Askual Promotion & Advertisement

Askual Promotion & Advertisement Askual Promotion And Advertising
Dire Dawa | Ethiopia

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉእንኳን ለኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ።Girma Moges
28/06/2023

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ
እንኳን ለኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
Girma Moges

"ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን፤ ትንሳሄውን በሚመስል ትንሳሄ ከእርሱም ጋር እንተባበራለን" ሮሜ 6፥5እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም ...
16/04/2023

"ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን፤ ትንሳሄውን በሚመስል ትንሳሄ ከእርሱም ጋር እንተባበራለን" ሮሜ 6፥5
እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
አስኳል ፕሮሞችንና አድቨርታይዚንግ
"አምሳለ"
በቅርብ ቀን
Girma Moges
#2015

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዩች እንኳን ለታላቁ የረመዳን ፆም በሰላም አደረሳችሁ:: መልካም የጾምና የፀሎት ወር እንዲሆንላችሁ  #አስኳል ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል!
22/03/2023

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዩች
እንኳን ለታላቁ የረመዳን ፆም በሰላም አደረሳችሁ::
መልካም የጾምና የፀሎት ወር እንዲሆንላችሁ #አስኳል ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል!


ዝግጁ ናችሁ...የድምጻዊት አስቴር አወቀ “ሶባ” አዲስ አልበም የጥምቀት ዋዜማ ይወጣል !ከመድረክ አያያዟ እና ከውብ አዘፋፈኗ በተጨማሪ በራሷ ተወዳጅ ግጥምና ዜማዎቿ የምትታወቀው ተወዳጇ ድም...
04/01/2023

ዝግጁ ናችሁ...
የድምጻዊት አስቴር አወቀ “ሶባ” አዲስ አልበም የጥምቀት ዋዜማ ይወጣል !

ከመድረክ አያያዟ እና ከውብ አዘፋፈኗ በተጨማሪ በራሷ ተወዳጅ ግጥምና ዜማዎቿ የምትታወቀው ተወዳጇ ድምጻዊት አስቴር አወቀ “ሶባ” የተሰኘ አዲስ አልበም የጥምቀት ዋዜማ እንደሚወጣ ሰዋሰው መልቲሚድያ አስታውቋል፡፡
በያዝነው አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ ለሕዝብ የተዋወቀው እና ከመቶ በላይ አንጋፋና ወጣት ተወዳጅ ድምጻዊያንን በጋራ ለመስራት ያስፈረመው ሰዋሰው መልቲ ሚድያ ፤ አስር የሙዚቃ ስራዎችን ያካተተው የድምጻዊቷ “ሶባ” የተሰኘ አዲስ አልበምን የጥምቀት ዋዜማ በሰዋሰው መተግበሪያ በኩል ለአድማጮች ያደርሳል ተብሏል፡፡
ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ/ም ድምጻዊ አስቴር አወቀ ከሰዋሰው መልቲ ሚድያ ጋር ስተፈራረም የሰዋሰው የማኔጅመንት አባላት ድምጻዊ አስቴር አወቀ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ድምጻዊት አስቴር አወቀ ከዚህ በፊት ሃያ አራት የሚደርሱ ዘመን አይሽሬ ተወዳጅ የሙዚቃ አልበሞችን እና ሁለት ነጠላ ዘፈኖችን ለሙዚቃ አፍቃሪያን ያደረሰች ሲሆን “ሶባ” ሃያ አምስተኛ አልበሟ ነው፡፡ ድምጻዊቷ ከሃገር ውስጥም በተጨማሪ በታላላቅ ዓለማቀፍ መድረኮች ስራዎቿን በማቅረብ ከፍተኛ አድናቆትን በማግኘት ኢትዮጵያዊቷ የፖብ ሙዚቃ ንግስት በመባልም ትታወቃለች፡፡
ሰዋሰው መልቲ ሚድያ ጥበበኞች የሚገባቸውን የፈጠራ ዋጋ እንዲያገኙ በማድረግ የሃገራችን ጥበብ ባህር ማዶ ተሸጋሪ እንዲሁን ለማስቻል ከ50 ሚሌዬን ብር በላይ ኢንቨስትመንት የተቋቋመ ሀገር በቀል ድርጅት ነው፡፡

ምንጭ: ሰዋሰው መልቲ ሚድያ
ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ

የአምባሰሏ ንግስት የክብር ዶክተር አንጋፋዋ አርቲስት የማሪቱ ለገሠ የክብር አቀባበል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በፎቶ ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ/ምምንጭ: የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የፌስቡ...
02/01/2023

የአምባሰሏ ንግስት የክብር ዶክተር አንጋፋዋ አርቲስት የማሪቱ ለገሠ የክብር አቀባበል

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በፎቶ ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ/ም
ምንጭ: የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የፌስቡክ ፔጅ

ደግነቱን ይዞ አረፈ 💔"የዓይን ብሌኖቼን በነፃ እንዲወስዱ ፈቅጃለሁ !"  | የአርቲስት ታሪኩ ብርሀኑ (ባባ)  ታህሳስ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮዽያ ብሔራዊ ...
11/12/2022

ደግነቱን ይዞ አረፈ 💔
"የዓይን ብሌኖቼን በነፃ እንዲወስዱ ፈቅጃለሁ !"

| የአርቲስት ታሪኩ ብርሀኑ (ባባ) ታህሳስ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮዽያ ብሔራዊ ቴአትር ሽኝት የሚደረግለት ይሆናል ::

ከቀኑ 9:00 ሰዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት ስርዓተ ቀብሩ እንደሚፈጸም ኮሚቴዎቹ ተናግረዋል።

