ARDALE FACE OF HARARI

Call Directions Website Contact the establishment

ARDALE FACE OF HARARI This page Harari ethnic culture, the beauty of the dress wedding dress costumes and special notice t

Best Song Collection 👉 Adiyay Entertainment Subscribe
15/08/2026

Best Song Collection 👉 Adiyay Entertainment Subscribe

🎵 Welcome to ADiYAY ENTERTAINMENT! 🎵📍 From Harar, Ethiopia | 📞 +25...

Best Harari Song By Wisam Ehsan ❤❤❤❤❤❤❤
10/07/2026

Best Harari Song By Wisam Ehsan ❤❤❤❤❤❤❤

AYSA is a timeless Harari classic, beautifully reimagined by Wisam ...

 !!!መቼም ሀረር የኢትዮጵያ አንድ አካል መሆኗን አትጠራጠሩም!! ቢሆንም "ሀረር" በአንድ ወቅት የአርሜኒያ ግዛት ብሗላም በሶቪየት ዘመን በአዘርባጃን ሶቪየት ሶሻሊስት ሪፐብሊክ ግዛት ሆና ...
06/05/2026

!!!

መቼም ሀረር የኢትዮጵያ አንድ አካል መሆኗን አትጠራጠሩም!! ቢሆንም "ሀረር" በአንድ ወቅት የአርሜኒያ ግዛት ብሗላም በሶቪየት ዘመን በአዘርባጃን ሶቪየት ሶሻሊስት ሪፐብሊክ ግዛት ሆና የቆየች ቢሆንም ቀጥላ የአርጻክ ሪፐብሊክ (Republic of Artsakh) የነበረች ከዛም ከ2020ው ጦርነት ብሗላ በአዘርባጃን ሶቪየት ሶሻሊስት ሪፐብሊክ ግዛት ሆነች። ቁልጭ የኛን ሀረርን!!!!
በአሁኑ በአዘርባጃን ደቡብ ምዕራብ ክፍል ከላቺን ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው ተራራማና የሀረር ወንዝ ዳርቻ አካባቢ
የምትገኘው ታሪካዊቷ የአዘርባጃኗ ሐረር ከእኛዋ "ሀረር" ጋር በቆዳ ስፋቷ የምትወዳደር ከ2,000 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረች ጥንታዊ ከተማ ነች። ይችህ ከተማ በጥንቱ ዘመን ቤርዳዞር ተብሎ በሚጠራው ሰፊ አውራጃ ውስጥ እንደ አንድ ቁልፍ ማዕከል ሆና ስታገለግል መቆየቷ በታሪክ ሰነዶች ውስጥ በስፋት ተመዝግቧል።
የሐረር ከተማ ምስረታ እና እድገት ከጂኦግራፊያዊ አቀማመጧ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው። ከተማዋ በታላላቅ የንግድ መስመሮች መገናኛ ላይ መገኘቷ ከተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚመጡ የንግድ ተጓዦች ካራቫንቶች (ካራቫንሳራዎች) የሚያርፉባት እና የሚገበያዩባት ስፍራ እንድትሆን አስችሏታል። በዚህም ምክንያት በከተማዋ ውስጥ በርካታ የንግድ ማረፊያዎች ተገንብተው ነበር። ይህም ከተማዋ በኢኮኖሚ እንድትጠነክር እና የሕዝብ ቁጥሯም እንዲጨምር ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጎላት ነበር። በጥንታዊ የአርሜኒያ ስልጣኔ ወቅት ከተማዋ የኪነ ህንፃ ጥበብ በከፍተኛ ሁኔታ የሚታይባት ስፍራ ነበረች። በተለይም በድንጋይ ላይ የሚቀረጹ ቅርሶች እና የአብያተ ክርስቲያናት ግንባታ የመንደሯን የጥበብ ደረጃ የሚያሳዩ አሻራዎች ሆነው እስከ ዛሬ ድረስ ዘልቀዋል።
