29/01/2026
በተባበሩት መንግሥታት የተመሰገነችው ኢትዮጵያ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኢትዮጵያ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለሰላም ማስከር ለሰራችው ስራ ምስጋናውን አቅርቧል🙏
ከ1500 በላይ ወታደሮችን እና ፖሊሶችን በማሰማራት ለሰላም ማስከበር ላበረከተችው አስተዋጽኦ የተባበሩት መንግስታት ምስጋናውን አቅርቧል።
ኢትዮጵያ በ1960 ከኮንጎ የጀመረችው ሰላም ማስከበር በአቢዬ ላይቤሪያ እና ዳርፉር የዘለቀ ሲሆን በነዚህ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች እስከ ሕይወት መስዕዋትነት የደረሰ ዋጋ ከፍላለች።
በተጨማሪም 164 ሴቶች በነዚህ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች መሳተፋቸውን የተባበሩት መንግሥታት የገለጸ ሲሆን በዝርዝሩ ውስጥ ኢትዮጵያ 10ኛ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት ያሰማራች ሀገር ሆናለች