30/07/2025
✍️ “ድንግል ሆይ ባማረ በተወደደ ነገር ሁሉ መሰልሁሽ ምስጋናሽን ግን ለመፈፀም አልቻልኩም፤ እግዚአብሔርን ባመሰገንሁ ጊዜ ባንቺ ለስሙ ምስጋና አቀርባለሁ፤ በስምሽም ጸሎቴን በጸለይሁ ጊዜ ጸሎቴን ለልጅሽ አቀረብሁ፤ ዳግመኛም ውዳሴሽን ወደማወቅ ባህር ልዋኝ ወደድሁ ወደ ክብርሽ ገናንነት ወደብ እደርስ ዘንድ ደከምሁ ያንዲቷን ማእበል ሞገድ ያህል ስንኳን አላለፍሁም፤ ወደ ፅርሀ አርያም ጠፈር ለመድረስ የሚቻለው ማነው? ከምድር በታች ወዳለው ባህር መሰረትስ መዋኘት ማን ይችላል? ድንግል ሆይ ክብርሽን ገናንነትሽን ጠንቅቆ መናገር የሚቻለው ማነው? እኛስ የአባቶቻችን ልጆች ነንና በእምነት ሆነን ድንግል ሆይ ክብርሽን ማን ይናገር ዘንድ ይችላል? ገናንነትሽን ማን መመጠን ይችላል?"
✍️ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