የንባብ ሀሁ-ኣችን

የንባብ ሀሁ-ኣችን 📚 ማንበብ ከተከታይነት አባዜ የሚያላቅቅ ራስን የመቻል ምልክት ነው!

ለወጣቶች አሁናዊ አኗኗር ጥሩ ሆነው ከተፃፉ መፅሐፎች መካከል
15/03/2025

ለወጣቶች አሁናዊ አኗኗር ጥሩ ሆነው ከተፃፉ መፅሐፎች መካከል

07/03/2025
27/11/2024

የአርማ መግለጫ

ክብ የመሆኑ ምሳሌ:-

ዓለም አቀፋዊ የንባብ ማኅበር እንደሚሆን ተስፋ በማድረግ የዓለምን ቅርጽ አስይዘነዋል። ምክንያቱም አለም በአንባቢዎች ስትሞላ ንቁ አስተዋይ እና ሰላማዊ ዜጋ ይፈጠራል። ስለዚህ ለማህበራችን ክብ አርማ ተጠቅመንበታል።

የአማርኛ የቃላት ምሳሌዎች:-

የህብረቱ ስም በአገራችን በመጀመሪያ ደረጃ ፊደላት ስም መመስረቱ ማንኛውም አንባቢ ሰፊ እውቀት ከማግኘቱ በፊት ፊደላትን በሚገባ ተረድቶ ማንበብ እንዳለበት እና የቃላቶቹን ትርጉም እና ሃይል መረዳት እንዳለበት ያመለክታል። በዚህ ምክንያት የመጀመሪያ ፊደላችንን ለማህበራችን ስያሜ ለመጠቀም አስችሎናል።

አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለም እና አንባቢዎች የተሰጡትበት ምሳሌነት:- 🇪🇹

እነዚህን ቀለሞች የመረጥንበት ምክንያት የሀገራችን ኢትዮጵያ ተወዳጁና የማይለዋወጥ ሰንደቅ ዓላማ በመሆኑ ማኅበሩ ተወዳጅ እንደሚሆን እና በአጠቃላይ ኢትዮጵያን እንደሚያገለግልና በአንባቢ ዙሪያም ድርጅታችን አንባቢ ልጆችን እንደሚያፈራ ይጠቁማል። በአገራችን ከልጅነት ጀምሮ በጥበብ ማደግንም አብሮ የሚያንፀባርቅ ገላጭ ምልከታ ነው።
በእነዚህ ቀለሞች የተከበበበት ሌላ ተጨማሪ ምክንያት የቀለማት ሁለንተናዊ ዓለማቀፋዊ ትርጉም ገላጭነቱ ግልፅ በመሆኑ ልንጠቀምበት ችለናል።ለምሳሌ:-
• አረንጓዴ ተፈጥሮን፣ እድገትን፣ ሚዛንን፣ ጤናን እና ብልጽግናን ይወክላል።
• ቢጫ፡- ደስታን፣ ብሩህ አመለካከትን፣ ጉልበትን፣ ጥንቃቄን እና ማስተዋልን ያመለክታል።
• ቀይ፡- ስሜትን፣ ፍቅርን፣ ጉልበትን፣ አደጋን፣ ሃይልን እና ጥንካሬን ያሳያል።
ንባብ የእነዚህ ቀለሞች ትርጉም ነጸብራቅ ነው። የእነዚህ ቀለሞች ትርጉም በአንባቢው የሚንፀባረቁ ባህሪያት ናቸው። ስለዚህ ለዓርማችን ልንጠቀምባቸው ችለናል።አንድም ዓለማቀፋዊ የቀለም ትርጓሜ አንድም የሐገራችን አርማ በመሆኑ ቀለምን እንደ ባለ ሁለት አፍ ጎራዴ ለማህበራችን ስያሜ ጥቅም ተጠቅመንበታል።

