28/09/2023
የደመራን ሥነ ሥርዓቶች በቅደም ተከተል
ሴቶቹ በጠዋት ተነስተው ማታ ይዞ ወደ አድባር የሚወጡትን ዳቦ ይጋግራሉ፡፡ወንዶቹ በቤተሰብ ዉስጥ ባለው የወንዶች ቁጥር መሠረት ለችቦ ገለባ ያዘጋጃሉ፡፡ ለደመራ የሚሆን (ጃባ ማስቃላ) ተቆርቶ ይዘጋጃል፡፡በጭቃ ምክንያት ተዘግቶ የነበረው የከብቶች ማደሪያ(በረት) በጠዋት ይከፈታል፤ ይታደሳል፤ይጸዳል፤በዚህ ቀን ከብቶች ወደ ታደሰላቸው በረት ገብቶ ያድራሉ፡፡ማንኛውም የተሰበረ አጥር ይስተካከላሉ፤ለደመራ የተቆረጠውን ዛፍ በሚመስል ላይ (የመስቀል አበባ) እና እርጥብ ሳር ታስሮበት ከበሩ አናት ላይ ይታሰራል፡፡ከሰዓት በኋላ የከብቶች ጊቢ እና አጥር ዕድሳት ከጠጠናቀቀ በኋላ በ10 ሰዓት አከባቢ ደመራ የሚተከልበትን ቦታእና ጉቶ ይዘጋጃል፡፡ደመራ ይደመራል፡፡ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ሲሆን ከብቶች በታደሰው ቅጥር ጊቢያቸው ውስጥ ይገባሉ፡፡ ከብቶች ከገቡ በኋላ ሁሉም ሰዎች በአድባር አባት መሪነት ደመራውን እየሎከሱ ይዞ በመውጣ ይጫወታሉ፡፡ ከቤት የወጡ ሁሉም ቤተሰቦች ሴቶችና ልጆች ጠላና ዳቦ ይዞ ወደ አድባር ይመጣሉ፡፡ ይህ ስነስርዓት ማድ ማውጣት በመባል ይታወቃል፡፡ሁሉም ቤተሰብ ሚጁና ማዱን እዛ ከአደረሱና ከምርቃት በኋላ ተራ በተራ ምግቡን በሙሉ ይበላሉ፤መጠጥም ይጠጣሉ፡፡ምግ ከተበላና መተጡ ከተጠጣ በኋል ትናንሽ ልጆች፤አባቶች፤እናቶችና አዛውንቶች ወደበቤታቸው ይሄዳሉ፤ወጣቶች ግን ደመራው እስኪቃጠል ድረስ የጎቤን ጨዋታ ስጫወቱ ያመሻሉ፡፡ቤተሰቡ ከአድባር ከተመለሱ ቡኋላ ጎመን በቅቤ ተዘጋጅቶ ከሙልሙል ጋር ይበላል፡፡ ይህ ማለት የጎመን ማሰሮ ውጣ የገንፎ ማሰሮ ግባ እና በክረምት ይበሉበት የነበረው የጎመን ማሰሮን በገንፎ ማሰሮ ተለውጦ መስቀል ጥጋብ እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡
የመስቀልን ሥነ ሥርዓቶች በቅደም ተከተል
በእለቱ ከ ሌሊቱ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ የተለያዩ ፐሮግራሞች ይካዳሉ፡፡ ከንጋት ጀምሮ የኮርማ መብራት(ኢብሳ ኮርማ) ከከብቶች ግቢ ውስጥ ይበራል፡፡ ይህም በክብቶች እረኛ የሚካሄድ ሲሆን ለሰዎች ብቻ ሳይሆን ለከብቶችምየክረምት ንጋትን የሚያሳይ ሥነ ስርዓት፡፡ በስነ ስርዓቱ ላይ ላሞች ሞኢ፤ባሮዲ በማለት ይመረቃሉ/ይባረካሉ፡፡ ሁሉም ከብቶች፤ፍየሎች፤በጎች፤….