24/08/2025
ደስታዬ በጌታ ሙሉ ነው ሸዋፈራው ላይ ከባድ ዘመቻ ተካሂድዋል እና ምን አድርጎ ነው ብዬ ጠየኩ ኦርቶዶክስ ተሳድቦ አሉኝ ( እንደመሰልቸት ብዬ) ምን ብሎ ነው የተሳደበ ለምንስ ይሳደባል ብዬ ስጠይቅ ግን መልሱ በጣም ያስቃል
አባቱን ተችቶ ( ግን ማስረጃ የለም ለማለቱ) 😀 ምን ብሎ? የንሰሃ አባቴ ምን ልሁን ምን ላድርግ የት ልዋል አይከታተለኝም ነበር ፀበል ብቻ ረጭቶኝ ይሄዳል ብሎ😂
እና ይሄ ነው የእንጀራ ገመድ ለመበጠስ ይሄ ሁሉ ግርግር እና እሩጫ?እንዴት ያሳፍራ🤗
ሁላችሁም የምትኖሩትን ህይወት እናንተ እራሱ የምትማረሩበትን የምትናደዱበትን በየ ቤቱ በየ ጓዳ ያለን እውነት እሱ በአደባባይ መናገሩ ያውም ፐርሰናሊ ራሱ ስለኖረው ህይወት መናገሩ በምን ስሌት አስልታችሁት ነው እንዴትስ ብታስቡት ነው ድንጋይ ያስነሳችሁ?
እንዴትስ ነው ?
እያፈርን ወገን እያፈርን የምር ደስ አይልም ለራሳችሁ እና ለእምነታችሁ ትንሽ እንኳን ክብር ካላችሁ እንደዚህ አይነት የወረደ የሚያቀላችሁን ነገር አታድርጉ።