Wazema Communication And Events

Wazema Communication And Events Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Wazema Communication And Events, Arts and entertainment, Addis Ababa.

24/03/2019

በሚሊዮን የሚቆጠሩ የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን የይለፍ ቃል 20 ሺህ በሚሆኑ ፌስቡክ ውስጥ በሚሰሩ ሰዎች ይታወቁ እንደነበር ይፋ ሆነ።

የኢንተርኔት ደህንነት ተመራማሪው ብሬይን ክሬብስ ፌስቡክ የደንበኞችን መረጃ በመደበቅ ረገድ ችግር እንዳለበት አጋልጧል። በጥናቱ መሰረት 600 ሚሊዮን የሚሆኑ የደንበኞች የይለፍ ቃል ምንም አይነት ጠጥበቃ ሳይደረግላቸው እንዲሁ ተጽፎ ለማንም ግልጽ በሆነ መልኩ እንደሚገኝ ተናግሯል።

እነዚህ የይለፍ ቃሎች ከፈረንጆቹ 2012 ጀምሮ የተከፈቱ ናቸውም ብሏል። ፌስቡክ ይህን ተከትሎ ሁሉንም የይለፍ ቃሎች በአንድ ቋት ውስጥ ለማስቀመጥ እየሰራሁ ነው በማለት ለማስተባበል ሞክሯል።

ክሬብስ ከፌስቡክ ሰራተኛ አገኘሁት ባለው ተጨማሪ መረጃ መሰረት፤ እንደዚህ አይነት ችግሮች ያጋጠሙት መተግበሪያውን የሚያበለጽጉት ሰዎች መጀመሪያውኑ የይለፍ ቃሉ ወደ ሚስጥራዊ ኮድ እንዳይቀየር አድርገው ስለሚያዘጋጁት ነው ብሏል።

የፌስ ቡክ ኢንጂኔር ሰኮት ሬንፍሮ እንደሚሉት ችግሮቹ ምን እንደሆኑ ለመለየት ጥረት አድርገናል መፍትሄውንም እናመጣለን ብለዋል።

መረጃው እንደሚያሳው አብዛኛዎቹ የዚህ ችግር ተጋላጮች የፌስቡክ ላይት ተጠቃሚዎች ናቸው። ኩባንያው ለሮይተርስ በሰጠው ቃል መሰረት "በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የፌስቡክ ላይት ተጠቃሚዎች፣ በአስር ሚሊዮን የሚቆጠሩ የሌላ ፌስቡክ ተጠቃሚዎችና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የኢንስታግራም ተጠቃሚዎች የችግሩ ተጋላጮች ናቸው።"

ቢሆንም ግን ቀጥሎ ሊመጣ የሚችለው መፍትሄ የይለፍ ቃልን እንደገና መቀየር ሊሆን ይችላል ተብሏል። የፌስቡክ መግቢያ (Log in) ደህንነቱ የተጠበቀ አይደለም በማለት ባለፉት ጊዜያት የተለያዩ የዜና ምንጮች ሲተቹት ቆይተዋል። መስከረም ወር ላይ የ50 ሚሊዮን ፌስቡክ ተጠቃሚዎች መረጃ ተጋላጭ ሆኖ እንደነበርም ይታወሳል።

በ2018 መጀመሪያ አካባቢም በሚሊዮን የሚቆጠሩ የፌስ ቡክ ተጠቃሚዋች መረጃ በካምብሪጅ የመረጃ ሳይንስ ኩባንያ እየተጠና መሆኑንም ፌስቡክ ገልጾ ነበር።

Meet Tewodros Abuhay! He is a taxi driver who provides free ride whenever he comes across pregnant women to wherever the...
03/02/2019

Meet Tewodros Abuhay! He is a taxi driver who provides free ride whenever he comes across pregnant women to wherever the woman want to go! Tewodros was given a certificate recognition from SPHMMC!