በመካከለኛው ዘመን የሐረር ከተማ ከፍተኛ የብልጽግና ደረጃ ላይ ደርሳ ነበር። በወቅቱ በነበሩ የንግድ እንቅስቃሴዎች አማካኝነት የከተማዋ ነዋሪዎች ከውጭው ዓለም ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበራቸው። ይህም በባህል እና በቴክኖሎጂ ልውውጥ ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በከተማዋ ዙሪያ የሚገኙት ለም መሬቶች ለግብርና ስራ ምቹ በመሆናቸው ነዋሪዎቿ በሰብል ምርት እና በእንስሳት እርባታም የታወቁ ነበሩ። ከግብርናው ጎን ለጎንም የተለያዩ የእጅ ጥበብ ስራዎች በተለይም የሸክላ ስራ እና የጨርቃጨርቅ ምርት በከተማዋ ውስጥ እጅግ የዳበሩ ነበሩ። ይህ የታሪክ ሂደት ከተማዋን በአካባቢው ካሉ ሰፈራዎች ሁሉ ጎልታ እንድትታይ አድርጓታል።
ይሁን እንጂ የሐረር ታሪክ በብልጽግና ብቻ የተሞላ አልነበረም። በታሪክ ሂደት ውስጥ በተለያዩ ወቅቶች የተነሱ ጦርነቶች እና የፖለቲካ ግጭቶች በመንደሯ ላይ ከባድ ጉዳት አድርሰዋል። በተለይም በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ እና በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በነበሩት ውጥረቶች ምክንያት የከተማዋ ነዋሪዎች ከፍተኛ መፈናቀል እና ስቃይ ደርሶባቸዋል። በ1897 ዓ.ም. በተደረገ ቆጠራ መሰረት ሐርር ከ500 በላይ ነዋሪዎች የነበሯት ሲሆን ሁሉም ብሄረሰባቸው አርሜኒያዊ እንደነበረ መረጃዎች ያሳያሉ። ነገር ግን ከ1918 እስከ 1921 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ በተከሰቱ ግጭቶች የሕዝቡ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ አሽቆልቁሏል። ከተማዋም የከተማነት ገፅታዋ ቀርቶ በአርሜኒያ ስር ስትገባ ወደ መንደር አንድ ግዛትነት ተለውጣለች። ይህም በከተማዋ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መዋቅር ላይ ትልቅ ጠባሳ ጥሎ አልፏል።
በሶቪየት ህብረት ዘመን የሐረር "መንደር" የስያሜ ለውጥ አስተናግዳለች። በወቅቱ በነበረው የፖለቲካ ጫና ምክንያት መንደሯ "ጃፋራባግ" ተብላ እንድትጠራ ተደርጎ ነበር። በኋላም በ1953 ዓ.ም. "አሻጊ ፋራጃን" የሚል ሌላ ስያሜ ተሰጥቷታል። እነዚህ የስም ለውጦች የመንደሯን ጥንታዊ ማንነት ለመቀየር የተደረጉ ሙከራዎች አካል ቢሆኑም ነዋሪዎቿ እና ታሪክ ጸሐፊዎች ግን ሁልጊዜም በሐረር ስሟ ሲጠሯት ቆይተዋል። ይህ የ"መንደሯ" ስም ከነዋሪዎቿ ማንነት እና ከታሪካዊ ስሯ ጋር በጥብቅ የተቆራኘ በመሆኑ በቀላሉ ሊረሳ አልቻለም።
ከ1994 ዓ.ም. ወዲህ በአካባቢው የተከሰቱት ለውጦች ለ"መንደሯ" አዲስ ምዕራፍ ከፍተዋል። የአርጻክ ሪፐብሊክ ታሪካዊ ቦታዎቹን መልሶ ለማደራጀት በወሰደው እርምጃ መንደሯ የቀድሞ ታሪካዊ ስሟን መልሳ እንድትጠቀም ተደርጓል። ይህም የመንደሯን ታሪካዊ እና ባህላዊ እሴቶች መልሶ ለማግኘት የተደረገ ትልቅ እርምጃ ነው። በአሁኑ ወቅት ሐረር የጥንታዊ ሥልጣኔ አሻራዎችን የያዘች የታሪክ ማሳያ ትመስላለች። በ"መንደሯ" ውስጥ የሚገኙት አሮጌ አብያተ ክርስቲያናት እና ጥንታዊ መካነ መቃብሮች የዘመናትን ታሪክ በዝምታ የሚተርኩ ምስክሮች ናቸው።ይህም አሁን ላይ ለቱሪስት ፍሰት ምክንያት ሆኖላታል። ነዋሪዎቿም አሁንም ድረስ የቀድሞ አባቶቻቸውን የግብርና እና የጥበብ ስራዎች በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።
- እና እቺህ ሐረር የከኛዋ ሀረር ጋር መንታ አይደለችም ትላላቹ?!😊 አሁን ለከተማችን እህት አግኝተናልና የአዘርባጃን መንግስትን ለማናገር እንዘጋጅ።😊
👉 ሻጊዝ አዶናይ🙏

