Dawuro Times

Dawuro Times አዳዲስ እና ጠቃሚ መረጃዎች DT

IPhone 17 ስልክ መያዝ እኛንም ያምረናል🙄
21/08/2026

IPhone 17 ስልክ መያዝ እኛንም ያምረናል🙄

ኢንተርኔት ሲጠቀሙ ብዙ ዳታ እንዳይቆጥሩ ለማድረግ ቀላል መፍትሄዎች!1. በአንድሮይድ (Android) ላይ· የዳታ ቆጣቢ (Data Saver) ያብሩ፦ ይህ በጣም ውጤታማው መንገድ ነው። አብዛኛ...
21/08/2026

ኢንተርኔት ሲጠቀሙ ብዙ ዳታ እንዳይቆጥሩ ለማድረግ ቀላል መፍትሄዎች!

1. በአንድሮይድ (Android) ላይ

· የዳታ ቆጣቢ (Data Saver) ያብሩ፦ ይህ በጣም ውጤታማው መንገድ ነው። አብዛኛዎቹን አፕሊኬሽኖች በዳራ ዳታ እንዳይጠቀሙ ይከለክላል፣ እርስዎ በንቃት ሲጠቀሙባቸው ብቻ ዳታ እንዲያወጡ ያስችላል።

· መንገድ፦ ቅንብሮች (Settings) > አውታረ መረብ እና ኢንተርኔት (Network & Internet) > የዳታ አጠቃቀም (Data Usage) > የዳታ ቆጣቢ (Data Saver) ይምረጡ እና ያብሩት።

· ማስተካከያ፦ እንደ መልእክት መላላኪያ ያሉ አስፈላጊ አፕሊኬሽኖች መልእክት እንዲያመጡ ከፈለጉ፣ ከData Saver ቅንብሮች ውስጥ "ያልተገደበ ዳታ" (Unrestricted data) በማድረግ ልዩ ፈቃድ መስጠት ይችላሉ።

· በየአፕሊኬሽኑ ዳራ ላይ ያጥፉ፦ የትኛዎቹ አፕሊኬሽኖች ብዙ ዳታ እንደሚያወጡ ካወቁ፣ የእነሱን ብቻ የዳራ ዳታ መጠቀም ያጥፉ።

· መንገድ፦ ቅንብሮች (Settings) > አውታረ መረብ እና ኢንተርኔት (Network & Internet) > የዳታ አጠቃቀም (Data Usage) ይሂዱ። አንድን አፕሊኬሽን በመምረጥ "የዳራ ዳታ ገድብ" (Restrict Background Data) የሚለውን ያብሩ።

2. በአይፎን (iPhone/iOS) ላይ

· ዝቅተኛ ዳታ ሞድ (Low Data Mode) ያብሩ፦ ይህ የአይፎን እትም ነው። የዳራ አፕሊኬሽኖችን እንቅስቃሴ ይገድባል እንዲሁም ራስ-ሰር ማውረዶችን እና ምትኬ (backup) ያግዳል።

· መንገድ፦ ቅንብሮች (Settings) > ሴሉላር (Cellular) > ሴሉላር ዳታ አማራጮች (Cellular Data Options) > ዝቅተኛ ዳታ ሞድ (Low Data Mode) ያብሩት።

· የዳራ አፕሊኬሽን እድሳት ያጥፉ፦ ይህ አፕሊኬሽኖች ጥቅም ላይ በማይውሉበት ጊዜ ይዘታቸውን እንዳያዘምኑ ያደርጋል።

· መንገድ፦ ቅንብሮች (Settings) > አጠቃላይ (General) > የዳራ አፕሊኬሽን እድሳት (Background App Refresh) ይሂዱ እና ያጥፉት።

#ተጨማሪ ምክሮች

· በአፕሊኬሽኖች ቅንብር ውስጥ፦ እንደ ዩቲዩብ ወይም ኔትፍሊክስ ባሉ አፕሊኬሽኖች ውስጥ የቪዲዮ ጥራትን ዝቅ ያድርጉ፣ ወይም እንደ ቴሌግራም ላሉት ራስ-ሰር ማውረድን በWi-Fi ላይ ብቻ ያስተካክሉ።

