Haile Tilaye / ሀይሌ ጥላዬ/

Haile Tilaye / ሀይሌ ጥላዬ/ ሥለፍቅርና አንድነት ብቻ እንወያይ እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል

20/05/2026
21/04/2022

ኢትዮጵያዊ ነን!
""""""""""""""""""
ፈቅደን ሲመሩን፣ ችቦ ተቀባይ
ለሚነዱን ግን፣ አሻፈረን ባይ
ካልነኩን በቀር፣ ቀድመን ማንዘምት
ከጋሻ በፊት፣ ጦር የማንሸምት

ኢትዮጵያዊ ነን!

ህብር ያስጌጠው፣ ሕይወት ለማብቀል
ዘር ሳናጣራ፣ የምንዳቀል
ለነዱን ሰይጣን ፣ ለመሩን ሠናይ
ጌታን ከገባር ፣ ለይተን ምናይ

ኢትዮጵያዊ ነን!

ብዙ ህልሞችን፣ ወዳንድ ዓላማ
የሰበሰበ ፣ገርቶ ያስማማ
በደምና ላብ ፣ያቆመው ካስማ
አገዳ አይደለም ፣የሚቀነጠስ
የዝምድናችን መተሳሰርያ
ሺ ጊዜ ቢከር፣ የማይበጠስ

ኢትዮጵያዊ ነን!

ምን ሆድ ቢብሰን ፣ምን ብንቸገር
እድር አይፈርስም፣ እንኳንስ አገር
ብለን በትዕግሥት ፣የምንሻገር
ሲገፈትረን ፣ግፈኛና አጥቂ
ቁልቁል ሲሰደን፣ ሽቅብ መጣቂ
ለውርደት ሲያጩን ፣የምንጀነን
ኢትዮጵያዊ ነን !

በበውቀቱ ሥዩም

30/03/2022

🙏🙏🙏🙏❤ *You*
❤ *Are*
❤ *One*
❤ *Person*
❤ *Very*
❤ *Important*
❤ *To*
❤ *Me*
❤ *And*
❤ *I*
❤ *Want*
❤ *To*
❤ *See*
❤ *You*
❤*After*
❤COVID-19
💝 *Send it to all the people you want to see after COVID-19.*💝

18/02/2022

የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር የፌድራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ለግብርና አገልግሎት የሚጠቀሙበት የመስኖ ውሃ ቦይ ባለመሰራቱ ለከተማችን ከፍተኛ የሆነ የመልካም አስተዳደር ችግር ሁኖ በመቆየቱ ከተማ አስተዳደሩ ካናል እንዲገነባ በተደጋጋሚ ጥያቄ በማቅረብ አዲሱ የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኃላፊ ኮማንደር አላምረው ተረፈ ጥየቄውን መሰረት በማድረግ ዛሬ ከአቦፀበል አካባቢ ጀምሮ እስከ ቆቦ ጅረት ድረስ ከ 1.5 ኪ.ሜ በላይ የሚሆን ዘመናዊ ኮንክሪት ካናል ለአሸናፊ ኮንትራክተር የፌድራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ባለስልጣናት በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል

05/08/2021
05/08/2021

ማሪታ ሎሬንዝ የቀድሞው የኩባ መሪ፣ የፊደል ካስትሮ ፍቅረኛ ነበረች። በ1960
( እኤአ) የአሜሪካ የስለላ ድርጅት፣ ሲአይኤ፣ ሰዎች ለአንድ ትልቅ ተግባር አጯት።
“ወደ ኩባ ተመልሰሽ ካስትሮን ማግኘት ትችያለሽ?”
“ አዎ”
“ይህን እንክብል ብንሰጥሽ፣ ምግቡ ውስጥ ለመጨመር ፈቃደኛ ትሆኛለሽ?”
“አዎ"
ማሪታ መርዛማውን እንክብል ይዛ ከአሜሪካ ወደ ሃቫና በረረች።
ካስትሮ በጊዚያዊነት ያረፈው ሂልተን ሆቴል ነው። ማሪታና ካስትሮ ተቃቅፈው ተሳሳሙ።
“ ልትገይኝ ነው አይደል የመጣሽው?”
“አዎ”
“ ሽጉጤ ይኸው፣ ግደይኝ ”
ማሪታ እየተንቀጠቀጠች ማልቀስ ጀመረች። “ ልገድልህ አልችልም። ምንም ያደረከኝ
ነገር የለም።"
ትንሽ ፍቅር ሰርተው ከክፍሉ እያለቀሰች ወጣች።
በጋዜጣ ፊታቸውን የሸፈኑት የሲ አይ ኤ ሰዎች የማሪታን ለቅሶ አይተው፣ ካስትሮ
የሞተ መስሏቸው በደስታ ፈነጠዙ። ማሪታ ምንም ሳትተነፍስ ከሆቴሉ ወጥታ በቀጥታ
ወደ አየር ማረፊያ ከነፈች። እቅዱም ከሸፈ።
ማሪታ ስለ ኩባ የነጻነት ትግል በተሰራ ዶክመንታሪ ፊልም ላይ ስለነበረው ሁኔታ
ስታስረዳ ልብን ትነካለች ።
ሲአይኤ የቆሸሸ ታሪክ ያለው ተቋም ነው። ቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ ያነበብኳቸው
Rogue State እና Confessions of an Economic Hit Man ስለ ሲአይኤ አይኔን
እንድከፍት ያደረጉ ድንቅ መጽሃፎች ናቸው።
ካለፉት 3 ዓመታት ጀምሮ በኢትዮጵያ የታዩ ክስተቶች፣ በተለይም ህወሃት በሰሜን እዝ
ላይ የፈጸመው ጥቃትና በርካታ አፍራሽ ክስተቶች አንዳች የሆነ ግንኙነት ይኖራቸው
ይሆን እያልኩ መጠየቅ ጀምሬያለሁ።
ብቻ የምዕራባውያን ወቅታዊ የኢትዮጵያ ፖሊሲ በ Rogue State ውስጥ ካነበብኳቸው
ታሪኮች ጋር በብዙ ነገር እየተመሳሰለብኝ የማወቅ ጉጉቴን ከፍ አድርጎታል።
(የቡርኪናፋሶው ወጣት ብሄርተኛ መሪ የቶማስ ሳንካራ አሳዛኝ ታሪክንም ዩ ቱዩብ ላይ
ማየት ትችላላችሁ።)
ለማንኛውም የኢትዮጵያ የድህንነት መስሪያ ቤት ነገሮችን አስቀድሞ አነፍንፎ
የሚያከሽፍ ብቃት አዳብሯል ብዬ አምናለሁ። የቀድሞው የኩባ የደህንነት ሃላፊ ወደ
700 መቶ ያክል የግድያ ሙከራዎችን ማክሸፋቸውን ሲናገሩ ስምቼ ወቼ ጉድ እያልኩ
ነው።
ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም
#ትክክለኛ ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ፔጃችንን
👉Like
👉follow
👉Share በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
ለሃሳብ አስተያይታችሁ 'ኮመንት ቦክሱን ' ይጠቀሙ።

ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራም ቻናላችንን ይጎብኙ👇
https://t.me/KebronMedia
ኢትዮጵያ ታሸንፋለች✊

Address

ይፋት መንደሬ
Debre Birhan

Telephone

+251913700004

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Haile Tilaye / ሀይሌ ጥላዬ/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to Haile Tilaye / ሀይሌ ጥላዬ/:

Shortcuts

Share