DireTube

DireTube DireTube.com is the #1 Ethiopian Video Sharing Site. DireTube is an Ethiopian media and entertainment website founded on October 26, 2008.

✌️ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጋና፣ ከአይቮሪኮስትና ከኮንጎ ብራዛቪል ያስመጣቸውን አራት ተጫዋቾች በይፋ አስፈርሟል፣✌️"ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጣህ ሲሉኝ አልደሠትም፤ምክንያቱም ኢትዮጵያ ሀገሬ፤...
12/05/2026

✌️ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጋና፣ ከአይቮሪኮስትና ከኮንጎ ብራዛቪል ያስመጣቸውን አራት ተጫዋቾች በይፋ አስፈርሟል፣

✌️"ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጣህ ሲሉኝ አልደሠትም፤ምክንያቱም ኢትዮጵያ ሀገሬ፤ጊዮርጊስም ቤቴ ነው"አሠልጣኝ ሚቾ፣

👉"እኔ የጊዮርጊስ አሠልጣኝ የሆንኩት በትምህርት ዝግጅቴም፣ በልምዴም ይኸንን ኃላፊነት መሸከም ትችላለህ ተብዬ ታምኖብኝ እንጂ ውለታ ተውሎልኝ አይደለም"አሠልጣኝ ፋሲል

✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ (ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

አንጋፋውና ታላቅ የውጤታማነት ታሪክ ያለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጋና፣ ከአይቮሪኮስትና ከኮንጎ ብራዛቪል ያስመጣቸውን አራት ተጫዋቾች ዛሬ በሸራተን ኢንተርናሽናል አዲስ ሆቴል በተካሄደ ስነ-ስርዓት በይፋ አስፈርሟል።

ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀውና በሸራተን አዲስ በተከናወነው የፊርማና የትውውቅ ስነ-ስርዓት አልፍሬድ ሜንሳህ (አጥቂ)፣ኬልቪን ኤዶ ዶሴህ (ተከላካይ) ሁለቱም ከጋና፣ ካርተር አሂሮ (ተከላካይ) ከአይቮሪኮስት እና ክረስት ቶሉንጋ ከኮንጎ ብራዛቪል ወደ ክለቡ ያዘዋወራቸውን አራት ተጫዋቾች በማስፈረም ከዚህ በኋላ የክለቡ ንብረት መሆናቸውን ይፋ አድርጓል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በፊፋ የተጣለበት ተጫዋች የማዘዋወር ዕግድ መነሳቱን ተከትሎ ለክለቡ የፈረሙት አራቱም ከባህር ማዶ የመጡት ተጫዋቾች ዛሬ ግንቦት 4/2018 ዓ.ም ጀምሮ ቡድኑን በመቀላቀል ልምምዳቸውን የሠሩ ሲሆን በቀጣይ ጨዋታ የመሠለፍ ዕድል ሊያገኙ እንደሚችሉ ይጠበቃል።

በፊርማ ስነ-ስርዓቱና በትውውቅ ፕሮግራሙ ላይ አስተያየቱን የሠጠው የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ"በጣም ጭንቅ ውስጥ ቆይተን፣ያን ሁሉ መከራ አልፈን አራት ተጫዋቾችን ማስፈረም መቻላችን ትልቅ ዕድል ነው፤በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት የተለመደው ሻምፒዮናነት በመሆኑ ሁለተኛ ደረጃ እንኳን ብዙም ቦታ አይሠጠውም፤አሁን የተሻለ ደረጃ ይዘን ማጠናቀቅ አለብን"ሲል ተጫዋቾች አስመጥተው በማስፈረማቸው መደሠቱን ከመግለፁ ውጪ ይሄ እንዲሆን ያደረጉትን በሙሉ በተለይ ሚድሮክንና ዋና ስራ አስፈፃሚውን አቶ ጀማል አህመድን አመስግኗል።

"እኔ የጊዮርጊስ አሠልጣኝ የሆንኩት በትምህርት ዝግጅቴም፣በልምዴም ይሄንን ኃላፊነት መሸከም ትችላለህ ተብዬ ታምኖብኝ እንጂ ውለታ ተውሎልኝ አይደለም፤ይሄንን ቀግልፅ መናገር እፈልጋለሁ"ብሏል ፋሲል ቀአስተያየቱ መጨረሻ።

