05/09/2026
ገራሚ የሆንን ህዝቦች
በሚሊዮን የሚቆጠሩ የማህበረሰባችን ክፍሎች በረሀብ እና ስራአጥነት በሚሰቃዩባት አገር ለአንድ የስራ ሀላፊ በወር ከሀያ ቀን በላይ ውሎአበል ማወራረድ ምን ይሉታል። ከሶስት ከአራት አመት በፊት አላግባብ የሆኑ ውሎአበሎች ይቀራሉ ሲባል በውሎአበል አማካኝነት የሚባክነውን የሀገሪቱን ሀብት የሚረዳ እና ያም ሀብት ምን መስራት እንደሚችል የሚረዳ ሰው ተስፋው ቀላል አይሆንም። የሆነው ሁኖ እየባሰ እንጅ እየተስተካከለ አልመጣም ።
አንድ ህዝብን ለማገልገል የመንግስት የስራ ሀላፊነት የሚቀበል ሰው ሀላፊነቱን ከተቀበለ በአጭር ጊዜ አስገራሚም አስደናቂም ሀብት ሲያፈራ ጥያቄ አንስቶ ምርመራ አድርጎ አላግባብ ኪራይ ሰብሳቢነት ወይም ዝርፊያ ካለ የተዘረፈውን ሀብት ማስመለስ እና ግለሰቡን ለፍትህ ማቅረብ የመንግስት የፅድቅ ሳይሆን የግዴታ ስራው ነው። ነገር ግን አሁን ላይ የሚስተዋለው እንደዛ አደለም የዘረፈውም ሀብት አይመለስ ግለሰቡም ለፍትህ አይቀርብምም።
የመረዳዳት ፣የመተሳሰብ እና ፈሪሀ እግዚአብሔር አለባት ከምትባል አገር እኒህን እና መሰል የህግ ጥሰቶች መበራከታቸው እና መፍትሔ አለመቀመጡ በቀጣይ በአገሪቱ ብሎም በህዝቦቿ ላይ ሊያደርሰው የሚችለውን መገመት አያዳግትም። ለምሳሌ በውጭው አለም እንደምናየው በአንድ ከተማ ውስጥ የማፍያ ቡድኖች መኖር ፤ ምንም እንኳ አሁንም ቢኖር ከመጠን ያለፈ እና በገሀድ የወጣ ኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋት፤ ትልልቅ የአገር አምራች እንዲስትሪዎች እና ፋብሪካዎች በውጭ ዜጎች መያዝ፤ ሰፊው ማህበረሰብ ከድህነት ወለል በታች ሁነው ጥቂት ህሌና ቢሶች በሀብት ማማ ላይ መቆናጠጥ( wealth gab ) መፈጠር እና የመሳሰሉት ችግሮችን ያስከትላል ።
ስለዚህ ይህን በመረዳት የሚመለከተው አካል አፋጣኝ መልስ ቢሰጥ መልካም ይሆናል።