02/04/2026
20 ሚሊዮን መደለያ አልቀበልም ያለው ጌታው ገዛኸኝ ተሬሳ በእግረኛው ሚዲያ...
(ዘሪሁን ተዝናኑ በፌስቡክ ገፁ ካጋራዉ የተወሰደ)
ታሪካዊ ቃለ - ምልልስ‼️
"★ እስከ 6ኛ ክፍል አውንታ በርሲሳ በሚለው ስሜ
ነበር የምጠራው ከ6ኛ ክፍል በኋላ
ገዛኸኝ ተሬሳ በሚል ተቀይሯል።
★ አሩሲ አካባቢ ነው የተወለድኩት። በእናቴ በኩል
ሶዶ ጉራጌ ነኝ። አውንታ ማለት የኮባ ተክል ስሩ
አሚቾ የሚባለው ነው።
★ ለረጅም ጊዜ የሰራሁት በፐርፎርመንስ ኦዲተር ነው።
★ ለ15 ዓመት ያህል በፐርፎርመንስ ኦዲተርነት ለ13
መስሪያ ቤቶች አገልግያለሁ። አሁንም እየሰራሁት
ያለሁት ኦዲቲንግ ነው።
★ በ2002 ዓ.ም ነው ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አካውንቲንግና
ፋንናንስ አጥንቼ በባችለር ዲግሪ የተመረቅሁት።
★ ከዚህ በፊት የሰራሁባቸው መስሪያ ቤቶች ሌብነትን
ያለማመዱ መስሪያ ቤቶች ናቸው።
★ መንገዶች ኮንስትራክሽን ፣ ኢኮስኮ ፣ የኢትዮጵያ
ንግድ ስራዎች ድርጅት ሌብነትን ከውጭ ሀገር
አስመጥተው ያከፋፈሉ ናቸው።
★ በሰራሁባቸው መስሪያ ቤቶች ብዙ አሳፋሪና ከሰው
አዕምሮ ውጪ ያሉ ድርጊቶች ሲከናወኑ አይቻለሁ።
ይኼንን በመሸሽ ነበር ያሳለፍኩት። ስሸሻቸው
እየተከተሉኝ መጡ። ከሀገር አባረሩኝ።
ፊት ለፊት ስጋፈጣቸው መሮጥ ጀመሩ።
እያሸነፍኳቸውም ነው።
★ ከጀርባዬ ያለው ሀቅ ብቻ ነው።
★ #የፊንቴክን ወንጀል ለፌዴራል ፖሊስ እኔ ነኝ
የጠቆምኩት።
★ ከፌዴራል ፖሊስ ፣ ከቂርቆስ ክ/ከተማ ጋር
በመጠቆምና መረጃ በመስጠት ነው የሰራነው።
★ ኮሚሽነር ብርሃኑ ይኼንን ነገር ከዳር የምታደርስልኝ
ከሆነ የማደርግልህን አታውቅም ብሎ አበረታታኝ።
★ ፊንቴክ ውስጡ የመኪና ሽያጭ ብቻ ሳይሆን የድንበር
ተሻጋሪ ወንጀሎች አሉበት። ህገ - ወጥ የሰዎች
ዝውውር ነበረበት። መኒ ላውንደሪ ነበረበት።
አደገኛ ወንጀሎች ነበሩበት።
★ ወንጀሎቹን መርምሮ ሳይጨርስ ሰዎቹን መያዝ
ጀመረ። ባለቤቱን ዳንኤል ዮሐንስን ያዘው።
ያን ጊዜ ግርማዬ ከሀገር ወጣ።
የዜግነት ድርሻዬን በዚህ ደረጃ ነው የተወጣሁት።
★ ፊንቴክ ማለት ፋይናንስ ቴክኖሎጂ ማለት ነው።
የቻይና ካምፓኒ ነው። ስራው ገንዘብ ማዘዋወር
ነው እንጂ መኪና ማስመጣት አይደለም።
የመኪና አስመጪነት ፍቃድ የለውም።
★ ጅቡቲ ላይ የታዩት መኪናዎች ሿሿ ናቸው።
የተለያዩ ሰዎች ያስመጧቸው እንጂ ፊንቴክ
ያስመጣቸው አይደሉም።
እንደሚመስለኝ ገንዘቡ ሊታጠብ ነው የፈለጉት።
★ 19 አይነት የወንጀል ጉዳዮች ስላሉበት መንግስት
የሚያየው ወንጀሎቹን ብቻ ነው።
★ ባለቤቱ ዳንኤል ዮሐንስ ከዚህ በፊት ሄሎ ታክሲ
የሚባል ድርጅት አቋቁሞ ወደባህልና ቱሪዝም
ሄዶ ተፈቀደለት። የተለያዩ ባህሪያት በማምጣቱ
ተከለከለ።
★ የነፃ ቀረጥ መብቱን ለሌላ መኪና አስመጪ ድርጅት