የቀድሞ የክለቡ አሠልጣኝ ሚቾ በተደጋጋሚ ከቡድኑ ጋር በመታየታቸውና በዛሬው የፊርማ ስነ-ስርዓትም ከኮቺንግ ስታፉ ጋር መድረክ ላይ በመታየታቸው በቀጣይ ቡድኑን ሊረከቡ ነው እንዴ?የሚል ጥያቄ በብዙዎች አእምሮ ውስጥ ቢፈጠርም አሠልጣኝ ሚቾ ግን "እመኑኝ በፍፁም ይሄ የማይሆን ነው፤የአራት ሀገራት ብ/ቡድንን ለማሠልጠን በሚደረግ ፉክክር በአራቱም ሾርት ሊስት (የመጨረሻ ዕቅድ) ውስጥ ነኝ"በማለት ጥርጣሬውን ወይንም የይሆናል መላምቱን የገፈፈ ቁርጥ ያለ ምላሽ ሠጥተዋል።

"ብዙ ሠዎች ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጣህ ሲሉኝ እንደዚህ አትበሉኝ ነው የምለው ምክንያቱም ኢትዮጵያ ሀገሬ ናት፤ጊዮርጊስም ቤቴ ነው"በማለትም ሰርቢያዊው ሚቾ ጨምረው ተናግረዋል።
***
👉ፎቶ ክሬዲት:- (ማርክነህ ሎሪሶ ኢንተርናሽናል ፎቶግራፈር)

♦️የአትሌት የብርጓል መለሠ የቀብር ስነ-ስርዓቱ ከነገ በስቲያ ሐሙስ ከቀኑ በ6:00 ሠዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል የሚፈፀም ይሆናል✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ (ሀትሪክ ስ...
12/05/2026

♦️የአትሌት የብርጓል መለሠ የቀብር ስነ-ስርዓቱ ከነገ በስቲያ ሐሙስ ከቀኑ በ6:00 ሠዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል የሚፈፀም ይሆናል

✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ (ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

👤ልብ በሚሰብርና በአስደንጋጭ ሁኔታ በድንገት በሞት የተለየችው የአትሌት የብርጓል መለሠ የቀብር ስነ-ስርዓት ከነገ በስቲያ ሐሙስ ከቀኑ በ6:00 ሠዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ቤተሠቦቿ፣የአትሌቲክሱ አመራሮች፣አትሌቶች፣አሠልጣኞች፣የስፖርት ቤተሠቦች በተገኙበት በክብር የሚያርፍ ይሆናል።

👤ቀደም ሲል የቀብር ስነ-ስርዓቱን ህይወቷ ከማለፉ በፊት ከአያቴ ጎን ቅበሩኝ ባለችው መሠረት ቤተሠቦቿ በሚገኙበት ጋሸና ለማድረግ ዕቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ሃሳቡ ተለውጦ ቤተሠቦቿ በተለይም ወላጆቿ፣ወንድምና እህቶቿ እንዲሁም የቅርብ ዘመዶቿ ወደ አዲስ አበባ መጥተው የአትሌቲከሱ ቤተሠብ በሚገኝበት በክብር ስነ-ስርዓቱ ቢፈፀም የሚል ውሳኔ ላይ በመደረሱ የቀብር ቦታው በአዲስ አበባ በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ከነገ በስቲያ ሐሙስ ከቀኑ 6:00 እንደሚፈፀም አስተባባሪዎቹ ለሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል ከላኩት መሠጃ ለመረዳት ተችሏል።

ነብስ ይማር!!

“አዲሲቱ አዲስ”የጥናታዊ ፅሑፍና የውይይት መድረክ ተካሄደየአዲስ አበባ ከተማን ዕድገት የቃኘና የከተሞችን አመሠራረት ያሳየ ምሁራዊ የጥናታዊ ፅሑፍ አቅርቦትና የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት ...
12/05/2026

“አዲሲቱ አዲስ”
የጥናታዊ ፅሑፍና የውይይት መድረክ ተካሄደ

የአዲስ አበባ ከተማን ዕድገት የቃኘና የከተሞችን አመሠራረት ያሳየ ምሁራዊ የጥናታዊ ፅሑፍ አቅርቦትና የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት በአድዋ ሙዚየም አዳራሽ ተካሂዷል።

ናሽናል ሚድያ አክሲዮን ማህበር (ኤን ቢ ሲ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን) ባዘጋጀው በዚህ መድረክ የአዲስ አበባን እድገትና ውበት የተመለከቱ የጥናት ወረቀቶች ቀርበዋል።የጥያቄና መልስ፣የአስተያየትና የውይይት መርሀ -ግብርም ተካሂዷል።