· የጉግል ፕሌይ ስቶር አውቶማቲክ አፕዴት ያጥፉ፦ አፕሊኬሽኖች በሞባይል ዳታ እንዳይዘመኑ ለመከላከል ነው።

· "ላይት" (Lite) አፕሊኬሽኖችን ይጠቀሙ፦ እንደ Facebook Lite፣ Instagram Lite ያሉት አነስተኛ ዳታ ይጠቀማሉ።

  ነው   ልዩ ባህሪያትና ለትምህርት የሚወሰድ ተግባሩ፦1/ የጊዜ አጠቃቀሙ፣2/ የሥራ ኃላፊነት ጠንቅቆ ማወቁ፣3/ ለሚያገለግለው ህዝብ ታማኝ መሆኑ፣4/ ከራሱ ይልቅ የተገልጋዩን ጥቅም ማስቀ...
21/08/2026

ነው
ልዩ ባህሪያትና ለትምህርት የሚወሰድ ተግባሩ፦
1/ የጊዜ አጠቃቀሙ፣
2/ የሥራ ኃላፊነት ጠንቅቆ ማወቁ፣
3/ ለሚያገለግለው ህዝብ ታማኝ መሆኑ፣
4/ ከራሱ ይልቅ የተገልጋዩን ጥቅም ማስቀደሙ፣
5/ ባለጉዳዮችን በእኩል ሥነ ልቦና ማየትና
6/ ለለውጥ የሚተጋ ስልችትና ተስፋ መቁረጥ
7/በዚህ ዘመን ከሥራ ተነጥለዉ ባለበት ሥራ የበዛበት ለራሱም ለህዝቡም ታማኝ የማይታበይ መሆኑ
8/ አገለግሎቱን ፈልገዉ ለተገናኙት ይህ ቢሮ ነዉ ቢሮ ዓይደለም ብለዉ የማያዉቅ ከራሱ ጥቅም የህዝቡን ጥቅም የምያስቀድም
9/ የህቤን ችግር ስከት፣ችግሮችና የችጎሮች የመፍታት መንስኤ እIኔ ብለዉ የምያምን አሳታፍ #ለእኔ አቶ ፈይሳን ልዩ ያደርገኛል።
🙏🙏🙏🙏ፋራዳው ጀግና ነህ በርታ💪💪💪

📡📡📡🛠🛠🛠 ለሚመለከተው ሁሉ 🔧🔧🔧🔧

አቶ ፈይሳ ወደ ታርጫ መሶብ አንድ ማዕከል ቢያድግ ህዝቡን የበለጠ ይጠቅማል እንድሁም ለተቋሙ ምሳሌ ይሆናል የምል አስተያየት አለኝ📢📢📢
ልሸለመዉ ይገባል ባይ ነኝ

ከሚሠራበት ዩኒቨርስቲ ጠርቶ አምጥቶ ከትምህርት ዝግጅት እና ከውስጥ potential ጋር የሚሄደውን ቦታ አለመስጠት እና መከልከል ለዳውሮ ብሔር ልምድ ሆኗል። መምህር ዘርሁን ለማን የመሰለውን...
20/08/2026

ከሚሠራበት ዩኒቨርስቲ ጠርቶ አምጥቶ ከትምህርት ዝግጅት እና ከውስጥ potential ጋር የሚሄደውን ቦታ አለመስጠት እና መከልከል ለዳውሮ ብሔር ልምድ ሆኗል።

መምህር ዘርሁን ለማን የመሰለውን ምሁር የሚቀመጥበት ቦታ ጭምር የታርጫ ከንቲባ ከልክሎ የሚሠራበት ቦታ ጀበና ቡና ቤት እና ዳቦ ቤት እንዲሆን አድርጋችሁ ይህንን የመሠለ ምሁር ቦታ አጥቶ በረንዳ ላይ እንዲቀመጥና እንዲዞር ማድረጉ ተገቢ አይደለም ፣በነገራችን ለተማሩ ሰዎች ዳውሮ አትሆንም ይህንን በውል እናውቃለን