የምስሎች የቀለም ምሳሌ:-

የምስሉ ቀለም ጥቁር ሰማያዊ መሆኑ ብዙውን ጊዜ ጥልቀትን፣ መረጋጋትን፣ መተማመንን እና ብልህነትን ጨምሮ የተለያዩ ትርጉሞችን ያሳያል። በንባብ እና በማህበር አውድ ውስጥ ጥቁር ሰማያዊ ትኩረትን የሚያበረታታ እውቀት፣ጥበብ እና የመረጋጋት ስሜት ጋር ያለውን ግንኙነት ሊያመለክት ይችላል። የማሰላሰል እና የውስጠ-ግንዛቤ ስሜትን ሊፈጥር ይችላል። ይህም ከንባብ እና ከመማር ጋር ለተያያዙ አካባቢዎች ተስማሚ ቀለም ያደርገዋል።በዚህም ምክንያት በኅብረቱ ምስል ላይ ጥቁር ሰማያዊ ቀለም ተጠቅመናል።

የሁለቱ ከዋክብት ⭐ ምልክት ምሳሌ

በጽሁፉ መካከል ያለው የኮከብ ምልክት ይህ የንባብ ማኅበር ወደፊት ኮከቦች የሚሆኑ ልጆችን እንደሚያፈራ ጠቋሚ ሲሆኑ በጨለማው ስፍራ ሁሉ የሚያበሩ እና ተወርዋሪ ከዋክብት እንደሚሆኑ የሚያሳይ አንፀባራቂ ባለ ራዕይ ምልክት ነው።

የሁለቱ ቋንቋዎች ምሳሌያዊ አስፈላጊነት :-

ወደፊት ዓለማቀፋዊ ይዘት እንደሚኖረውና የሐገራችን ቋንቋም በዓለማት እንደሚጠቀስ በማሰብ በክብር ቦታውን ይዟል

ስዕላትና ፊደላት በነጭ ሰሌዳ የመስፈሩ ምሳሌነት:-

ነጭ ብዙ ጊዜ ንፅህናን፣ ንፁህነትን እና አዲስ ጅምርን ያመለክታል። በነጭ አካላት የተገለጹ ገጸ-ባህሪያት ወይም መቼቶች ትኩስነት ወይም የሞራል ግልጽነት ስሜት ሊፈጥሩ ይችላሉ።
ሰላም እና መረጋጋት፡- ነጭ ሰላምን፣ መረጋጋትን እና መረጋጋትን ሊወክል ይችላል። ጸጥ ያለ ድባብ ለመፍጠር ወይም የአንድ ገጸ ባህሪ ሰላማዊ የአእምሮ ሁኔታን ለማመልከት ሊያገለግል ይችላል።ይህም ለንባብ መኅበሩ መገለጫ ሊሆን ችሏል..

ሰላም የንባብ ማኅበራችን ተከታዮች📚 በዓመቱ ሁለተኛ ሰንበት በ12/01/2017 በሚኖረን ውይይት ርዕሱ ስላልተነገረ ጉዳይ  እንወያያለን።🌾እንግዳ ይዞ መምጣት መለያችን ይሁን።ሰአት ይከበር!አ...
20/09/2024

ሰላም የንባብ ማኅበራችን ተከታዮች📚
በዓመቱ ሁለተኛ ሰንበት በ12/01/2017 በሚኖረን ውይይት ርዕሱ ስላልተነገረ ጉዳይ እንወያያለን።🌾
እንግዳ ይዞ መምጣት መለያችን ይሁን።
ሰአት ይከበር!
አድራሻ ጎጃም ደ/ማርቆስ ቦሌ ቋፈርስት
ሰዓት 8:00

በልተን ከምንገነባው አካላዊ ቅርፅ በላይ ማንበባችን ከሁሉም፣በሁሉም ለሁሉም የበቃንና የተዘጋጀን ያደርገናል 💫

ቤተ ሀሁ 9ኛ ዙር 9ኛ ሳምንትበዕለተ ሰንበት📚ጥር 28-2015📚  እሁዳችንን ከ8:00-10:30 ባለው ጊዜ  በነፃነት፣በመከባበር እንዲሁም በመደማመጥ ሆነን:-  🙊ይሉኝታ ⁉️ 🧐ይሉኝታ ትርጓ...
03/02/2023