የናሽናል ሚዲያ አክስዮን ማህበር ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘካርያስ ብርሃኑ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።አቶ ዘካርያስ እንዳሉት ኤን ቢ ሲ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተመልካችን የሚመጥኑ፣በጥናትና ምርምር የተደገፉ ርዕሰ ጉዳዮችን አየር ላይ እያዋለ መሆኑን ገልፀው በአድዋ ሙዚየም የተካሄደው ሲምፖዚየምም የዚሁ አካል መሆኑን ገልፀዋል።የከተማነት ጉዞ ከትናንት እስከ ዛሬ እሳቤውና አፈፃፀሙ፣ ስኬትና ተግዳሮቶቹ ምን እንደሆነ በጥልቀት መስማትና መረዳት፣መጠየቅና መወያየት፣ ከምንም በላይ ደግሞ በከተማ ማደስ የታየው አስደናቂ የለውጥ አመራርና የሥራ አፈጻጸም በሌሎች የህይወትና የኑሮ ለውጥ ሥራዎች እውን የሚሆንበትን ምስጢር አውቆ ለመተግበር እንደዚህ ዓይነት መድረክ በጣም አስፈላጊና ወሳኝ እንደሆነ አቶ ዘካርያስ ብርሃኑ ገልጸዋል።ፖለቲከኞች እና አስተዳዳሪዎቹ ከሚነግሩት ባሻገር የዘርፉ ምሁራንና ተመራማሪዎች ፣ባለድርሻ አካላትና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በአንድ መድረክ ታድመው ለተሻለ የጋራ ውጤት በጋራ እንዲመክሩና እንዲወያዩ በማለም መድረኩ የተዘጋጀ መሆኑንም ኃላፊው ጨምረው ገልጸዋል።

በዕለቱ፣ አርኪቴክት ዳዊት በንቲ "ከተሞችና የአዲስ አበባ ዘመናዊ ጉዞ" በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፅሑፍ አቅርበዋል።

አርክቴክት ዳዊት በንቲ " ከተሞችና የአዲስ አበባ ጉዞ" በሚል ርዕስ ባቀረቡት የጥናት ወረቀት በዓለም ላይ የከተሞች አመሠራረት ላይ ታሪካዊ ዳራዎችን አንስተዋል።

እንደ አርክቴክት ዳዊት ስለ ከተማ እድገት ስናነሳ የመካከለኛው ዘመን ከተሞች፣የህዳሴ ዘመን ከተሞች እንደነበሩ ጠቅሰው ከ1800 አንስቶ በኢንዱስትሪ አብዮት የከተማ ተሀድሶ ይደረግ እንደነበር አንስተዋል።

የአዲስ አበባ ዘመናዊ ጉዞ በብዙ የዕድገት ደረጃዎች ማለፉን የጥናት አቅራቢው ገልፀው ይህም ታሪክ በሙዚየም ተቀምጦ አዲሱ ትውልድ ሊያውቀው ይገባል ብለዋል።

"የከተማ ትራንስፎርሜሽን እሳቤዎች፣ ትግበራ እና እንድምታዎች በአዲስ አበባ" በሚል ርዕስ ጥናት ያቀረቡት እሸትአየሁ ክንፉ( ዶ/ር ኢንጂነር) አዲስ አበባ ከንጉሡ ዘመን አንስቶ እድሳት እየተደረገላት መምጣቷን ገልፀዋል። አዲስ አበባ በቀደሙት ዘመናት ለማዘመን ነባራዊ ሁኔታዋ ባይመችም በጊዜው የመጡት መንግሥታት እንደ አቅማቸው ከተማዋን ለመቀየር መሞከራቸውን የጥናት አቅራቢው ገልፀዋል።

ከ2010 ዓ.ም በኃላ የከተሞች ጉዳይ እንደ ትልቅ ጉዳይ ተቆጥሮና ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶበት ሰፊ የማዘመን ሥራ መሠራቱን፣ይህም በቁርጠኛ አመራር የመጣ መሆኑን ጥናት አቅራቢው ገልፀዋል።

በዕለቱ የታደሙ ባለድርሻ አካላት እና ከልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተጋበዙ እንግዶችም ለጥናት አቅራቢዎቹ አስተያየት እና ጥያቄዎችን ሰንዝረዋል።

በሲንፖዝየሙ የታደሙት የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር በተያያዘ ሰፊ ማብራሪያና ገጠመኞቻቸውን ተናግረዋል።