ነፍስ ይማር ምሁር ዘርሁን ለማ

👉በአለም ውሰጥ ስኬታማ ለመሆን
👉ደደብ መሆን በቂ አይደለም ትሁትም መሆን ይኖርበታል ❗️❗️❗️

ታርጫ ከተማ ላይ አደባባይን የሰራው መሃንዲስ ጠ*ንጋራ ነው አሉ🙄
20/08/2026

ታርጫ ከተማ ላይ አደባባይን የሰራው መሃንዲስ ጠ*ንጋራ ነው አሉ🙄

 #ከ1992-2018 ዓ.ም የደዉሮ ዞን ዋና አስተዳደር የሆኑት !!
19/08/2026

#ከ1992-2018 ዓ.ም የደዉሮ ዞን ዋና አስተዳደር የሆኑት !!

ዝምታ ሌብነትን የሚያስፋፋ ነዳጅ ነው!🌿🌿🌿 #ዝምታ ሌብነትን ዋነኛ አጋርና ማበልፀጊያ የዘመኑ ነዳጅ ነው። የተደራጀ ሌብነት ሚስፋፋውና ሥር የሚሰደደው ጥፋቱ በዝምታ ሲሸፈን፣ ድምፅ የሚያሰማ...
18/08/2026

ዝምታ ሌብነትን የሚያስፋፋ ነዳጅ ነው!
🌿🌿🌿
#ዝምታ ሌብነትን ዋነኛ አጋርና ማበልፀጊያ የዘመኑ ነዳጅ ነው። የተደራጀ ሌብነት ሚስፋፋውና ሥር የሚሰደደው ጥፋቱ በዝምታ ሲሸፈን፣ ድምፅ የሚያሰማና የሚታገል አካል ሲታጣ ነው።

ሰዎች አላግባብ የተደረጉ አሰራሮችን አይተው እንዳላዩ ሲያልፉ፣ አጥፊዎች ያላንዳች ፍርሃት ድርጊታቸውን እንዲቀጥሉ መንገድ ይከፍታል።

የዜጎች ዝምታ ግልፅነትና ፍትሃዊነት በግለሰቦች መልካም ፈቃድ ብቻ እንዲወደቁ ያደርጋል። “ብናገር ምን ይለወጣል?” የሚል አስተሳሰብ በህብረተሰቡ ዘንድ እንዲሰርፅ በማድረግ የጋራ ትግል መንፈስን ያዳክማል ማለት ነዉ።

#ለዚህ ነው ሁላችንም #መናገር፣ #ማጋለጥና #እምቢ ማለት ሌብነትን እሳት የሚያጠፉ ዋና ዋና መሳሪያዎች የሚሆኑት። እያንዳንዱ ዜጋ ለፍትህና ለእውነት ድምፁን ሲያሰማ፣ የሌብነትና የሙስና ነዳጅ አልቆ ግልፅነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ስርዓት ይገነባል ማለት ነዉ ።

በደቡብ ምዕራብ የሌቦች ራስ ምታት አንድ ሰው ተገኝቷል። ዶ/ር አስራት ይባላል። ሌብነትን ስለተጠየፈ ተሳዳጅ ሆኗል።  ወንድሜ ከነዚህ ጅቦች እግዚአብሔር ይጠብቅህ‼
18/08/2026

በደቡብ ምዕራብ የሌቦች ራስ ምታት አንድ ሰው ተገኝቷል። ዶ/ር አስራት ይባላል። ሌብነትን ስለተጠየፈ ተሳዳጅ ሆኗል።

ወንድሜ ከነዚህ ጅቦች እግዚአብሔር ይጠብቅህ‼

መጽሐፍ ቅዱስንና የሕዝብ መሪን የሚያገናኛቸው ነገር መሪነት እንደ አደራና ኃላፊነት መታየቱ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ መሪ ማለት ሕዝብን ለመግዛት ብቻ ሳይሆን ሕዝቡን በፍትሕ፣ በጥበብና በቅንነት...
18/08/2026