03/02/2019

ሻለቃ ኃይሌ ወደ ኃላፊነቱ እንዲመለስ ተጠየቀ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ለሁለት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ሲመራ ቆይቶ ከወራት በፊት ከኃላፊነቱ መልቀቁን ያስታወቀው ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ ወደ ኃላፊነቱ እንዲመለስ ክልሎችና የከተማ ስፖርት አመራሮች መጠየቃቸው ታወቀ፡፡

ስፖርት ኮሚሽን ጥር 18 እና 19 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ በአገሪቱ ስፖርታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከክልልና ከከተማ የስፖርት አመራሮች ጋር ባካሔደው ውይይት ወቅት የቀድሞው ባለድል አትሌት ወደ አመራርነት ቦታው ይመለስ ጥያቄ መነሳቱ ታውቋል፡፡

ስፖርት ኮሚሽኑ ያቀረበው የውይይት አጀንዳ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተለይም በማዘውተሪያዎች አካባቢ የሚስተዋለው የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር፣ በስፖርቱ ሊኖር የሚገባው የመሪነት ሚናና ውጤታማነት ላይ ለመምከር ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በከፍተኛ ወኔና ብቃት ለመምራት ኃላፊነቱን በመውሰድ ከሁለት ዓመት ቆይታ በኋላ ግን ‹‹በቃኝ›› ያለው የኃይሌ ገብረሥላሴ ጉዳይ ተነስቶ ነበር፡፡ ከተወሰኑ ክልሎች ዝምታ በስተቀር፣ ኃይሌ ወደ ቀድሞው ኃላፊነቱ እንዲመለስ የሚጠይቁ አስተያየቶች መስተጋባታቸውን በውይይቱ የታደሙ የክልል አመራሮች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ጥያቄውን ካነሱት ክልሎች መካከል ቤንሻንጉል ጉምዝ፣ ደቡብ፣ አማራና ትግራይ ሲጠቀሱ፣ በተለይም ኃይሌ ከፌዴሬሽኑ የለቀቀበት ምክንያት በግልጽ ሊነገር እንደሚገባ ማሳሰባቸው ተነግሯል፡፡ የመድረኩ አዘጋጅ ስፖርት ኮሚሽን፣ ስለጉዳዩ ያለው ነገር ባይኖርም ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የኮሚሽኑ ሙያተኞች በበኩላቸው ኮሚሽኑ ጥያቄው ተገቢ ቢሆንም ዘግይቷል የሚል እምነት እንዳለው ገልጸዋል፡፡ ስለዚህ ጉዳይ የኃይሌ ገብረሥላሴ አስተያየት እንዲሰጥበት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲከስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ በመጥራት የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች በስፖርት አመራር ጉዳይ ላይ ለሚያነሱት ጥያቄ ውሳኔ ሊያስተላልፍ እየጠየቁ ነው፡፡

ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ ስለጉዳዩ እንደገለጹት ከሆነ፣ በፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ፕሬዚዳንቱ በሌሉበት ተቀዳሚው ምክትል ፕሬዚዳንት ተክቶ ይሠራል በሚለው አግባብ ሥራ አስፈጻሚውና የስፖርት ኮሚሽኑ ምክር ቤት በደረሱበት የፌዴሬሽኑ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በዚህ አኳኋን እየጠመራ ይገኛል፡፡ የዓለም አቀፉን አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ) መሠረት በመድረግ የፌዴሬሽኑን ኃላፊነት ተቀብለው እየሠሩ ለሚገኙት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ የዕውቅና ደብዳቤ መጻፉን ጭምር ተናግረዋል፡፡

30/12/2018

• ሞዛምቢክ ተማሪዎችን ያበረታታሉ በማለት ነፍሰጡር ሴቶች ከሌሎች ጋር ተቀላቅለው እንዳይማሩ የሚከለክለውን ህጓን አነሳች።
በ2003 በወጣው ህግ መሰረት ነፍሰጡሮች የማታ ትምህርት ብቻ እንዲከታተሉ ነበር የተፈቀደው።
• የ112 ዓመት ዕድሜ ባለጸጋ የሆኑት በአሜሪካ በእድሜ ትልቁ ሰው ሪቻርድ ኦቨርተን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ሰውዩው ህይወታቸው ከማለፉ በፊት ዕድሜ ልኬን ሲጋራ ማጨሴ ምንም ጉዳት አላደረሰብኝም ማለታቸው ብዙዎችን አስገርሞ ነበር።
• ታዋቂዋ የሆሊዉድ ፊልም ተዋናይት አንጀሊና ጆሊ ወደፊት ፖለቲካ ውስጥ ልትገባ እንደምትችል ገለጸች።
ተዋናይቷ በአሁኑ ሰአት በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ልዩ አምባሰደር ሆና በማገልገል ላይ ትገኛለች።

ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን?ጤናማና የተስተካከለ ሰውነት ያላቸው ሰዎች ቁርሳቸውን አይዘሉም ይባላል። ነገር ግን ቁርስ መብላት ሙሉ በሙሉ ጤናማ ወይም ቀጭን ያደርገናል ማለት አይ...
18/12/2018

ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን?
ጤናማና የተስተካከለ ሰውነት ያላቸው ሰዎች ቁርሳቸውን አይዘሉም ይባላል። ነገር ግን ቁርስ መብላት ሙሉ በሙሉ ጤናማ ወይም ቀጭን ያደርገናል ማለት አይደለም።
ነገር ግን ምን ያህሎቻችን ቁርስ በትክክለኛው ሰአት እንመገባለን?
ቁርስ ሳይዘሉ መመገብ ትክክለኛ መሆኑን ለማሳየት የሚቀርበው ምክንያት ሌሊቱን ሙሉ ሲጾም ያደረ ሰውነታችንን በምግብ መጠገን አለብን የሚለው ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ሰውነታችን የሚያድገው እና ጉዳት የደረሰባቸው የሰውነት ክፍሎች የሚጠገኑት በምንተኛበት ወቅት መሆኑ፤ ብዙ ጉልበት እንድንጨርስ ያደርገናል።

ስለዚህ በቁርስ ሰአት ምግብ መብላት ብቻ ሳይሆን የተመጣጠነ ምግብ መመገብ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን የስነ ምግብ ባለሙያዋ ሳራ ኤልደር ትናገራለች።
ነገር ግን አሁንም ድረስ ቁርስ የዕለቱ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነው ወይ? በሚለው ሃሳብ ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረስ አልተቻለም።
ቁርስ አስፈላጊ ነው ወይስ አይደለም?
በተለያዩ ጥናቶች መሰረት ቁርስ መብላትም ሆነ ቁርስ መዝለል ተያይዘው የሚነሱት ካላስፈላጊ ውፍረት ጋር ነው። ምንም እንኳን በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የተለያዩ ሃሳቦች ቢኖሩም፤ ግንኙነቱ ግን ምንድነው?
ሰባት ዓመታት በፈጀና 50 ሺ ሰዎች በተሳተፉበት አንድ ጥናት መሰረት የተመጣጠነ ቁርስ በሰአቱ የሚመገቡ ሰዎች ምሳ ወይም እራት ሰአት ላይ ከበድ ያለ ምግብ ከሚመገቡ ሰዎች አንጻር፤ የክብደት መጠናቸው ጥሩ በሚባል ደረጃ ላይ እንደተገኘ ያሳያል።

አጥኚዎቹ እንደሚሉት እነዚህ ቁርሳቸውን በትክከል የተመገቡ ሰዎች ቀኑን ሙሉ የሚሰማቸው የረሃብ ስሜት የቀነሰ እንደሚሆንና የሚመገቧቸው ምግቦች መጠን እንደሚቀንስ ያስረዳሉ።
የተመጣጠነ ቁርስ በተገቢው ሰአት መመገብ ያልቻሉት ሰዎች ደግሞ ሰውነታቸው ሌሊቱን ሙሉ ያቃጠለውን ሃይል መተካት ስላለበት፤ ቀኑን ሙሉ ምግብ ቢመገቡም የመርካት ስሜት ስለማይኖራቸው ከመጠን ያለፈ ምግብ እንዲመገቡ ይገደዳሉ።
ሆኖም አጥኚዎቹ ቁርስ ያልተመገቡ ሰዎች በቀጥታ ላላስፈላጊ ውፍረት የተጋለጡ ናቸው የሚለውን ሃሳብ ማረጋገጥ አልቻሉም።

የ27 ዓመቱ ኬንያዊ ሁለት ሚስቶችን በአንድ የሰርግ ስነስርዓት አገባ።ጋብቻው የተፈፀመው ካጃዶ በተሰኘ የኬንያ ግዛት ሲሆን ወጣቱ ያገባቸው ሴቶች የ23 እና የ25 ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች...
16/12/2018

የ27 ዓመቱ ኬንያዊ ሁለት ሚስቶችን በአንድ የሰርግ ስነስርዓት አገባ።

ጋብቻው የተፈፀመው ካጃዶ በተሰኘ የኬንያ ግዛት ሲሆን ወጣቱ ያገባቸው ሴቶች የ23 እና የ25 ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው።

Programs - Tuesday And Thursday From 6:00 - 7:00 Pm Wazema music  And Information - Saturday night 7:00 - 9.00 PM Wazema...
13/12/2018

Programs
- Tuesday And Thursday From 6:00 - 7:00 Pm Wazema music And Information
- Saturday night 7:00 - 9.00 PM Wazema Saturday Night Show.
Host and Producer Simon Tsegaye ,Sima
Ethiofm 107.8

Address

Addis Ababa
24055

Telephone

+251975757557

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wazema Communication And Events posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share