24 ሰዓት Online

24 ሰዓት Online ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃወች አዝናኝና አስተማሪ የሆኑ ልጥፎች ይጋሩበታል!!

​🕒 24 ሰዓት Online
🔥 ትኩስ መረጃዎች | አነጋጋሪ ጉዳዮች | ድንቅ እውነታዎች
🤝 የሁላችሁም ገጽ!
​---
​🌍 24/7 Updates: Trending News, Viral Stories & Incredible Facts.
✨ Welcome to the community!

05/03/2026

1 ሊትር ቤንዚን
በብላክ በአካባቢያችሁ
ስንት ነው?

ዝነኛው ኢትዮጵያዊ የፊልም ባለሞያ ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ በበርሊን ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ተሸለሙ።ኃይሌ ገሪማ በጀርመን መዲና በርሊን ትናንት ማክሰኞ በተካሄደ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስ...
18/02/2026

ዝነኛው ኢትዮጵያዊ የፊልም ባለሞያ ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ በበርሊን ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ተሸለሙ።
ኃይሌ ገሪማ በጀርመን መዲና በርሊን ትናንት ማክሰኞ በተካሄደ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል (Berlinale) ላይ ለፊልም ጥበብ ዕድገት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለሙያዎች የሚሰጠው «የበርሊን ካሜራ» (Berlinale Camera) የክብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ኃይሌ ገሪማ በአፍሪካ ታሪክ፣ በቅኝ አገዛዝ፣ በማንነት እና በማኅበራዊ ፍትህ ላይ በሚያተኩሩ ሥራዎቻቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ ዳይሬክተር፣ አዘጋጅ እና መምህር ናቸው።
ለበርካታ አስርት ዓመታት በአሜሪካ በሚገኘው ሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ የፊልም ፕሮፌሰር በመሆን በርካታ ወጣት የፊልም ባለሙያዎችን ማፍራታቸው የሚነገርላቸው ኃይሌ ገሪማ በተለይም በአፍሪካ እና በተቀረው ዓለም የሚኖሩ ጥቁር ሕዝቦችን ታሪካዊና ፖለቲካዊ ተሞክሮዎች የሚዘክሩ «ሰንኮፋ» እና «ጤዛ» በተሰኙ ፊልሞቻቸው አድናቆት አትርፈዋል።
በርሊን ከተማ ውስጥ በሚገኘው ዴልፊ ፊልም ፓላስት በተካሄደ ልዩ የፊልም ማሳያ መርኃ ግብር ላይ ፕሮፌሰር ኃይሌ «ጥቁር አንበሶች ፤ የሮማ ተኩላዎች» (Black Lions – Roman Wolves) የተሰኘውን አዲሱን የፊልም ፕሮጀክታቸውን አስተዋውቀዋል።
አዲሱ የፊልም ሥራቸው ጣሊያን ቅኝ ለመግዛት ያደረገችው ሙከራ በኢትዮጵያ ላይ ያስከተለውን ተጽዕኖ፣ ሙከራውን ለማክሸፍ የተደረገውን ተጋድሎ እና የታሪክ ትውስታን የሚዳስስ እንደሆነ ተገልጿል።
ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ ዓለም አቀፍ ክብር ያጎናጸፋቸው ሽልማት የተበረከተላቸው ለነጻ የሲኒማ ጥበብ ላላቸው የዕድሜ ልክ ቁርጠኝነት፣ ታሪክን በፊልም የመተረክ ብቃታቸው፣ እንዲሁም የአፍሪካውያንን ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ እንዲሰማ ላደረጉት ከፍተኛ ጥረት እውቅና ለመስጠት ነው ተብሏል። ሽልማቱ ፕሮፌሰር ኃይሌ ከተጎናጸፉት ክብር ባሻገር ለኢትዮጵያ እና ለመላው አፍሪካ የፊልም ኢንዱስትሪ ትልቅ ኩራት የሚሆን ነው። በተጨማሪም ዓለምን የሚያስተምር እና የሚያነቃቃውን የኃይሌ ገሪማን የጥበብ ጉዞ በድምቀት የዘከረ ሆኗል።
DW

Facebook ከተመሰረተ 22 ዓመት ሆነው እኛ ደግሞ 12 አመቱን ከ facebook ጋር ነበርን!!እናንተስ ከ facebook ጋር ስንት አመት ቆያችሁ?
04/02/2026

Facebook ከተመሰረተ 22 ዓመት ሆነው እኛ ደግሞ 12 አመቱን ከ facebook ጋር ነበርን!!
እናንተስ ከ facebook ጋር ስንት አመት ቆያችሁ?

ምን እየሞከራችሁ ነው?
03/02/2026

ምን እየሞከራችሁ ነው?

እየሞከርኩ ነው የሚለውን የኮሜዲያን ያሲኖ አጭር ቁምነገር አዘል ቀልድ ብዙ ተከራዮች ቀልዱን በአድናቆት የተቀባበሉት ሲሆን በጣም በርካታ አከራዮችም አካራዩም እየሞከረ ነው መክፈል ካልቻልክ ...
02/02/2026

እየሞከርኩ ነው የሚለውን የኮሜዲያን ያሲኖ አጭር ቁምነገር አዘል ቀልድ ብዙ ተከራዮች ቀልዱን በአድናቆት የተቀባበሉት ሲሆን በጣም በርካታ አከራዮችም አካራዩም እየሞከረ ነው መክፈል ካልቻልክ የሰው ቤት ልቀቅ አከራዩም ብዙ ወጭ አለበት ሲሉ ተደምጠዋል!!
የናንተ አስተያየትስ ምንድን ነው?

