15/01/2025
jan, 17_18/ 2025,you have to see
የ6 ፕላኔቶች ሰልፍ ደረሰ
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
👉 በመላው ዓለም የምትገኙ የከዋክብት ተመልካቾች በጥር ወር በ2017 ዓ.ም. የ6 ፕላኔቶች፦
በኢትዮጵያዊ ሥነ ፈለክ አጠራር
👉 መሪህ፣ መሽተሪ፣ ዝሁራ፣ ሳተርን ወይም በውጪው አጠራር ማርስ፣ ጁፒተር፣ ቪነስ፣ ሳተርን፣ ዩራነስ፣ ኔፕቱን
ድንቅ ሰልፍን በሰማይ ላይ የምታዩበት ምርጥ ምሽት መጣ።
👉 ያለምንም መሣሪያ በቀላሉ በዐይን ማየት የምንችለው ማርስ፣ ጁፒተር፣ ቬኑስ እና ሳተርን ናቸው።
👉 ዩራኑስ እና ኔፕቱን ለመመልከት ግን ቴሌስኮፕ ያስፈልገናል።
💥 በመኾኑም ፀሓይ ከጠለቀች በኋላ ወደ ደቡብ ምዕራብ አድማስ ስንመለከት ፕላኔት ቬኑስ እና ሳተርን ተቀራርበው ሲታዩ ያለምንም መሣሪያ በዐይን ብቻ ማየት ትችላላችሁ። ከሁለቱም ብሩህ የሆነችው ደግሞ ኮከበ ምዕራብ ወይም በአቡሻሕር አጠራር አስታርቦ ሸሽ ቬነስ ስትኾን በብርሃን አነስ ብሎ የሚታየን ሳተርን ነው።
👉 በሰማይ ላይ ከፍ ብለን በዐይናችን ስንመለከት ከቬኑስ ቀጥሎ በምሽት ሰማይ ላይ ሁለተኛው ደማቅ ብርሃን በኢትዮጵያዊ የሥነ ፈለክ አጠራር መሽተሪ ወይም ፕላኔት ጁፒተር በሠውር (ታውረስ) መናዝል በቀንዶቹ መኻከል በቀዩ የሠውር ዐይን በአልዴባራን ትይዩ ደምቆ በዐይን ይታያል።
👉 በምሥራቃዊው አድማስ አቅራቢያ ደግሞ ቀዩ ፕላኔት በኢትዮጵያ የሥነ ፈለክ ሥያሜ "መሪህ" ወይም ፕላኔት ማርስ በቀይ ቀለም በድምቀት አብርቶ ለሁሉም በዐይን ይታያል።
💥 በተለይ ኀሙስ ጥር 8 (January 16) ቀይ ፕላኔቱ ወደ ምድር በጣም ቅርብ በሆነ አቀራረብ ላይ ስለሚኾን መልክአ ማርስ በፀሐይ ሙሉ በሙሉ ያበራል። በዓመቱ ውስጥ ከየትኛውም ጊዜ የበለጠ ብሩህ ይሆናል እናም ሌሊቱን ሙሉ ይታያል። ክቡራን የከዋክብት ተመልካቾችና አድናቂዎች ማርስን ለማየት እና ፎቶግራፍ ለማንሣት ይህ በጣም ጥሩው ጊዜ ነው። መካከለኛ መጠን ያለው ቴሌስኮፕ ካላችሁ በፕላኔቱ ብርቱካንማ ገጽ ላይ አንዳንድ ጥቁር ዝርዝሮችን እንድታዩ ያስችላችኋልና ምሽታችሁን ተጠቀሙበት።
👉 በቴሌስኮፕ ከኾነ በዐይን ባይተዩም ፕላኔት ዩራነስ በጁፒተር አቅራቢያ ሲኾን ኔፕቲዩን ደግሞ ወደ ቬኑስ እና ሳተርን ቅርብ በመሆን አስደናቂ ሰልፍን ይሠራሉ።
👉 ፕላኔቶች ሁል ጊዜ በሰማይ ማየት የተለመደ ነው። ብዙም ያልተለመደው ግን ስድስት ብሩህ ፕላኔቶችን በአንድ ጊዜ ማየት ነው። ይህም በየዓመቱ የማይከሰት መኾኑ ነው። በሳይንስ "አሰላለፍ" (alignment) ይባላል።
👉 በተለይ ጥር 9 እና 10 (January 17 - 18) የፕላኔት ዝሁራ ወይም ቪነስ እና የፕላኔት ዙሀል ወይም ሳተርን ግጥጥሞሽ በሰማይ ላይ (በ2 ዲግሪ አካባቢ) ማለት ምድር ላይ ኾነን ስንመለከት በኹለት የጣት ስፋቶች ርቀት ተቀራርበው ለዐይይ ይታዩናል እንደማለት ነው።
👉 ከሳይንስ ዕይታ በተጨማሪ የፕላኔት ሰልፍ እጅግ ብዙ መንፈሳዊ ዝርዝር ፍቺዎችን የያዘ ሲኾን በዐጭሩ ለመግለጽ የጠፈር ስምምነትን፣ ዐዲስ ጅምርን እና መንፈሳዊ መነቃቃትን፣ የሰማያዊ ሥርዐት ፍጹምነትን፣ የሥጋ የነፍስ የመንፈስ ጽምረታዊ ሰልፍን፣ ያንጸባርቃል። በተለይ መንገዳችንን አጽናፈ ዓለምን ወደፈጠረ ወደ የብርሃን አምላክ ወደ እግዚአብሔር እንድናደርግ ምልክት ይኾናሉ። በተለይ እያንዳንዱ ፕላኔት ያላቸው ፍቺ እጅግ በርካታ በመኾኑ በዚህ ውሱን ጽሑፍ ላይ መግለጽ አይቻልም።
በዚህ ላይ ያለውን ሰፊ መንፈሳዊ ምሳሌ ከፈለጋችሁ "ማዛሮት" የሚለውን መጽሐፌን ሳይንሳዊ ትርጉም ከፈለጋችሁ "አንድሮሜዳ 1 እና 2 መጻሕፍትን አንብቡ።
👉 እኔም በነዚሁ ቀናት ከወዳጆቼ ጋር በመኾን የሰማይ ምልከታ በማድረግ ምሽታችንን ተፈጥሮን በማድነቅ የፈጠራቸውን አምላክ በማመስገን የምናመሸ ሲሆን ለዐዳዲስ የሰማይ ተመልካቾች በቴሌስኮፕ የጁፒተርን 4 ጨረቃዎች፣ የሳተርንን ቀለበትን በማሳየት ያላቸውን ሳይንሳዊና መንፈሳዊ ጉዳዮችን ለሚመጡ ተመልካቾች በማስረዳት ምርጥ ምሽቶች ይኾኑልናል።
✍️ መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