የሲምፖዚየሙ አወያይ እና የኤን ቢ ሲ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብሩክ ከበደ በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ እንደ ሚዲያ የተሰራውን እና ሊሰራ የሚገባውን ጉዳይ አብራርተዋል። የከተማዋን ሥር ነቀል እድገትና ተያይዘው የመጡ ቱሩፋቶች የምንረዳበትንና ከህዝብ ጋር የምናገናኝበትን የመገናኛ ዘዴ (communication)በተመለከተም ሰፊ ሞያዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

"ኢዲሲቱ አዲስ" በተሰኝ ዐቢይ ርዕስ ዛሬ የተካሄደው ሲንፖዝየም ሙሉ መርሃግብር በኤን ቢ ሲ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በቅርቡ ለህዝብ እንደሚሰራጭ ታውቋል።

የዚህን ስምፖዚየም የሚድያ ማስተባበር ያከናወነው ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን (ዕዝራ እጅጉ) እንደሆነ ታውቋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሳዑዲ ዓረቢያ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው በአስጨናቂ ሁኔታ ...
12/05/2026

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሳዑዲ ዓረቢያ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በማስመልከት ለኢትዮጵያና ለሳዑዲ መንግሥታት፣ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።

ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
***
ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት እንደሚከተለው ነው፦

መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

‹‹ተዘከሩ መቁሓነ ዘከመ ተሞቃሕክሙ ምስሌሆሙ ወእለ ተሣቀዩ ከመ ዘሀለውክሙ በሥጋክሙ፡-
ከእነርሱ ጋር አብራችኋቸው እንደታሰራችሁ ሆናችሁ እስረኞችን ዐስቡ፤ መከራ የጸናባቸውንም በሥጋችሁ ከእነርሱ ጋር እንዳላችሁ ሆናችሁ ዐስቡ››
(ዕብ. 13፡3)

እውነተኛ እምነትም ሆነ ጤናማ አመለካከት የሚመዘነው መከራ ስለሚቀበሉ ሰዎች ሰምቶና አይቶ በዝምታ ባለማለፍ፤ ይልቁንም በእነርሱ ሕመም ውስጥ ራስን በማስገባት በሚሰማው ጥልቅ ኀዘን እና በሚደረገው ድጋፍ ነው፡፡ ይልቁንም በዚች ዓለም የምንኖር ለችግርና ለመከራ ቅርብ እንደመሆናችን የታሰሩትን መጎብኘት፣ የተገፉትን ማጽናናት፣ በስደት ምድር ላይ ሆነው በሞት ፍርድ የሚጨነቁትን ወገኖች ስቃይም እንደራሳችን ስቃይ በመቁጠር ስለእነርሱ ድምፅ መሆንና ማዘን ስንችል በሰማያዊው መንግሥት የማይጠፋ የጽድቅ ዋጋን እናከማቻለን፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን!

እረኛ በበረት ውስጥ ያለችው አንዲት በግ ስትጠፋ ወይም ለአደጋ ስትጋለጥ ዝም ብሎ እንደማያይ ሁሉ፣ በሳዑዲ ዓረቢያ ምድር በሞት ጥላ ሥር ሆነው ‹‹የፍትሕ ያለህ›› እያሉ የሚጮኹ፤ በጭንቀት ቀናትን የሚቆጥሩና ድምፅ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን ልጆቻችን የተሻለ ኑሮ እናገኛለን ብለው በተሰደዱበት ሀገር ሕይወታቸው በጅምላ ሊቀጠፍ እንደሆነ መረጃውን ከልዩ ልዩ መገናኛ ብዙኃን የተገነዘብን በመሆኑ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ጠቀሜታው የሰው ልጆችን ሕይወት ለመጠበቅ ነውና የኢትዮጵያ መንግሥት በከፍተኛ ደረጃ ከሚገኙ ከሳዑዲ ባለሥልጣናት ጋር በመነጋገር በግፍ የተፈረደባቸው ልጆቻችን የሞት ፍርድ እንዲነሳላቸውና ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበት መንገድ ይመቻች ዘንድ የተጀመሩ ሥራዎች ልዩ ትኩረት እንዲሰጥባቸው፤ ወገኖቻችንም በቋንቋ እጥረትና በሕግ አማካሪ እጦት ለሞት እንዳይዳረጉ ከአደራ ጭምር እናሳስባለን ፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ለሰው ልጅ የሰጠው ታላቅ ስጦታ ሕይወት ነው፤ "አትግደል" የሚለው ሕግም በማንኛውም ምድርና ቋንቋ የሚሠራ ሲሆን ፍርድ ያለ ምሕረት ከሆነ አምላካዊ ቁጣን ይጋብዛልና የሳዑዲ ባለሥልጣናት የሁለቱን ሀገራት የቆየ ታሪክና ወዳጅነት አስበው፣ በሞት ፍርድ ጥላ ሥር ላሉት ወገኖቻችን ምሕረትን እንዲያደርጉ፣ ቅጣቱንም ወደ እስራት እንዲቀይሩ በአባታዊ ርኅራኄ እንጠይቃለን ፡፡

ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችም በማያውቁት ቋንቋ እንዲሁም ባልተረዱት የሕግ ሂደት ሞት የተፈረደባቸውን ወገኖች ስቃይ ተመልክተው የፍትሕ መዛባትን እንዲቃወሙና የንጹሐንን ነፍስ እንዲታደጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በመጨረሻም፣ ማንኛውም በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ሰው ሕይወቱ ሊጠፋ አይገባምና ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን የክርስትናችን አንዱ መገለጫ የአንደኛው ወገን ሕመምን በጋራ መካፈል እንደሆነ ተረድታችሁ ወደ ፈጣሪያችን በጸሎት እንድትማጸኑ፤ መላው ኢትዮጵያውያንም ለመፍትሔው የበኩላችሁን ጥረት እንድታደርጉ ስንል አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን።

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
© የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሰጠው መመሪያ መሰረት ሁሉም የባንክ ደንበኞች ነባር ሂሳባቸውን በቀጣይነት ለማንቀሳቀስ የባንክ መረጃቸውን ከብሄራዊ መታወቂያ ካርዳቸው(Fayda Id) ጋር እያስተሳ...
12/05/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሰጠው መመሪያ መሰረት ሁሉም የባንክ ደንበኞች ነባር ሂሳባቸውን በቀጣይነት ለማንቀሳቀስ የባንክ መረጃቸውን ከብሄራዊ መታወቂያ ካርዳቸው(Fayda Id) ጋር እያስተሳሰሩ ይገኛሉ፡፡
ስለሆነም እርስዎም እስከ አሁን ድረስ ይህንን ካላደረጉ ካሉበት ሆነው ይህንን ማስፈንጠሪያ https://fayda.addisbank.com.et በመጠቀም ወይም በአቅራቢያዎ ወደሚገኙ ቅርንጫፎቻችን ጎራ በማለት ይህንን ተግባር እስከ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንዲያከናውኑ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

አዲስ ባንክ- ለስኬትዎ የታመነ

ለወዳጅ ዘመድ ያጋሩ!
Website- (http://www.addisbanksc.com/)
Telegram- (t.me/AddisBank_sc)
Facebook- (http://facebook.com/addisinternationalbank)
Linked in- (https://www.linkedin.com/company/addis-international-bank/)

አትሌቷ ዛሬ ማለዳ በጃንሜዳ ልምምድ እየሰራች ወድቃ ህይወቷ አለፈዝነኛዋ የረጅም ርቀት ሯጭ የብርጓል መለሰ ዛሬ ግንቦት 4/2018 ዓ.ም ማለዳ በጃንሜዳ ልምምድ እየሰራች ሳለ በድንገት ወድቃ...
12/05/2026

አትሌቷ ዛሬ ማለዳ በጃንሜዳ ልምምድ እየሰራች ወድቃ ህይወቷ አለፈ

ዝነኛዋ የረጅም ርቀት ሯጭ የብርጓል መለሰ ዛሬ ግንቦት 4/2018 ዓ.ም ማለዳ በጃንሜዳ ልምምድ እየሰራች ሳለ በድንገት ወድቃ ነው ህይወቷ ማለፉ ተሰማ። አስክሬኗ በአሁኑ ሰዓት ለምርመራ ወደ ምኒልክ ሆስፒታል ተወስዷል።

እ.ኤ.አ በ2015 በኮንጎ ብራዛቪል በተካሄደው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ሀገሯን ወክላ በግማሽ ማራቶን የነሃስ ማራቶን ያመጣችው አትሌቷ በዛው ዓመት በአሜሪካ ቺካጎ ማራቶን 2ኛ መውጣቷ ይታወሳል። በ2018 ደግሞ በቻይና ሻንጋይ ማራቶን 2:20.37 በሆነ ጊዜ ከሶስት ዓመታት በፊት በሀገሯ ልጅ ትዕግስት ቱፋ ተይዞ የነበረውን የቦታውን ሪከርድ (2:21.52) ከአንድ ደቂቃ በላይ በማሻሻል ማሸነፏ ይታወሳል።

