02/07/2025
የሆነ ሁሉም #ሼር ያድርግ ይሄን መልዕክት ( )
የትናንቱ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔዎች ግራ የሚያጋቡ ሆነው በአነጋጋሪነታቸው ቀጥለዋል፤ ጉዳዩን ለማጥራት ሰነዶችን አገላብጠን፥ ሰዎችን አናግረን መረጃዎችን ሰብስበናል፥ እነሆ፦
➡️ የውዝግቡ መነሻ....
የፋይናንስ መመሪያውን ያላከበሩ አራት ክለቦች መቻል፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ሲዳማ ቡናና መቐለ 70 እንደርታ የካቲት 15/2017 የገንዘብ ቅጣት፣ የተጫዋቾችና የአመራሮች እገዳ እንዲሁም የዝውውር ክልከላ ተወሰነባቸው
አራቱ ክለቦች ቅጣቱን በመቃወም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወሰዱት፤ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን አገደው፤ ፌዴሬሽኑ ደግሞ ደንቤ ተጥሷል ብሎ ለፊፋ አቤቱታ ላከ፤ ፊፋ ግንቦት 29/2017 በመለሰው ደብዳቤ የፌዴሬሽኑ ስሞታ ልክ ነው፥ ቅሬታችሁን ለመደበኛ ችሎት ሳይሆን ለአለም አቀፉ የስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት አቅርቡ ብሎ በክለቦቹ ላይ ወሰነ፤ ይህ ይፋ ከሆነ ከሁለት ቀናት በኋላ የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ ተካሄደ
➡️ የሲዳማ ደስታ፥ የድቻ አቤቱታ
ሰኔ 1/2017 በኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን 2-1 አሸንፎ ዋንጫ ወሰደ፤ ክልሉ ለተጫዋቾቹ የመሬት ሽልማት ጭምር ሰጠ፤ ወላይታ ድቻዎች ደግሞ የታገዱ ተጫዋቾች ተሰልፈዋል፥ ዋንጫው ለእኛ ነው የሚገባው የሚል መከራከሪያ ይዘው ለሶስት ሳምንት ያህል ቅሬታቸውን ሲያቀርቡ ቆዩ፤ በዋንጫው ጨዋታ ለሲዳማ ሁለቱን ጎሎች ያስቆጠሩት ሀብታሙ ታደሰና መስፍን ታፈሰ ከታገዱት ተጫዋቾች መካከል ይገኙበት ነበር
➡️ የፌዴሬሽኑ ውሳኔዎች
ከዋንጫው ፍፃሜ 24 ቀናት በኋላ ትናንት ሰኔ 24/2017 የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ የታገዱ ተጫዋቾችን አሰልፍሃል ብሎ ዋንጫውን ከሲዳማ ቡና ነጥቆ ለወላይታ ድቻ ሰጠ፤ ሲዳማዎች ደነገጡ፤ ወላይታ በደስታ ውላ በጭፈራ አመሸች፤ አቶ ኢሳያስ ጅራ በፕሬዝዳንትነት የሚዘውሩት ፌዴሬሽኑ ከሊጉ የሚወርድ ክለብ የለም ብሎ ጥያቄ የሚያጭር ውሳኔ ይፋ አደረገና መነጋገሪያ አጀንዳ ጨመረበት
➡️ የመጫወቻ ጠጠሮች
ፌዴሬሽኑ፥ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ የሚመሩት የፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር ከሀዋሳ ከተማ፣ ከሲዳማ ቡና፣ ከመቻልና ከመቐለ 70 እንደርታ በተጨማሪ ሌሎች ክለቦች ላይ ጠንካራ ምርመራ አላደረገም፥ ብዙ ክለቦች የፋይናንስ ህጉን አላከበሩም የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል(በዛሬው መግለጫ የሚነሳው ዋነኛው የጨዋታው ጠጠር ይህ ነው)
ስለዚህ አራቱ ክለቦች ብቻ ከተቀጡና ነጥባቸው ከተቀነሰ ሊጉን ስለሚሰናበቱ እሱን በማስቀረት ነጥብ ተቀንሶ ደረጃቸው ዝቅ እንዲልና ፎርፌ እንዲሰጥባቸው ተወሰነ፥ ነገር ግን በሊጉ ይቀጥሉ ተባለ
ቅድሚያ ወደ ከፍተኛ ሊግ የወረዱት አራቱ ክለቦች መቐለ 70 እንደርታ፣ አዳማ ከተማ፣ ስሁል ሽረና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ደግሞ ባሉበት ይቆዩ ብሎ ወሰነ
➡️ ጥያቄዎቻችን
★ የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ የተካሄደው ሰኔ 1/2017 ነበር፤ የታገዱ ተጫዋቾች መሰለፋቸው ከእለቱ ጀምሮ ሲነገር ቆይቷል፤ ከዛ በኋላ ሲዳማ ተጫዋቾቹን መሬት ሸልሟል፤ ወላይታ ድቻ ፍትህን ፍለጋ ብዙ ጠይቋል፤ 24 ቀን ሙሉ ለምን መዘግየት ተፈለገ?
ክፍል ሁለት ቀጥሎ እናቀርባለን