ቤተ ሀሁ 9ኛ ዙር 9ኛ ሳምንት

በዕለተ ሰንበት
📚ጥር 28-2015📚 እሁዳችንን ከ8:00-10:30 ባለው ጊዜ በነፃነት፣በመከባበር እንዲሁም በመደማመጥ ሆነን:-

🙊ይሉኝታ ⁉️

🧐ይሉኝታ ትርጓሜው ከወድየት ነው?
👉ይሉኝታ ከአክብሮት ወይስ ከፍራቻ ይመነጫል?
👉ይሉኝታ ያለበት ሰው አርቆ አሳቢ ሊሰኝ አይችልም?ሊባልስ አይገባውም?ወይስ ኋላ የቀረ ያሰኘዋል?
👉 በይሉኝታ የምንኖረው ወዳጅ ላይ ነው? ለጠላትም ይሉኝታ ይሰራል?

በሚሉ ሐሳቦች ዙርያ የራሳችንን እይታ ከነባራዊ ሀሳቡ ጋር በማያያዝ፣ያነበብነውን በማከል፣በሰከነ መንፈስ የምንነጋገር ይሆናል።

ጠቃሚ የገፅ ቅጠሎች ከመፅሐፍት ብቻ የሚገኙ አይደሉም! ከተገለጡ የሰው ልጆችም ልዩ የመፅሐፍት ገፆች ናቸውና ጥያቄዎችን በመወርወር፣በመመርመር ሰውነትን እየገለጥን በጋራ እናንብበው❌✅
👉መገኛ ሰዓት:- 8:00
👉መገኛ ቦታ:-ቋ-ፈርስት ቢሮ ቁጥር 117(ቦሌ ቄሴ ሱቅ ጎን በሚገኘው ፎቅ)
🏃‍♂ ውይይቱን ለመካፈል ለማወቅ መፈለግ እንዲሁም መገናኘት ነው የሚያስፈልገው።መግቢያ #ነፃ📚
ስንመጣ ወዳጅ ጓደኛን መጋበዝ አንርሳ!

👉 ቦታውን ካላወቁ ከውይይት ሰዓቱ በፊት ቀድመው ይደውሉ👇
☎️09 42 86 27 33
☎️09-38-94-99-18
☎️09-48-27-13-58


ቤተ ሀሁ 8ኛ ዙር በዕለተ ሰንበት(እሁድ) 📚ጥር 21-2015📚  እሁዳችንን ከ8:00-10:30 ባለው ጊዜ  በነፃነት፣በመከባበር እንዲሁም በመደማመጥ ሆነን:-👉ቅናት መነሻው ከየት ነው?👉የቅና...
28/01/2023

ቤተ ሀሁ 8ኛ ዙር

በዕለተ ሰንበት(እሁድ)
📚ጥር 21-2015📚 እሁዳችንን ከ8:00-10:30 ባለው ጊዜ በነፃነት፣በመከባበር እንዲሁም በመደማመጥ ሆነን:-
👉ቅናት መነሻው ከየት ነው?
👉የቅናት መነሻ ከፍቅር ነው ከጥላቻ?
👉ቅናት ጥቅም ይኖረው ይሆን?ጉዳቱስ
👉 የቅናት መደምደምያው በበጎ ጎን እና በጎ ባልሆነ ጎን ምን ይሆናል?
በሚሉ ሐሳቦች ዙርያ የራሳችንን እይታ ከነባራዊ ሀሳቡ ጋር በማያያዝ የምንመጋገብ ይሆናል።