 !!  #ለምን?!🤔የሀረር ከተማ ቶፖግራፊ (topography) ስንመለከት ዙሪያዋ በተራሮች የተከበበች ነች። ይህም የሀረር ቶፖግራፊ በሦስት ከፍተኛ ተራራማ አካባቢዎች ልንመለከተው እንችላለን...
29/04/2026

!! #ለምን?!🤔
የሀረር ከተማ ቶፖግራፊ (topography) ስንመለከት ዙሪያዋ በተራሮች የተከበበች ነች። ይህም የሀረር ቶፖግራፊ በሦስት ከፍተኛ ተራራማ አካባቢዎች ልንመለከተው እንችላለን።
• ​የጨርጨር ተራራዎች
• ​የጉርሱም (ሻዳ ዋ ማዳ) ተራራዎች
• ​የሐረር ተራራዎች ናቸው።
ወደ ውስጥ ስንገባ ከተማዋ በተለይ ጀጎል በአስራ ሐንድ ጥልፍልፍ ተራሮች እና ኮረብታዎች ተከባለች። ጀጎልም ራሷ በኮረብታ ላይ የምትገኝ ነች። ይህ አጋጣሚ ሳይሆን ለሰው ሰራሽ እና ለተፈጥሮ አደጋ (እንደ እሳት፣ጎርፍ እና ጠላት እንዳትጠቃ) ሆን ተብሎ የተመረጠ አከባቢ ነው። እንደ የአው በርካድሌ ኮረብታ ፣ አፌይዛሮ ፣ ጂኔላ ፣አቡከር ፣​ጋራ ጀቤ ፣ ደከር ፣ሐኪም ጋራ በመሳሰሉት ተራራ እና ኮረብታዎች ጀጎል ታጅባለች። ታዲያ ከነዚህ ውስጥ የሑሉም አይን፣የሑሉም ካሜራ አቅጣጫውን ወደ ሐኪም ጋራ ካረገ ሰነባብቶዋል።
ዛሬ በከተማችን በየትኛውም አቅጣጫ ጎልቶ ከፍ ብሎ የሚታየው "Harar" የሚለው ፅሑፍ የከተማዋን ገፅታ ላይ ግርማሞገስ ጨምሮ እያየነው እንገኛለን።
ማውንቴን ሞኖግራፍስ (Mountain monographs) ወይም ሒልሳይድ ሌተርስ (Hillside letters) በመባል ይታወቃል። በሰለጠኑት አገራት በከተሞች ከፍታዎች ላይ ማኖሩ የተለመደ ነው። ይህ እንደ ብራንድ (ልዩ አርማ) ሆኖ ከማገልገሉ ባሻገር ትልቁ የቱሪዝም ማስታወቂያ በመሆን ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ነው።
"አው ሐኪም ሰሪ" ወይም "አው ሐኪም ጋራ" እየተባለ የሚጠራው የጀጎል አጎራባች የደቡቡ ጋሻ ዛሬ ቀን ወቶለት ለልማት ተመርጠዋል። ይህ ማውንቴን ሞኖግራፍ የአይናችንን ትኩረት ይውሰደው እንጂ በቀጣዩ የጀጎል ሰገነት ሆኖ ማየት ሳይሆን የምንሔድበት ለሐይኪንግ ምንመርጠው የምንዝናናበት ልዩ ስፍራ ሊሆን ጥቂት ግዜያት ነው የቀሩት።
እናስታውስ ከሆነ የዛሬ ስድስት አመት የእንጦጦን ተሞክሮ መሰረት ተደርጎ በሐኪም ጋራ እና በሴላት ፓርክ ተተመሳሳይ ፕሮጀክቶች እንደሚሰራ ተነግሮ ነበር። አሁን ወደተግባር ተገብቷል!!!