በ2022 በፖርቹጋል ሊዝበን ግማሽ ማራቶን 1:07.18 በሆነ ጊዜ የቦታውን ሪከርድ ሰብራ አሸንፋለች። ባለፈው ዓመት በተካሄደው የፍራንክፈርት ማራቶን 2:2047 በሆነ ሰዓት 2ኛ ወጥታ ነበር። በ2018 በዱባይ ማራቶን 2:19.36 የገባችበት በማራቶን የግል ምርጥ ሰዓቷ ነው።

የፊታችን ግንቦት 16 በካናዳ በሚካሄደው የኦታዋ ማራቶን ከሚሳተፉት 12 ሴት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል አንዷ የነበረችው ጀግናዋ አትሌት የብርጓል መለሰ ለአሸናፊነት የሚረዳትን ጠንካራ ልምምዷን በመስራት ላይ ሳለች ነው ዛሬ ማለዳ በድንገት ወድቃ ህይወቷ ያለፈው።

የብርጓል ባለትዳርና የሁለት ልጆች እናት ነበረች። አስክሬኗ ነገ ጠዋት ወደ ቤተሰቦቿ ወደ ወሎ ሽኝት ይደረግለታል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ባለፉት 10 ወራት ከ600 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ -  ከ23 ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው  የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋልጉምሩክ ኮሚሽን በ2018 ...
12/05/2026

የጉምሩክ ኮሚሽን ባለፉት 10 ወራት ከ600 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

- ከ23 ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል

ጉምሩክ ኮሚሽን በ2018 የበጀት ዓመት በ10 ወራት 600 ነጥብ 23 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ።

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ(ዶ/ር) ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ በ2018 በጀት ዓመት አስር ወራት 598 ነጥብ 91 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 600ነጥብ23 ቢሊዮን መሰብሰብ ችሏል፡፡

አፈፃፀሙ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 257 ነጥብ 82 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡

ለገቢ አፈጻጸሙ እድገት የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙና ኮሚሽኑ በተከታታይ የወሰዳቸው የሪፎርም ሥራዎች ተጠቃሽ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ባለፉት 10 ወራት ውስጥ ከ23 ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ገቢና ወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን መቆጣጠር መቻሉንም ጠቁመዋል።

በቁጥጥር ስር ከዋሉ የኮንትሮባንድ እቃዎች ውስጥ ኤሌክትሮኒክስ ጥራታቸው ያልተረጋገጠ መድኃኒቶች የተለያዩ ልብሶች የምግብና መጠጥ እንዲሁም የመኪና መለዋወጫ፣ ሲጋራና የግንባታ እቃዎች ይገኙበታል ብለዋል።

ማዕድንና የግብርና ምርቶች እንዲሁም የቀንድ ከብቶች በህገወጥ መንገድ ከሀገር ውስጥ ወደ ውጪ ሊወጡ ሲሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ጠቁመዋል።

“ግሮው ኢትዮጵያ 2026" የተሰኘ የመጀመሪያ አገር አቀፍ የሰብል ጥበቃና ማዳበሪያ ኤክስፖ ሊካሄድ ነው“ግሮው ኢትዮጵያ 2026" የተሰኘ የመጀመሪያ አገር አቀፍ የሰብል ጥበቃና ማዳበሪያ ኤክ...
12/05/2026

“ግሮው ኢትዮጵያ 2026" የተሰኘ የመጀመሪያ አገር አቀፍ የሰብል ጥበቃና ማዳበሪያ ኤክስፖ ሊካሄድ ነው

“ግሮው ኢትዮጵያ 2026" የተሰኘ የመጀመሪያ አገር አቀፍ የሰብል ጥበቃና ማዳበሪያ ኤክስፖ ከግንቦት 14 – 16, 2018 ዓ.ም (May 22- 24, 2026) በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽንና ንግድ ማዕከል እንደሚካሄድ የኤክስፖው አዘጋጅ ዊ‑ሊንክ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በዛሬው እለት በግዮን ሆቴል በሰጠው መግለጫ አስታውቋል::

ኤክስፖው የግብርና ግብአት አምራቾች፣ አስምጪዎች፣ አቅራቢዎችን፣ አከፋፋዮች፣ አርሶ አደር ማህበረሰብን፣ በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ ኢንቨስተሮችን፣ የሪጉላቶሪ፣ የምርምርና የስልጠና ተቋማትን ለማቀራረብ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