የሚያዳምጠኝ ሰው እፈልጋለሁ ወይም ደግሞ መስማት እፈልጋለሁ፣ምን አገኛለሁ?ብሎ ለሚጠይቅ ሁሉ ተገኝቶ ይሞክረው እንላለን። ማሰብ፣መመራመር፣መጠየቅ የሚችል ሁሉ መጦ መወያየት ይችላል። ቦታ ቢጠበን በሐሳብ እንተቃቀፋለን ኑ እንመጣለን።
👉መገኛ ሰዓት:- 8:00
👉መገኛ ቦታ:-ቋ-ፈርስት ቢሮ ቁጥር 117(ቦሌ ቄሴ ሱቅ ጎን በሚገኘው ፎቅ)
🏃‍♂ ውይይቱን ለመካፈል ለማወቅ መፈለግ እንዲሁም ማንበብ ብቻ ነው የሚያስፈልገው።መግቢያ #ነፃ
ስንመጣ ወዳጅ ጓደኛን መጋበዝ አንርሳ!

👉 ከውይይት በፊት ቀድመው ይደውሉ👇
☎️09-38-94-99-18
☎️09-48-27-13-58


ቤተ ሀሁ 7ኛ ዙር ሰባተኛ ሳምንትበዕለተ ሰንበት(እሁድ) 📚ጥር 14-2015📚  እሁዳችንን ከ8:30-10:30 ባለው ጊዜ  በነፃነት፣በመከባበር እንዲሁም በመደማመጥ ሆነን:-👉ጥርጣሬ ምንጩ ከወ...
21/01/2023

ቤተ ሀሁ 7ኛ ዙር ሰባተኛ ሳምንት

በዕለተ ሰንበት(እሁድ)
📚ጥር 14-2015📚 እሁዳችንን ከ8:30-10:30 ባለው ጊዜ በነፃነት፣በመከባበር እንዲሁም በመደማመጥ ሆነን:-
👉ጥርጣሬ ምንጩ ከወድየት ነው?
👉ተጠራጣሪነት አለመታመን ነው?ወይስ አለማመን?
👉የጥርጣሬ መንፈስ ከጤነኝነት የሚመነጭ ነው ወይስ ቅናትንም ያክለዋል?
👉ጥርጣሬ ከማመን አንፃር ያለው ጉልህ አስተዋፅዖ እና እንከኖች ምንድናቸው?
👉የጥርጣሬ መዳረሻውስ ምን ይሆን ?
በሚሉ ሐሳቦች ዙርያ የራሳችንን እይታ የምንመጋገብ ይሆናል።

የሚያዳምጠኝ ሰው እፈልጋለሁ ወይም ደግሞ መስማት እፈልጋለሁ፣ምን አገኛለሁ?ብሎ ለሚጠይቅ ሁሉ ተገኝቶ ይሞክረው እንላለን። ማሰብ፣መመራመር፣መጠየቅ የሚችል ሁሉ መጦ መወያየት ይችላል። ቦታ ቢጠበን በሐሳብ እንተቃቀፋለን ኑ እንመጣለን።
👉መገኛ ሰዓት:- 8:30
👉መገኛ ቦታ:-ቋ-ፈርስት ቢሮ ቁጥር 117(ቦሌ ቄሴ ሱቅ ጎን በሚገኘው ፎቅ)
🏃‍♂ ውይይቱን ለመካፈል ለማወቅ መፈለግ እንዲሁም ማንበብ ብቻ ነው የሚያስፈልገው።መግቢያ #ነፃ
ስንመጣ ወዳጅ ጓደኛን መጋበዝ አንርሳ!

