Sol ma bo

Sol ma bo ሰዋሰው

29/05/2022

አይዞን ወገኔ
ዛሬ ያስጨነቀን መፈናፈኛ ያሳጣን ነገ የእርሱ ተራ ነው፡፡

memory
22/05/2022

memory

10/05/2022

ፈጥነህ ሰውን አትመን "ጨው" በራሱ መጀመሪያ ሰታየው "ስኳር" ይመስላል!

መቸም አንረሳቹህም  በያላቹህበት ሰላም ሁኑልን መልካም የፋሲካ በአል ይሁንላቹህ እንኳን አደረሳቹህ!!!
23/04/2022

መቸም አንረሳቹህም በያላቹህበት ሰላም ሁኑልን መልካም የፋሲካ በአል ይሁንላቹህ እንኳን አደረሳቹህ!!!

22/04/2022
21/04/2022

ፈታ በሉበት

 #አሀዱሰላም ሰላም የተወደዳቹህና የተከበራችሁ የምታምሩ ኢትዮጵያን የአሀዱ የስነ-ፅሑፍ ምሽት ቤተሰብ እንዴት ናቹህ♥ያው ሁላችንም እንደምናውቀው አሀዱ የስነ-ፅሑፍ ምሽት ያለፈው እሁድ በ11...
25/12/2020

#አሀዱ

ሰላም ሰላም የተወደዳቹህና የተከበራችሁ የምታምሩ ኢትዮጵያን የአሀዱ የስነ-ፅሑፍ ምሽት ቤተሰብ እንዴት ናቹህ♥
ያው ሁላችንም እንደምናውቀው አሀዱ የስነ-ፅሑፍ ምሽት ያለፈው እሁድ በ11/04/2013 ነበር ለህዝብ ኘሮግራሙን እሚያቀርበው ሆኖም በተለያዩ ችግሮች ከወረዳው ባህልና ቱሪዝም ጋር በተፈጠረው አለመስማማት ተፈጥሮ አዳራሽ ተከልክለን ኘሮግራሞችን ለህዝብ አላቀረብንም ነበር፡፡
ሆኖም 13/04/2013 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ስአት በወጣት ማህከል በኖርዌ አዳራሽ ውስጥ ኢትዬጵያዊነት የተሰኝው የጥበብ ማዕዳችን ተካሂድዋል፡፡ በስነፅሑፍ ምሽታችን ውስጥ
አነቃቂ ንግግር ..........ግጥም...........ወግ

ሀገርን እሚሰራ ሀገርን እሚታደግ ሀገርን እሚያበጃጅ ሀገርን እሚገነባ ትልቁ ግንበኛ እኛው ነን፡፡ ኢትዮጵያ ብለን እምንላትም የምትገነባ የምትሰራ ህንፃ ወይም አስፖልት አይደለችም፡፡ ኢትዬጵያ ሰው ናት ማሰብ እሚችል ሰው፡፡ ኢትዬጵያን እኛ አልገነባናትም እኛ አናፈርሳትም፡፡ ኢትዬጵያ ስትገነባ የኖረችው በእግዛብሄር ዐዕምሮ ውስጥ ነው፡፡ኢትዬጵያን እኛ አልገነባናትም እኛ አናፈርሳትም ስለዚህ አትፍሩ፡፡

የሚሉ ንግግሮች እና የተለያዮ ኘሮግራሞች ቀርበው ነበር፡፡
ፈጣሪ ኢትዬጵያንና ልጆችዋን ይባርክ!!!✍✍

https://telegram.me/ahdeuyesenetsuhufmesh*t

ab music:ቀሳፊ ምርቃት/በ አሌክስ አብርሃም /ሰማሁ ምርቃትሽን ….ከእናት አንጀትሽ ቁልቁል ሲዥጎደጎድታየኝ ምድረ መልዓክ …ብራና ዘርግቶ ቃልሽን ሊከትብ ትከሻሽ ላይ ሲያረግድበረካሁንልኝ...
21/12/2020

ab music:
ቀሳፊ ምርቃት

/በ አሌክስ አብርሃም /

ሰማሁ ምርቃትሽን ….
ከእናት አንጀትሽ ቁልቁል ሲዥጎደጎድ
ታየኝ ምድረ መልዓክ …
ብራና ዘርግቶ ቃልሽን ሊከትብ ትከሻሽ ላይ ሲያረግድ
በረካሁንልኝ …ከፍ ያርግህ በሰው ፊት …
እድሜ ጥምቡን ይጣል ይቅና ማቱሳላ
እርጅና እጁ ይዛል አካላትህ ይስላ

ዝም !