" ?" ?

#አንድ ☝️ - መልስ አለው!!

አው ሐኪም ሰሪ ለሀረር ልዩ ትርጉም አለው። ሐኪም ጋራ ከተፈጥሮ የስነ-ምህዳር (ecosystems) አንዱ ነው። ሀረርን ከመሰረቷት የቀድሞ መንደሮች ውስጥ አንዱ "ሐረዌጌይ" ነው። ይህ መንደር በግዜው የጠላት መከላከያው የቅኝት ማማው የነበረው ይህው አው ሐኪም ጋራ ነው። ስለዚህ አው ሐኪም ጋራ ላይ መጀመሩ አንዱን የቀድሞ የሀረር መንደር ዳግም እንዲያንሰራራ ለታሪክም ለቱሪዝምም መሰረት የሚጥል ይሆናል።

#ሑለት ✌️ - ታሪክ አስታዋሽ
የጀጎል ግንብ ካሉት በሮች መሐከል በስተ ደቡብ የሚገኘው በር "በድሪ በሪ" ሌላየኛው የአርበኛ መጠሪያው "ባቡል ሐኪም" ነው። ይህ ከአው ሐኪም ጋራ ትይዩ የሚገኝ እና ከበሩ ጋር ተዛማጅ የሆነ አገልግሎት የሚሰጥ ነበር። ባህላዊ መድሐኒቶች፣ህክምና፣ሐይማኖታዊ ትሪትመንት ይሰጥባቸው የነበሩ በመሆኑ "የሐኪሞች ተራራ" (Mountain of Doctors/Healers) ተብሎም ይጠራል። ይህ ስም የመጣው ከተራራው ግርጌ በሚገኙ ዋሻዎች ውስጥ ይኖሩ ከነበሩ 70 የሚደርሱ የሃይማኖት አባቶች ወይም "ሸይኾች" እንደሆነ ይታመናል። በዚህም ምክንያት "ሐኪም" የሚለውን ስያሜ አግኝቶዋል።

አው ሐኪም ጋራ በሀረር ከተማ በስተ ደቡብ የሚገኝ ሲሆን ከፍታውም ከባሕር ጠለል በላይ 2200 ሜትር ይደርሳል።ይህም ተራራው የሀረርን ከተማ ቁልቁል ለማየት የሚያስችል ስልታዊ ቦታ ላይ እንዲገኝ አርጎታል። ከተራራው ጀርባ ያለውን የኤረር ሸለቆን (Erer Valley) በግልጽ ለመመልከት ያስችላል። አለፍ ሲልም ከከፍታ ላይ ሀረርን በተለይ ጀጎልን ለማየት የተሻለ Panoramic view አቅጣጫ እና ከፍታ የሚገኘው በዚሑ ሐኪም ተራራ ላይ ነው።

👉 ?