ሰጠው። በዚህም 401 ሚሊዮን ብር ተላልፏል።
★ ግርማይ ገ/ሚካኤል የተባለው ደግሞ አስካሉካን
ትሬዲንግ በሚል ደቡብ አፍሪካ ለዓለም ዋንጫ
አጓጉዛለሁ ብሎ ብር ይዞ ጠፍቶ በኢንተርፖል
ተይዞ መጥቶ ፍርድ አግኝቶ የተለቀቀ ነው።
★ ዳንኤል ዮሐንስና ግርማይ ገ/ሚካኤል
3.5 , 3.5 ሚሊዮን ብር አዋጥተው በ7 ሚሊዮን ብር
በጋራ ፊንቴክን መሰረቱ።
ዳሰማን ደግሞ ዳንኤል ዮሐንስና እስቲፋኖስ ዮሐንስ
በጋራ የመሰረቱት ነው። ላይፍ ላይን ኢንቨስትመንት
የሚባል ደግሞ አለ። አመጣጡ መስመሩ ይኼ ነው።
★ ከጀርባ ሆነው ነበር ስራውን የሚሰሩት።
★ በመታሰራቸው አላዝንም።
★ ኢትዮጵያ ውስጥ ሌብነት በህግ አግባብ ፍርድ
ሊሰጠው ይገባል።
★ በአደባባይ የስቅላት ወንጀል ሆኖ ሲበየን ብቻ
ነው ብዬ የማስበው።
★ በአሳሳች ማስታወቂያ ምክንያት ህብረተሰቡን
አሳስታችኋል ብሎ መንግስት ከያዛቸው
እኔ ልሆን አልችልም።
★ በ7 ሚሊዮን ብር ካፒታል መኪና እናስመጣለን ያለን
ካምፓኒ አላዩትም ማለት ነው። ወይም አይተውት
ችላ ብለው አልፈውታል ማለት ነው።
★ አንድ ማስታወቂያ ሲሰራ ህጋዊነቱን ማረጋገጥ
የማስታወቂያ ሰራተኛው ሀላፊነት ነው።
በፍትሀብሔርም ያስቀጣል። በውስጡም
ወንጀል አለበት።
★ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የፓርላማ አባል ስለሆኑ
ያለመከሰስ መብት አላቸው። ያለመከሰስ
መብታቸውን አስነስቶ ወደ ፍርድ ቤት ማቅረብ
የፖሊስና የፍትህ ሚኒስትር ስራ ነው።
ፓርላማውም ሀላፊነት አለበት።
★ ሌሎች ያልተያዙም አሉ። ድምፃዊ ታደለ ሮባም አለ።
የፊንቴክ አምባሳደር ነው። ጋዜጠኛ ትዕግስትም አለች።
ሁለት ቲክቶከሮችም አሉ።እነሱን የመያዝ የመልቀቅ
የኔ ፋንታ አይደለም። የፖሊስ ፋንታ ነው።
ፖሊስ ሊተዋቸው ወይም ሰሞኑን ሊለቀሙ ይችላሉ።
★ አብርሃም ግዛው አንድ ቦታ ላይ ብቻ አልነበረም።
ሄሎ ታክሲ ላይ ፊት ለፊት ታየዋለህ።
ፊንቴክ ኢንቨስትመንት ላይ በየቦታው ታየዋለህ።
ዳሱማ ትሬዲንግ ላይ እንደገና ታየዋለህ።
ሳያውቁ ነው ልትለኝ አትችልም።
★ የፖሊስ ሪፖርት እንደሚያመለክተው እያንዳንዳቸው
8 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መኪና ተሸልመዋል።
ይኼ ከገንዘቡ ውጪ ነው።
★ መንሱር ጀማልን ደጋግሜ ነካካሁት። ደጋግሜ ስነካካው
ሚዛኑን ሳተ እና ተሳደበ። የኔ ድክመት መልኬ ሆኖ
ታየው። ተሳደበ እና ፖሰተ።
★ መንግስት የሚለቀው ከሆነ ተምሮ ሰቃይ ተማሪ
ሆኖ ይወጣል የሚል ተስፋ አለኝ።
★ ወንጀል እና ክፋት ይለያያል።
★ በዚህ ጉዳይ ብራቸውን ከተበሉ ሰዎች ውስጥ
ቂርቆስ ክ/ከተማ ራሱን አንቆ የገደለ ሰው አለ።
ከዚህ ሰውዬ ጀርባ ልጆች አሉ። ቤተሰብ አለ።
አንደኛው ኩላሊቱን ዲያለሲስ የሚያደርግ ነው።