'GROW ETHIOPIA 2026' በሰብል ጥበቃ (ፀረ-ነፍሳት፣ ፈንገስ ማጥፊያዎች፣ አረም ማጥፊያዎች፣ ባዮ-ተባይ ማጥፊያዎች)፣ ልዩ ማዳበሪያዎች፣ ባዮስቲሙላንቶች እና ትክክለኛ የግብአት አጠቃቀም ቴከኖሎጂዎች ላይ ያሉ ቴክኖሎጂዎችንና የቅርብ ጊዜ ግኝቶችን ለማሳየት ያለመ ሆኖ መምጣቱና ከላይ የተዘረዘሩት አካላትን የሚያቀራርብ በመሆኑ ፋይዳው እጅግ ከፍተኛ መሆኑን የዊ‑ሊንክ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር እንዳለ ገብሬ ገልጸዋል::

ዶ/ር እንዳለ አክለውም ይህ ኤክስፖ አርሶ አደሮች ከግብርና ግብአቶች አምራቾችና አስመጪዎች ጋር በቀጥታ እንዲገናኙ የሚያስችል አንድ ማዕከል በመሆን የሚያገለግል በመሆኑ፣ ትክክለኛ የምርቱ አስመጪዎችን በመቅረብ ትክክለኛ እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ግብአቶች እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ብለዋል።

የዊ‑ሊንክ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ምክትል ስራ አስኪያጅ የሆኑት ዳንኤል ጥላሁን በበኩላቸው በኤክስፖው ዋና ዋና የጸረ-ተባይ ፥ የጸረ-ፈንገስ ፥ የጸረ-አረም እና የማዳበሪያ አስመጪዎች እና አከፋፋዮች ምርታቸውን በማቅረብ በኤግዚቢሽኑ እንደሚሳተፉና የኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ የመካናይዝድ እርሻዎች፥ አርሶ አደሮች፣ የግብርና ግብአት አከፋፋዮች (agrodealers)፣ የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮች፣ የምርምር እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሳተፉ ተናግረዋል::

በተጨማሪም ከ10,000 በላይ ጎብኚዎችም ይታደሙበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል::

ከኤክስፖው ጎን ለጎን ከግብርና ተቋማት፣ ከዩኒቨርሲቲ፣ ከምርምር ተቋማት፣ ከግሉ ሴክተር፣ ወዘተ የሚሳተፉበት የፓናል ውይይቶች፣ ሲሚናሮች የተሻሻሉ አሰራር ተሞክሮዎች እንደሚቀርቡ የተገለፀ ሲሆን በግብርና ግብአት አቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ያለውን ክፍተት ለመሙላት እና ወደተሻለ ቁመና ለማምጣት ታስቦ የተዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡

ዊ‑ሊንክ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሀገሪቱ የግብርና ግብአቶች አቅርቦት በተሻለ መልኩ እንዲሳለጥ ለማመቻቸት የተመሰረተ ነው::
#ድሬትዩብ

የዲግሪ ሰርተፊኬት ህትመት በአንድ ማዕከል ብቻ ሊከናወን ነው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች የዲግሪ ሰርተፊኬት ህትመት በአንድ ማዕከል ብቻ ሊከናወን ነው አለ ትምህርት ሚኒስቴር።በሚኒ...
12/05/2026

የዲግሪ ሰርተፊኬት ህትመት በአንድ ማዕከል ብቻ ሊከናወን ነው

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች የዲግሪ ሰርተፊኬት ህትመት በአንድ ማዕከል ብቻ ሊከናወን ነው አለ ትምህርት ሚኒስቴር።

በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፤ አሰራሩ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ለመከላከል ያለመ ነው፡፡

ከዚህ በፊት ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጨረታ ባሸነፈ ድርጅት በኩል የተማሪዎችን የትምህርት ማስረጃ የሚያሳትሙበት አሰራር ለሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አጋላጭ ሆኖ ቆይቷል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎቻቸውን ዲግሪ በአንድ ማዕከል ብቻ እንዲያሳትሙ ይደረጋል ነው ያሉት፡፡

አዲሱ ዲግሪ ታትሞ እስኪደርስ ድረስ ትምህርት ሚኒስቴር ዲግሪ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የድጋፍ ደብዳቤ እንደሚጽፍ ገልጸው፤ ህትመቱ በዚህ ዓመት እንደሚጀምር ጠቁመዋል።