ሐኪም ጋራ የሀረሪ ባህላዊ ቤቶችን ለመስራት ግብአት የሚገኝበት በመሆኑ ለረጅም ግዜ ሲገለገሉበት ኖረዋል።
ይህ ጋራ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ ሐብቶች እና የቱሪዝም መስህብ ያለው ለዘመናት የተዘነጋ የሀረር ሐብት ነው።
የተፈጥሮ የስነ-ምህዳር (ecosystems) አንዱ ከመሆኑ ባለፈ ተራራው በከፍተኛ ደረጃ የኖራ ድንጋይ (Limestone) እና ግራናይት (granite) በስፋት የሚገኝበት ነው። በቀድሞ ሀረር ታሪክ ለዘመናት ሳይቋረጥ የሚፈስ ውሃ የሚገኝበት ከአው ሐኪም ተራራ የሚመነጭ ውሃ ውስጥ ለውስጥ የሚፈስና የማይደርቅ የውሃ ምንጭ አለው። ይህም ለሀረር ከተማ የውሃ አቅርቦት መሠረት እንደነበርና "ሐጂ ቦምባ" በተባሉ ግለሰብ ቧንቧ እንደተዘረጋለት ታሪክ ያስረዳል። በዚህም ምክንያት "ሚይ ጉፋት" የውሃ ማማ" (water tower) ተደርጎ ይወሰዳል።
ሐኪም ጋራ በ1970ዎቹ አረንጓዴ ስፍራ በዛፍ የተሸፈነ የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ሰው ሰራሽ ምክንያቶች የውሃ ምንጩ የቀነሰ እና የደከመ ነበር። ብሗላም ከ2013 እስከ 2017 ለአራት አመታት በተከናወነ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ የአካባቢው ሥነ ምህዳር ተመልሶ ምንጩ ዳግም ጨምሮዋል።
ይህ አው ሐኪም ተራራ ተፈጥሮ የለገሰችው ሐብቱ ሲሆኑ ሰው ሰራሾቹን የቱሪዝም መስህቦች ስንመለከት በተራራው አናት ላይ የምናገኘው እና በይዘት እና በምህንድስናው ቀዳሚው የአው አብዱልቃዲር አል ጀይላኒ መስጂድ ነው። ይህ ታሪካዊ መስጂድ አሁንም እያገለገለ ይገኛል። በተጨማሪም በአው ሐኪም ጋራ እና በአቅራቢያው
በስተምእራብ አው በርኸሌ አዋች በአው ሐኪም አቅራቢያ የሚገኝ ሲሆን የአው በርኻድሌ መካነ መቃብር (shrine) በስፍራው ይገኛሉ። አውሶፊ ያህያ፣አው ሰኢድ አሊ አዋችም በሐኪም ጋራ አቅራቢያ ይገኛሉ። እነዚህና ሌሎች በርካታ የስልጣኔ መነሻ እና ቅርሶች ለቱሪዝም መዳረሻነት እንዲሑም ለተለያዩ ጥናቶች በር የሚከፍት ነው።
ይህን አው ሐኪም ጋራ መመረጥ ቀዳሚ መደረጉ በቂ ምክንያት እንዳለው የምንረዳበት ነው።
👉 የማቃትን አካፍያለው፤እናንተም ጨምሩበት....
👉

10/04/2026

 አብዱልዋሲ አቡበከር ሀረር አሲማቤ በድሮበሪ በሪ አው ፈዘል ቶያቤ ኣውዞ ሓጂ አቡበከር አብራሂም ኢስማኢል ዋ ኣይዞ ጊስቲ ከዲጃ ኢምራን ሙሑመድቤ ተወለዳ፤ አዪ ሀረሪ ወልዲ ዪሊቅባዛል ኩትቤ...
08/04/2026


