ሁሉ ተቃወምኩ። ይህ የተፈጥሮ ዝንባሌ በኋላ የሚደርስብኝን የመከራ ሕይወት በቀጥታ የሚያመራና እንደ እጣ ፈንታ የሆነ ነገር ይመስል ነበር።አባቴ ጥበበኛና የተከበር ሰው ስለ ነበር፤ እኔ ልፈጽመው ያሰብኩትን ነገር አስቀድሞ ተረድቶ በጣም ጥሩና ጠቃሚ ምክር ሰጠኝ። አንድ ቀን ጠዋት ወደ እርሱ ክፍል ጠራኝ፣ ስለ ሀሳቤና አላማይ ጉዳይም በታላቅ ትህትና አነጋገረኝ።“ከማይረጋ የመንከራተት ፍላጎት በስተቀር የአባትህን ቤትና