የሚታተመው ሰርተፊኬት የደህንነት መለያ መስፈርቶችን እንደሚያሟላ ገልጸው፤ ልዩ መለያ ኮድ (QR Code) እና ሴሪያል ቁጥርን ጨምሮ ሌሎች መለያዎችን ያካተት እንደሚሆን ገልጸዋል።

በ2017 ዓ.ም የተመረቁ ተማሪዎችን ጨምሮ ከዚህ በኋላ የሚመረቁትም ሙሉ በሙሉ በአዲሱ ስርዓት መሰረት በአንድ ማዕከል የሚታተመውን ዲግሪ ብቻ እንዲወስዱ ይደረጋሉ ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ከ2017 ዓ.ም በፊት ተመርቀው ነገር ግን ዲግሪያቸውን ያልወሰዱ ተማሪዎች በአዲሱ አሰራር ብቻ እንደሚስተናገዱ አመልክተዋል።

ከዚህ በፊት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲሰጥ የነበረው ጊዜያዊ የትምህርት ማስረጃ (Temporary Degree) አሰጣጥ በነበረበት እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

አሁን ላይ ከ160 በላይ በሚሆኑ የፌዴራል ተቋማት ላይ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የማጥራት ስራ እየተከናወነ እንደሆነ አንስተው፤ በቀጣይ በክልሎች እና በግሉ ዘርፍ የማጥራት ስራው እንደሚቀጥል አመልክተዋል።
(ኤፍ ኤም ሲ)

ስምንት አንጋፋ የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አገኙየባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፤ በምርምር፣ በ...
12/05/2026

ስምንት አንጋፋ የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አገኙ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፤ በምርምር፣ በመማር ማስተማር እና በከፍተኛ የማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ላቅ ያለ አስተዋፅኦ ላበረከቱ 8 (ስምንት) ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት (Full Professorship) ማዕረግ እድገት መፍቀዱን በታላቅ ደስታ ይገልጻል።

እነዚህ ምሁራን ለዓመታት በእውቀት ሽግግር እና በሳይንሳዊ ምርምር ዘርፍ ላሳዩት ትጋትና ለሀገራዊ ዕድገት ላበረከቱት የማይተካ ሚና ይህ ከፍተኛ የአካዳሚክ ማዕረግ የሚገባቸው መሆኑ በቦርዱ ተረጋግጧል።

የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያገኙ ምሁራን ዝርዝር፡
1. ፕሮፌሰር አባይነህ ሙንሼ አብተው – በባዮሜዲካል ሳይንስ (Biomedical Sciences)
2. ፕሮፌሰር አያሌው ወንዴ መለሰ – በውሃ አካላት ኢኮሎጂ እና አስተዳደር (Wetland (Aquatic) Ecology and Management)

3. ፕሮፌሰር ዳዊት አስራት ጌታሁን – በ Educational Psychology
4. ፕሮፌሰር ደሳለኝ እጅጉ ብርሐኔ – በዱር እንስሳት ኢኮሎጂ እና ጥበቃ (Wildlife Ecology & Conservation)

5. ፕሮፌሰር ፍቅረሰላም ጋረድ መንግሥቱ – በኮሙኒኬሽን ኢንጂነሪንግ (Communication Engineering)
6. ፕሮፌሰር ጌታሁን የማታ ሉሌ – በዕፅዋት ኢኮፊዚዮሎጂ (Plant Ecophysiology)

7. ፕሮፌሰር ጌትነት ታምሩ ጥግነህ– በ Inorganic Chemistry
8. ፕሮፌሰር ማተብ ታፈረ ገድፈው – በትምህርት ፖሊሲ እና አመራር (Education Policy and Leadership)

ዩኒቨርሲቲያችን ለተከበራችሁ ፕሮፌሰሮች፣ ለቤተሰቦቻችሁ እንዲሁም ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ "እንኳን ደስ አላችሁ" እያለ፤ ወደፊትም በምርምርና በፈጠራ ስራዎቻችሁ የዓባይ ጓዳ የሆነችውን እናት ዩኒቨርሲቲያችሁንና ሀገራችሁን በበለጠ እንድታገለግሉ ይመኛል።
(ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ )

ጠ/ሚ ዐብይ ናይሮቢ ናቸውጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባኤ ላይ ለመታደም ዛሬ ጠዋት ናይሮቢ ኬንያ ገብተዋል።
12/05/2026

ጠ/ሚ ዐብይ ናይሮቢ ናቸው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባኤ ላይ ለመታደም ዛሬ ጠዋት ናይሮቢ ኬንያ ገብተዋል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when DireTube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to DireTube:

Share