አብዱልዋሲ አቡበከር ሀረር አሲማቤ በድሮበሪ በሪ አው ፈዘል ቶያቤ ኣውዞ ሓጂ አቡበከር አብራሂም ኢስማኢል ዋ ኣይዞ ጊስቲ ከዲጃ ኢምራን ሙሑመድቤ ተወለዳ፤ አዪ ሀረሪ ወልዲ ዪሊቅባዛል ኩትቤ ቁራንጌይ ዪለምዲዛል፤ አሺር ጋር ዩሑርዛል፤ ቶያቤ ቆባችዞበሕ ሌቃ፡ አዞኩትዞም፤ ጌይ መድረሳቤ፤ ቀኃስቤ ለመዳ የእቤሔሩም መድኃኔዐለም መድረሳቤ ኢላ 12ታኝ ፈስሊዞው ሔለዳ፡፡
ዲላገዞም መንግስቲ ጋርቤ ደላጊዋ ዳይ ሐዋዚያ ሓጃ ቢሮቤ(ሠራተኛና መህበራዊ ጉዳይ ቢሮ) ተጌበላማ ኢላዋ ሐያትዞ ሒያ አዱኚትቤ ቲትላዪቄሲ ዪ ቢሮቤዞ ደላጊዋ ዳይሐዋዚያ ሑክሚ ጋር ሐካምነትቤ ዪደልጊንናር፡፡
ሲያሳ ሐያትዞው ዚሔጅነሳ፤ ዪሺርቲ ዚቃነናሳም አላይ አዜባችበሕ መኽናቤ ጪንጨሕዞው ኣሻ፤ ዪቤም ኢላ ሊግ ዚጉትቲ ሐቢዶኝ አግቡር መኽናቤ ዪደልጊንናር፡፡ አሐድጊር 1990ችቤ ሊግ አሶሰምዞቤ ዚትኸለቃ ሺኢው መቄቀልዞ ደረር ኤላም ፡፡ ሶሰምዞ ዚቀረቡ ዚጉትቲ ሐቢዶኝ ሒንጫያችቤ ሙቃወማ አይኒበርማም አላይ ሊግ አግቡር ዘልታ ኡሱእ ዪትመለሕኩት ሐፍዛያ አታበርቤ ሊግዞ ዘቀረቤያችቤ አሐድ ኡሱእ መውጠእ ናረቤው የእሳ አብዱልዋሲኡ ዩጡቅሶማ አዞም ቦሪነትቤ ዪትቄበለዩማ፤ ያእ አባ አብዱልዋሰእ ሱራዞቤ ዪትመለሕኩት ዩኹናል፤ የኽኒማም ሊግ ኤቀድ ዚናራች ጊሽታኝዞ የእ አበባሕ ረብሻ ኸለቁማ አባም ሪዛይን ዛሻሳ፤ አብዱልዋሲኡም ሐጂስቤ ሐቢዶኝዞቤ ጊረገባ፡፡ አጃኢቡም አልታ ዪ አሳስቤ ሚሬኛች ተራኡማ ዘሳነኑሳ፤ አብዱልዋሲእ ኡኩ ዪሊማ ዪምደሓል ሚልሓ ሚሬኛዞሌ፤ ሊግ መላ ዘሌላ ሙነዘማን፤ ሚስቲ አመት ዛሾ መሳመታች/ዲብላናች ዲብላን ቀውሊዞ አንደቤሐል/ ዲብላን ቀውሊ ለሓዳዚዩን ናርማ/ ኢላሆጂም አሐድ ኡሱኡም አለትሔበሬኙም ባያ፤ አብዱልዋሲእ ታሪኹ ዚለሐዴውኩትቤ ኣኺራ ገበኣ፡፡ሊግሌም ሙትዞሌም አልታዋ አልመትቀበርዞቤ ከፍ ዪለነዛል አልላሁ መርሒም ባይቲ የትኺሻሜሊ
ጌሲ አብዱለዋሲኡ ታሪኽዞው ኡፍ ነከእኩትቤም ኢጪሕሪኩት ዛሼኝ ሑኩማ ጋር ዲላጋዞቤ ሑሉፍ ዚናሬው እጂ ሲነትዞንታ፤ ኣውዞ አሐድ ሒርፈት አትሌመዶማ ሜሻ ያሺማ ሐያትዞው ዪቺኽሊባኩቲንታ፡፡
ዪዞም ቀብሪ ኡን መቤረቅዋ መክተብንታ፡፡ አውዞ መጬሐረዞው ኪልከታቡ አዞ ኡንዞው መሔከልቤ አረቢቤ ዚጬሐሩሎው መንቀሽንናር፤ አላያቹም ዪው ዪደልጉዛላች የንበሩማም አብዱልዋሲኡ ሉይ የሻዛል አረቢዞዉም ዪከትቢማ መንቀሽዞንታ፡፡ አዪ ሐረሪም ሑኩማ ደላጊ መኽና ሙጢም አልታዋ አላይ ሲነትኾቤም ኪልደለግኹ ሩሕኾው መኔራ ፊዝቤ አትኼሽንታ፤ አብዱልዋሲእቤ ዪው ኒለምዳና፤ አዜቦው ሊመድባ
አብዱልዋሲእ ጋሩም ኣሻማ አትሌመዴዩማ አታይ አቦረዳ፤ ከኦት ቀሐታቹም ዞለዳሳ አሐድዜቤ አብሱማም ሪኣ፡፡ አዞ ሆጂ 66 ኡምሪዞቤ ሒያ አዱኚትቤ ተላዬና አልላሁ ሱት ጀነትዞው የዋፍቃ፤ ሳቲ አዛብዞቤ በሪእ ዩሻ ወልዳች፤ አሕላችዋ መሪኛችዞ ጀሚእሌም አልላሁ ሰብሪዋ ኢማን የስጠዩ ኪላና ገልጌብዚኛው ዪቤ ኑጉልባሐና፡፡
Credit - ካቲብ አባ አዩብ አብዱላሒ ፈቂ

Address

Harar
3200

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ARDALE FACE OF HARARI posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to ARDALE FACE OF HARARI:

Shortcuts

Share