መጽሐፍ ቅዱስንና የሕዝብ መሪን የሚያገናኛቸው ነገር መሪነት እንደ አደራና ኃላፊነት መታየቱ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ መሪ ማለት ሕዝብን ለመግዛት ብቻ ሳይሆን ሕዝቡን በፍትሕ፣ በጥበብና በቅንነት ለመምራት ኃላፊነት የተሰጠው ሰው ነው።

1. መሪ ለድሆችና ለተጨቆኑ ይቆማል

ምሳሌ 31፥8–9 ድምፅ ለሌላቸው እንዲናገሩና የችግረኞችን ፍርድ በፍትሕ እንዲያስተናግዱ ያሳስባል።

2. መሪ ፍትሕን ማስፈን አለበት

ምሳሌ 29፥4፦

“ንጉሥ በፍርድ አገርን ያጸናል፤ ጉቦ የሚወድ ግን ያፈርሳታል።”

ይህ መሪ ለግል ጥቅም ሳይሆን ፍትሕንና ሕግን በእኩልነት ማስፈን እንዳለበት ያስተምራል።

3. መሪ ጥበብ ሊኖረው ይገባል

ምሳሌ 11፥14፦

“መሪ በሌለበት ሕዝብ ይወድቃል፤ አማካሪዎች በብዛት ባሉበት ግን ደኅንነት አለ።”

ስለዚህ መሪ ብቻውን የሚወስን ሳይሆን ጥሩ አማካሪዎችን ማዳመጥ ይገባዋል።

4. መሪ ለሕዝቡ አገልጋይ ነው

ኢየሱስ በማርቆስ 10፥42–45 ታላቅ መሆን የሚፈልግ ሰው ለሌሎች አገልጋይ መሆን እንዳለበት አስተምሯል።

ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ መሪነት “ሕዝቡን እንዴት እገዛለሁ?” ብቻ ሳይሆን “ሕዝቡን እንዴት አገለግላለሁ?” የሚል ነው።

5. ሥልጣን ከእግዚአብሔር የተሰጠ ኃላፊነት ነው

ሮሜ 13፥1 ሰዎች ለሚገዙ ሥልጣናት እንዲገዙ ይናገራል፤ የሚኖረው ሥልጣንም ከእግዚአብሔር ጋር የተያያዘ መሆኑን ያሳያል።

6. መሪ ከጉቦና ከሙስና መራቅ አለበት

ዘዳግም 16፥19 ፍርድን እንዳያጣምሙ፣ ፊት እንዳያዳሉና ጉቦ እንዳይቀበሉ ያዛል።

7. መሪ ራሱን መግዛት አለበት

ምሳሌ 16፥32፦ ንዴቱን የሚገዛ ሰው ከከተማን ከሚይዝ ብርቱ ሰው ይልቅ እንደሚበልጥ ይናገራል። ስለዚህ መሪ ራስን መቆጣጠር ይገባዋል።

8. መሪ ለሥራው ተጠያቂ ነው

መጽሐፍ ቅዱስ መሪዎች ከሌሎች ይልቅ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ያሳያል። ያዕቆብ 3፥1 መምህራን የበለጠ ፍርድ እንደሚቀበሉ ይገልጻል። ይህ መሪነት በተለይ ከተጠያቂነት ጋር እንደሚያያዝ ያስተምራል።

#በአጠቃላይ

ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ጥሩ መሪ ሕዝቡን የሚያገለግል፣ ፍትሕን የሚያስፍን፣ ሙስናን የሚጠላ፣ ጥበብን የሚፈልግ እና ለድርጊቱ ተጠያቂ የሆነ መሆን እንዳለበት ያስተምራል።

Address

Bole
1000

Telephone

+251917922665

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dawuro Times posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share