30/01/2026

ሰላም
ለሃገራችን

ባካሪ ሳኛ አዲስ አበባ ገባ
25/01/2026

ባካሪ ሳኛ አዲስ አበባ ገባ

አንዳንዱ አካባቢ ይገርማል 😍
22/01/2026

አንዳንዱ አካባቢ ይገርማል 😍

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ታሪካዊውን ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ገዛ​በኢትዮጵያ ቀዳሚው ባለሀብት የሼህ መሐመድ ሁሴን ዓሊ አላሙዲ ንብረት የሆነው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ አንጋፋውን ዋቢ ሸበሌ...
22/01/2026

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ታሪካዊውን ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ገዛ
​በኢትዮጵያ ቀዳሚው ባለሀብት የሼህ መሐመድ ሁሴን ዓሊ አላሙዲ ንብረት የሆነው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ አንጋፋውን ዋቢ ሸበሌ ሆቴልን መግዛቱ ተበሰረ። የግዢ ስምምነቱን የሚድሮክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ እና የሆቴሉ የቦርድ ፀሐፊ ልዑል በዕደማርያም መኮንን ተፈራርመዋል።
​የታቀዱ ዋና ዋና ለውጦች
​ደረጃውን የጠበቀ እድሳት፦ ሆቴሉ በ60 ዓመታት ታሪኩ ውስጥ የነበረውን ይዘት ጠብቆ፣ በዓለም አቀፉ የማርዮት (Autograph Collection by Marriott) የጥራት ደረጃ እንዲታደስ ይደረጋል።
​ለዓለም አቀፍ ጉባዔ ዝግጅት፦ ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው 32ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ እንግዶች ምቹና ዘመናዊ ማረፊያ እንዲሆን ታቅዷል።
​ታሪካዊ እሴት፦ በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን ተገንብቶ በደርግ የተወረሰው ይህ ሆቴል፣ በ2000ዎቹ መጀመሪያ ላይ ለንጉሣዊ ቤተሰቡ ወራሾች ተመልሶ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ ግል ይዞታነት ተዛውሯል።
​"የሆቴሉን ታሪክ ጠብቆ በማዘመን ለትውልድ ለማሻገር በመስማማቱ ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ምስጋና ይገባዋል።" — ልዑል በዕደማርያም መኮንን

🛑 "ዱካክ" ወይስ ሳይንሳዊው "Sleep Paralysis"? በህልምና በውል መሃል ያለው አስፈሪው ደቂቃ! 👻🛌​በእኩለ ሌሊት በከባድ ጭንቀት ነቅተው፤ በደረትዎ ላይ የሆነ ግዙፍ ነገር ተጭኖዎ...
22/01/2026

🛑 "ዱካክ" ወይስ ሳይንሳዊው "Sleep Paralysis"? በህልምና በውል መሃል ያለው አስፈሪው ደቂቃ! 👻🛌

​በእኩለ ሌሊት በከባድ ጭንቀት ነቅተው፤ በደረትዎ ላይ የሆነ ግዙፍ ነገር ተጭኖዎት ያውቃል? ለመጮህ ቢሞክሩ ድምፅዎ አይወጣም፣ እጅና እግርዎን ለማንቀሳቀስ ቢታገሉ ሰውነትዎ እንደ ድንጋይ ይዝላል...

​ይህ በሀገራችን "ዱካክ" ተብሎ የሚታወቀው አስፈሪ ክስተት፣ በሳይንሱ ደግሞ "Sleep Paralysis" (የእንቅልፍ ሽባነት) ይባላል።

​ይህ ሁኔታ የሚፈጠረው አዕምሯችን ከእንቅልፍ ሲነቃ፣ ሰውነታችን ግን ገና ከእንቅልፍ ዑደት (REM Sleep) ሙሉ ለሙሉ ሳይወጣ ሲቀር ነው።

​አዕምሮ ነቅቷል፦ አካባቢያችሁን ታያላችሁ፣ ትሰማላችሁ።

​ጡንቻዎች ተኝተዋል፦ ጡንቻዎቻችሁ ገና በ"ፓራላይዝ" ሁኔታ ውስጥ ስለሆኑ ትዕዛዝ አይቀበሉም።

​ቅዠት (Hallucination)፦ በዚህ ቅጽበት የሌለ ድምፅ መስማት ወይም አንድ ሰው ክፍል ውስጥ ያለ (ጥቁር ጥላ) ሊመስለን ይችላል።

​ማስታወሻ፦ ሁኔታው እጅግ አስፈሪ ቢሆንም፣ በጤና ላይ የሚያመጣው ምንም አይነት አካላዊ ጉዳት የለም።

​ዱካክን ለመቀነስ ወይም ለማስወገድ እነዚህን ነጥቦች ይሞክሩ፦

​የአተኛኘት ዘይቤ፦ በብዛት በጀርባ ተንጋሎ መተኛት ለዱካክ ያጋልጣል። ስለዚህ በጎን መተኛትን ይልመዱ።

​እንቅልፍ ማስተካከል፦ በቂ እንቅልፍ አለማግኘት እና ከፍተኛ ድካም ለዚህ ዋነኛ መንስኤዎች ናቸው።

​መረጋጋት፦ ሁኔታው ሲፈጠር "አሁን ያልፋል" ብሎ ራስን ማረጋጋት የጭንቀቱን መጠን ይቀንሳል።

​እስኪ የእርስዎን ገጠመኝ ያጋሩን! "ዱካክ" ሲይዝዎት እንዴት ነው የሚያልፉት?

በከባድ ትግል? 😰

​በጸሎት? 🙏
ወይስ "እስኪ ይለቀኝ" ብለው ተረጋግተው በመጠበቅ? 😅
ሀሳብዎን ኮመንት ላይ ያጋሩን! 👇🏽

Address

Adwa
Addis Ababa
0000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when 24 ሰዓት Online posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to 24 ሰዓት Online:

Share