***
"የዓይን ብሌኖቼን በነፃ እንዲወስዱ ፈቅጃለሁ "
- አርቲስት ታሪኩ ብርሐኑ | 2000 ዓ/ም

"ስሜ ከላይ የተጠቀሰው ስጦታ አድራጊ ለስጦታ ተቀባይ የዓይን ባንክ ሕይወት ሲያልፍ ከአስከሬኔ ላይ የዓይን ብሌኖቼ በነጻ እንዲወስዱ ፈቅጃለሁ፡፡ ስሜ ከላይ የተጠቀሰው ስጦታ አድራጊ ለስጦታ ተቀባይ የኢትዮጵያ የዓይን ብሌኖቼን በነፃ እንዲወስዱ ፈቅጃለሁ።"

- አርቲስት ታሪኩ ብርሐኑ -ባባ፤
የዓይን ብሌን የመለገሻ ቃል መግቢያ ቅጽ ላይ በ 23 ዓመቱ፣ 2000 ዓ/ም ላይ የገባው ቃል ላይ ያሰፈረው - 09/08/00

በርካታ ፊልሞችን በመስራት የሚታወቀው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ /ባባ/ ባደረበት ህመም በሕክምና ሲኒዳ ቆይቶ ዛሬ ታህሳስ 2 ቀን 2015 ዓ.ም ማለዳ ላይ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

***
ቴዎድሮስ ተሾመ ስለባባ የገለፀው..
ከዓመታት በፊት ነው።

የሚቀጥለውን የ''ጨዋታ ከቴዲ ጋር'' ሾው እንግዳ ከአዘጋጆቼ ጋር ስንወያይ ለምን ታሪኩ ባባ አይሆንም እንደውም በቅርቡ ስለሚሞሸር በዛው ስለፍቅር ህይወቱም እናወራዋለን ብለን ወሰንን።

እንደሚሞሸር ስሰማ ሰርጉን ከፍ አድርገን በአምስት ኮከብ ሆቴል...... ሆቴሎቹንና አጋር ድርጅቶችን አስተባብረን እሱ ምንም ወጪ ሳያወጣ እንደግስለትና የሾው አካል እናድርገው ብለን ወሰንን።

ታሪኩ በዚህ አጋጣሚ በትልቅ ሆቴል ውስጥ ያማረ ሰርግ እንዲያደርግ ስለምናግዘው......ሁላችንም ባመጣነው ሀሳብ ተደስተናል።

የፕሮግራሙ አዘጋጅ የሺነህ ይህን የምስራች ለታሪኩ የመንገሩን ሀላፊነት ተቀብሎ ታሪኩ ጋ ደወለለት።

ታሪኩ ሀሳቡን ከየሺነህ ከሰማ በኋላ ሰፈሩ ተ/ሀይማኖት እንዲመጣና እንዲወያዩ ቀጠረው።

የሺነህ ይህንኑ ነግሮኝ እኔ ሆቴሎችን የማነጋገሩን ሀላፊነት ወስጄ እሱ ደግሞ ከታሪኩ ጋር የሰርጉን ዝርዝር ሁኔታ ሊነጋገሩ ወደታሪኩ አመራ።

እኔ በተሰጠኝ ሀላፊነት አንድ ባለአምስት ኮከብ ሆቴል አነጋግሬ ተስማምተን ትክክለኛውን የሰርጉን ቀን እንደማሳውቃቸው ተነጋግረን የየሺነህን መምጣት መጠበቅ ጀመርኩ።

የሺነህ መጣ።

ሲመጣ ግን ሲሄድ የነበረው ጉጉትና ፈገግታ ፊቱ ላይ አልነበረም።

''ምነው'' አልኩት የሺነህን

''ሰፈሩ የቀጠረኝ አውቆ ነው'' አለኝ
''ልክ እንደተገናኘን እጄን ይዞ የሰፈሩን ሰዎች እና የተክለሀይማኖት ጀርባ አካባቢዎችን በሙሉ እያስጎበኘኝና ሰዎቹን በሙሉ በትህትና እያጎነበሠ ሠላምታ እየሠጠ

'''አየህ የሺነህ አሁን እናንተ ባዘጋጃችሁት ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ውስጥ እነዚህን ሁሉ ሰዎች የሚያስገባ ቦታ ይኖራል?

እነሱስ በባህላቸው እንደለመዱት ድንኳን ጥለው በሬ አርደው

'ሙሽራዬ ሙሽራ አበባ
ይዘህ....በጊዜ ግባ'

ብለው መርቀው ሳይሸኙኝ ይዤ ሰመለስ 'ሀይሎጋ' ብለው ሳይቀበሉኝ......
በጓዳቸው በጣሉትና በጠመቁት ጠላና ጠጅ ሳይራጩ ...........

እዛ ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ውስጥ ያልሆናችሁትን ሁኑ......
እኔ ስደሰት እናንተ ተመልከቱ

ብላቸው ደስ እሚላቸው ይመስልሀል?

ስላሰባችሁልኝ አመሠግናለሁ።
እኔን ግን የሚያስደስተኝ በሰፈሬ ውስጥ በድንኳን ብዳር ነው።

ብሎ እንደመለሰው ነገረኝ።

ታሪኩ በአካል ተገናኝተን ምን ያህል እንዳስተማ

13/11/2022

ኮሜድያን እሸቱ መልካም ስራ እያከናወነ ነው

29/09/2022

Address

Dire Dawa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Askual Promotion & Advertisement posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to Askual Promotion & Advertisement:

Share