★ ማስታወቂያ የፍትሀብሔር ጉዳይ አይደለም።
እስከ 5 ዓመት ሊያሳስር ይችላል።
★ ለወንጀለኛ እስከተባበርክ ድረስ ወንጀለኛ ነህ።
★ ንግድ ፍቃዱን አልተመለከቱም። የራሳቸውን ገንዘብ
ብቻ ነው የተመለከቱት።
★ ቢመለከቱት ኖሮ እንደ እነ ሉላ ገዙ ፣ ዕፀገነት አበበ
እና አምለሰት ሙጬ ይኼ ማስታወቂያ ይቅርብኝ
ይሉ ነበር። እነ ሉላ ያዩት ነገር ስላለ ነው ይቅርብን
ያሉት።
★ ሰራዊት ፍቅሬ ከዚህ በፊት ሲኖትራክ ይመጣላችኋል
ብሎ ገንዘባቸውን የተበሉ ሰዎች ብዙ ናቸው።
★ ሰለሞን ቦጋለ ለሆስፒታል ብሎ ብዙ ብር ለቅሞ
እስካሁን ገንብቶ አላየነውም። ገንብቶ ብናየው
እናከብረው ነበር። እስካሁን ግልፅ የሆነ ነገር የለም።
★ ዜጋ ዜጋ ነው። ሲኒየር ዜጋ የሚባል ነገር የለም።
ማንኛውም ሰው ወንጀል እስከፈፀመ ድረስ
በሕግ እኩል ነው።
★ የሌብነት ሲስተሙ ጨምሯል። አደገኛነቱ ጨምሯል።
★ ገንዘባቸውን የተበሉ ሰዎች ጀርባቸው ብዙ ቁስል አለ።
ያ ቁስል አንተንም ሊሰማህ ይገባል። ሰራዊት ፍቅሬም
ሊሰማው ይገባል። ሁላችንም ሊሰማን ይገባል።
ገንዘባቸውን ወይም መኪናቸውን ቢያገኙ ከእኔ በላይ
ደስተኛ የለም።
★ በረከት ገበሬዋ ለፌዴራል ፖሊስ ከሳኝ ነበር።
አንድ ሺህ ዳላር ሰጥቼዋለሁ ካለች ማስረጃ ታምጣ።
★ ሰሞኑን ደግሞ ወደ እርዳታ ድርጅቶች እንሄድባቸኋለን።
ቤ/ክርስቲያን ፣ መስጂድ ቸርች ውስጥም አሉ።
★ ከሚገባው በላይ የሚያከብሩኝና የሚወዱኝ ሰዎች
አሉ። የነሱን ቃል ጠብቄ እሄዳለሁ።
★ ስራዬ ከመንግስት ጋርም ሆነ ከፓርቲ ጋር ምንም
አይነት ግንኙነት የለውም።
★ የእኔን ኮንተንት አንዲት ስህተት ብታገኝበት
እዚህ ሰፈር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነው
የምባረረው። የሰውን አመኔታ ላለመብላት
ጥንቃቄ እያደረግሁኝ እጓዛለሁ።
★ የፊንቴክ ባለቤት አቶ ዳንኤል ራሱ ደውሎልኝ
ሰዎች ለአውንታ 20 ሚሊዮን ብር እንስጠውና
ይኼንን ጉዳይ ያቁም ብለውኛል። ልስጣቸው ወይ?
ወይስ አንተ ተነጋግረህ ነው ወይ ብሎኛል።
★ ሕዝቡ የሚሰጠኝን 5 ብር ጣፍጦኝ ነው የምበላው።
★ መስሪያ ቤቴ ከሚሰጠኝ ደመወዝ በላይ
5 ብሯ ትጠቅመኛለች።
★ ለልጆቼ የማስተላልፈው ርስት ይኼ ብቻ ነው።
★ ይኼንን ንፁህነቴን ረሃብ ካላስቸገረኝ ፣ ድህነት
ካላስቸገረኝ ይዤው እጓዛለሁ።
★ ተደብድቤ ጳውሎስ ሆስፒታል ተኝቼ አውቃለሁ።
በመጨረሻም የማመሰግናቸው ፦
★ ለፌዴራል ፖሊስ ኢንስፔክተር ሀብታሙ
ላንተ ልዩ ክብር አለኝ።
★ ኮሚሽነር ብርሃኑ ኢትዮጵያዊነትን የምወደው
እንዳንተ ያሉ ሰዎች ስላሉ ነው እንጂ ተሟጦ
ባለቀ ነበር። ምልክቶቼ ትሆናላችሁ።
እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ።
በተጨማሪም ፦
ደመወዝ ከፋዮቼንም አመሰግናለሁ። እንዳትረሱ
ደመወዜን ክፈሉ ‼️"