ይወጡና ወደ ተዘጋጀላቸው ሳር ይሄዱና ያለምንም ገደብ ይመገባሉ፡፡ በዙህ ቀን ሁሉም እንስሳት ሊረኩ ይገባል፡፡ በዚህ ቀን ላሞች አይታለብም፤ፈረስም አይረገጥም፡፡ ላሞች ከሰዓት በኃላ እስኪመጡ ድረስ አባቶች በአብዳሪ ላይ የ እርድ ስነ ስርዓት ያካሂዳሉ፡፡ አብዳሪ በሬ ይበላል ቀሪው ይከፋፈላል፡፡ ከቀን 6 ሰዓት አከባቢ ላሚቹ በሹል ሳር ረክተው ወደ ግቢው ይገባሉ፡፡ በዚሁ ቀን ከሰዓት በኃላ ከብቶቹ ወደ ግቢው ገብተው በተሰቦቹም ከ አብዳር ወደ ቤቱ ከገቡ በኃላ ቤት ውስጥ የተለያዩ ፕሮግራሞችን ያካሂዳሉ፡፡ ለመስቀል የተዘጋጀው በግ ይታረዳል፡፡ የበጉን ደም እርጥብ ሳር በመንከር ከብቶቹ ላይ ይረጩላቸዋል፡፡ ኮርማ ጪሪ ጎዲ፤ሪማ ሃፒ ጎዲ፤ኮርሚ ባሮዱ፤ዳልቲን ያማራቱ.. በማለት ሁሉንም ከብቶች ይመርቁና ወደ ግቢ ያስገባሉ፡፡ ከዚህ ከጥሎ ያለው ፕሮግራም ዘመድ ከዘመድ፤ቤተሰብ ከጎሮቤት ጋር ቤት ለቤት በመሄድ የመብላትና መጠጣት ፕሮግራም ነው፡፡ በዚህ ቀን የሚዘጋጀው ባህላዊ ምግቦች ገንፎና ጨጨብሳ ስሆን ይህ ምግብም የሚዘጋጀው በዘመናዊ እቃዎች ሳይሆን በባህላዊ ነው፡፡ ይህ ስርዓትም (ኦኮሌ ዳቡ) ይባላል፡፡ ምግቡን ከበሉ በኃላም እርጥብ ሳር እና ቢጫውን አደይ አበባ ይይዙና
“ኦኮሌ ዳባና ሰኣፍ ናማን ኑ ዳቢ”
ዳራሪ ዳራሪ ዳራራ ባራና ሶራቴ
ካን ባራ ኤጌሬ ባሂ ሶራዱ
ዋን ዳራራ ኛቱ ሃንቱትኒ ያባዱ
በማለት ያብባሉ፡፡ ሁሉም ቡተሰብ በወይራ ከታጠነው ኤለምቱ ውስጥ የተቀመጠውን ወተት እየተቀባበሉ ጠጥተው
አናኢ አናኢ አዳማ ታኢ አናን ኢራ ሆኢ
አላልቱ ታኢ ዲቡ ናናኢ ሆኢ
ዲቡ ናናኢ ዲቡ ቦባሲሆኢ
አዮ ናጊ ባካ ሳኒ ጋሄ ሃምቱን ሂን ጋሂን
እያሉ ይመርቃሉ፡፡ ይህ ምርቃት የሚያሳየውም ኦሮሞ ለከብቶች ያለውን ፍቅርና ክብር ነው፡፡ ተመርቆ ከተበላ ከተጠጣ በኃላ ወጣቶች ክረምቱን ሙሉ ሲቀልቧቸው የነበሩትን ፈረሶች አውጥተው ኮሪኣአውን ከተሰቀለበት አውርደው የፈረስ ጉግስ ይደረጋል፡፡ ይሄ ቀን ይበልጥ የጠቀለበው ፈረስ የማን እንደሆነ የሚረጋገጥበት ቀንም ነው፡፡ አመሻሹ ላይ ሴቶች እርጥብሳርና አበባ ይዘው የአዲስ አመት መዝሙር እየዘመሩ ይጫወታሉ፡፡ ወጣት ወንዶችም ሌሊቱን ሙሉ ጎቤ እያሉ እየጨፍራሉ፡፡
Meskel 🥰✌️