👉 ከውይይት በፊት ቀድመው ይደውሉ👇
☎️09-32-81-77-50
☎️09-45-93-30-70


14/01/2023

ሰላም የሀሁ ቤተሰቦች ከበዓል በፊት ያደረግናቸው ተከታታይ የውይይት ቀናት የተሳኩ እና የተገኘን ሁሉ መልካም እውቀትን መሸማመታችን ይታወሳል። ይህ በእንዲህ እንዳለ መጭዎች እሁዶች የሰርግ ቀናት፣የንግስ በዓላት እና መሰል በዓሎች በመደራረባቸው ምክንያት የነገን እሁድ ውይይት (07-05-2015)አለመኖሩን ለማሳወቅ እንወዳለን። ውይይት በማኅበሩ የለም ማለት የሚያጋጥሙን መሰል ድርጊቶች ላይ ውይይት አይኖርም ማለት እንዳልሆነ ይታወቃል።እናም በምንታደምባቸው ቦታዎች ሁሉ መልካም ነገሮችን በመቃረም ለሆዳችን ስጋዊ መብልን፣ለአይምሯችን ደግሞ እውቀታዊ እና ሀሳባዊ ምግብ በመመገብ ሁሉን አቀፍ እንሁን። ማንበብ መፅሐፍትን ብቻ ሳይሆን ባሕል እና ወግን፣እምነት እና አምልኮን፣ቱፊት እና ስርዓትን ነውና መፅሐፍትም የተቀዱት ከተዘረዘሩት ምንጮች ነውና ከምንጮቹ እውቀትን ለመጠጣት ራሳችንን ዝግጁ እናድርግ

ሆኖም በሰኞ ምሽት እንዲሁም በሐሙስ ምሽት(2:30 በኋላ )የእረፍት ሰዓታትን በመጠቀም የምናሳልፋቸውን የእሁድ ቀናት ለማካካስ በቴሌግራም ቤታችን እንድንወያይ እንጠይቃለን።

"መልካም ምሽት"

በሕዳር 27/2015 በደብረ ማርቆስ ከተማ በተካሔደው የኤች አይ ቪ ኤድስ ቀን አመራሮች በተገኙበት እና የጤና ቢሮዎች ባሉበት ሸጋ መርሐግብር ተሰናድቶ መቅረቡ ይታወሳል። በቀኑም 📚የሀሁ የን...
08/12/2022

በሕዳር 27/2015 በደብረ ማርቆስ ከተማ በተካሔደው የኤች አይ ቪ ኤድስ ቀን አመራሮች በተገኙበት እና የጤና ቢሮዎች ባሉበት ሸጋ መርሐግብር ተሰናድቶ መቅረቡ ይታወሳል። በቀኑም 📚የሀሁ የንባብ ተወካይ አባላት በቦታው በመገኘት የኤች አይ ቪ ኤድስ ወረርሽኝ ሊቀንስ የሚችልበትን መንገድ ከመፅሐፍት ንባብ ፣ራስን ከመገንባት፣ በከተማው የሚገኙ መፅሐፍት ማከራያ እና ማዋሻ ቦታዎች(አትሮንስ እና ሐዲስ መፅሐፍት ማከራያዎች) በመጠቆም ስሜትን በምን መገደብ እና መቆጣጠር እንዲቻል ከኤች አይ ቪ ኤድስ መሰረታዊ መከላከያ ጋር አዋዝተን ለማቅረብ ሞክረናል።
ወደፊት የሰው ልጅ በማንበብ ራሱን ካልገነባ እና ካላጠነከረ በሰው ልጆች ግፊት ተፈጥሯዊ ስሜቱን ሊቆጣጠር የሚችልበት መንገድ ጠባብ እንደሆነ እሙን መሆኑን እናምናለን። ለዚህም ሀሁ የንባብ ማኅበርን በመርዳት የተሻለ ትውልድ እንፍጠር ስንል ሀሳባችንን ለተሰበሰበው ሁሉ ለማስገንዘብ ሞክረናል። በዕለቱም በስማችን የተፃፉ ብሮሸር፣ባነር እና አባላትን በመያዝ ለማኅበሩ እውቅና ተፈጥሯል።
እርሶም ማኅበሩን በማስተዋወቅ ሀሳቦችን like share በማድረግ ማኅበሩን ያግዙ።

Address

Debre Mark'os
Debra Markos
YENEBABHAHUACHEN

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የንባብ ሀሁ-ኣችን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to የንባብ ሀሁ-ኣችን:

Shortcuts

Share