እግርህን እንቅፋት ጎንህን ጋሬጣ
ጤናህን ድቅስቃስ የመንደር ሽውታ
አይንካብኝ ብለሽ የመረቅሽኝ ለታ

ዝም !

ዘርህ ዋርካ ይሁን ወንዝ ዳር ያበበ
ታሪክህ ዘላለም ባደባባይ ይድመቅ እየተነበበ
ደሆች ፊትክን አይተው በጥጋብ ይኑሩ
ልጆጅህ በስምህ ለዘላለም ይኩሩ
ብለሽ ስትመርቂኝ

ዝም !

ካ,ይንሽ የፍቅር እንባ ፊቴ እየረገፈ
ለእልፍ ምርቃትሽ እንቢ አለኝ ልሳኔ ‹‹አሚንታን ›› ነጠፈ
ዝምታየ አይክፋሽ ክፉ ፍራቴ ነው ልሳኔን የዘጋው
በምርቃትሽ ውስጥ የምርቃት መቅሰፍት ውስጤን እየወጋው
በክፉ የሚያይህን ጨለማ ያልብሰው
ክፉ ተራማጁን እግሩን ያልመስምሰው
ብለሽ አሚን ያልኩት ምርቃትሽ ያዘ
በክፉ የሚያየኝ አይኑ ታወረና
በጭፍን ሊፈጀኝ ጎራዴ መዘዘ
የህሊና እግሮቹ የሰለሉ ጠላት
ብረት ተመርኩዞ መንገዴ ላይ ቆመ
አሚን ካለሽ አፌ ‹‹እግዚኦታ›› ተመመ !

ግዴለሽም እማ …

ጠላቴ አይኑ ይብራ ይግደለኝ እያየ
ባቡሰጥ ብትሩ እኔን እየሳተ ወገን አሰቃየ
ጥላቴ እግሩ ይስላ ይቅደመኝ ከሮጠ
በለመሹ እግሮቹ መንገድ እየዘጋ
ከዘመን ሩጫ ትውልድ ተቋረጠ !

ግዴለሽም እማ …..

ጥላቴን መርቂው አይኑ ፀሃይ ይሁን ቦግ ብሎ ይብራ
ምናልባት ምናልባት እውነቱን ቢያሳየኝ
ወይ እውነቴን አይቶ ለልጅሽ ቢራራ ጥላቴ ዓይኑ ይብራ …
ያኔ ትሰሚያለሽ ድል ካረገ ልሳን የሃቅን ፉከራ !

እንጅ ባንድ ምድር ልጅ እየመረቁ ‹‹ጠላትን›› ቢገፉ
ርግማን ያወረው በደፈናው ጠላት ለልጅሽ ነው ደፉ !
አሚን?

https://telegram.me/ahdeuyesenetsuhufmesh*t

አሁን ደግሞ አጭር አነቃቂ ፁሁፍ እንጋብዛቹሁ

#ከአሀዱ

📝 `:... ተማሪ እያለህ ትምህርት ጨርሺ ስመረቅ ደስተኛ ሆናለሁ አልክ

ከዛም ተመረቅክ

ስትመረቅ ደግሞ ስራ ስይዝ ደስተኛ ሆናለሁ አልክ

ስራም ያዝክ

ስራተኛም እያለህ ሳገባ ደስተኛ ሆናለሁ አልክ

ባለትዳርም ሆንክ

ባለትዳር ስትሆን ልጅ ስወልድ ደስተኛ ሆናለሁ አልክ

የልጅ አባትም ሆንክ

የልጅ አባት ሆነህ የልጅ ልጅ ሳይ ደስተኛ ሆናለሁ አልክ

አያትም ሆንክ

አያትም ስትሆን በቃ ከሞት በኃላ ደስተኛ ሆናለሁ አልክ
........

ደስታ ነገ የምትታቀድ , ሳትሆን
ዛሬ የምትኖር መሆንዋን ሳናውቅ
ስንቱቻችን ደስታን እየጠበቅን
በደስታ ቢስ ህይወት ኖርን

ደስታ እኮ የሌለንን ነገር በመፈለግ ሳይሆን ባለ ነገር በመብቃቃት የምትመነጭ ልዩ ስሜት ናት

ደስታ ነገ የምትገኝ ሳትሆን

ዛሬ !

አሁን የምትኖር ናት::

https://telegram.me/ahdeuyesenetsuhufmesh*t

https://telegram.me/ahdeuyesenetsuhufmesh*t

https://telegram.me/ahdeuyesenetsuhufmesh*t

You can view and join right away.

Address

Gondar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sol ma bo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share