Soccerr bet

Directions

Soccerr bet Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Soccerr bet, Arts and entertainment, Addis Ababa.

ፔጃችንን ይቀላቀሉ ..እየተዝናኑ ይማሩ…እየተማሩ ይዝናኑ!
ይህ ገፅ ኪነ-ጥበብን እና ስፖርትን( እግርኳስን )በተመለከተ መረጃ የሚተላለፍበት..ወቅታዊ ዜናዎች የሚነገርበት ሲሆን ከዛም በተጨማሪ ወጥ ተከታታይ ልብ ወለዶችን፤ ግጥሞችና ጥቅሶች የሚቀርቡበት የስፖርት እና የመዝናኛ ገፅ ነው፡፡

🚨 ሪከርድ፡ ሪያል ማድሪድ በጆሴ ሞሪንሆ ስር በ188 ጨዋታዎች ብቻ 500 ጎሎችን አስቆጥሯል።🍛በሪያል ማድሪድ ታሪክ ይህንን ታላቅ ምዕራፍ በአጭር የጨዋታ ብዛት (በፍጥነት) በማሳካት ረገድ ...
15/10/2026

🚨 ሪከርድ፡ ሪያል ማድሪድ በጆሴ ሞሪንሆ ስር በ188 ጨዋታዎች ብቻ 500 ጎሎችን አስቆጥሯል።

🍛በሪያል ማድሪድ ታሪክ ይህንን ታላቅ ምዕራፍ በአጭር የጨዋታ ብዛት (በፍጥነት) በማሳካት ረገድ እሳቸውን የሚቀድም አሰልጣኝ የለም።

ምንጭ፡ ማርካ (Marca)

የእኛ የምን ጊዜውም ጥበበኛ ተጫዋች ሜሱት ኦዚል በዛሬው 37ኛ ዓመቱን ይዟል።🎈🎉መልካም ልደት 🪄🇩🇪
15/10/2026

የእኛ የምን ጊዜውም ጥበበኛ ተጫዋች ሜሱት ኦዚል በዛሬው 37ኛ ዓመቱን ይዟል።🎈🎉

መልካም ልደት 🪄🇩🇪

የለንደኑ አርሰናል ከሜዳ ውጭ ያሉ 60 የስራ መደቦችን ሊቀንስ መሆኑ ተሰማከ22 ዓመታት ረጅም ጥበቃ በኋላ የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ የቻለው አርሰናል፣ በክለቡ ውስጥ ሰፊ የሰ...
15/10/2026

የለንደኑ አርሰናል ከሜዳ ውጭ ያሉ 60 የስራ መደቦችን ሊቀንስ መሆኑ ተሰማ

ከ22 ዓመታት ረጅም ጥበቃ በኋላ የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ የቻለው አርሰናል፣ በክለቡ ውስጥ ሰፊ የሰራተኞች ቅነሳ ሊያደርግ መሆኑን የቴሌግራፍ ዘገባ አመለከተ። ክለቡ ዛሬ ጠዋት ለሰራተኞቹ ባስተላለፈው መርዶ፣ 60 የሚሆኑ የስራ መደቦች እንደሚቀነሱ የገለጸ ሲሆን፥ ውሳኔው የሚያተኩረውም ከሜዳ ውጭ ባሉ የስራ ክፍሎች ላይ ነው።

ይህ የቁጠባ እርምጃ የወጣው ክለቡ ለዋና አሰልጣኙ ሚኬል አርቴታ በዓመት 20 ሚሊዮን ፓውንድ የሚያስገኝ አዲስ የአራት ዓመት ውል ካቀረበ ከአንድ ሳምንት በኋላ መሆኑ በክለቡ ደጋፊዎችና የስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል።

ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ዉሉን ማደስ አይፈልግም!በቀጣዩ የዝዉዉር መስኮት ከማንቸስተር ዩናይትድ መልቀቅ ይፈልጋል!     🥇THE ATHLETIC
15/10/2026

ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ዉሉን ማደስ አይፈልግም!

በቀጣዩ የዝዉዉር መስኮት ከማንቸስተር ዩናይትድ መልቀቅ ይፈልጋል!

🥇THE ATHLETIC

🔴 የጂሚ ካራገር አነጋጋሪ አስተያየት፦ «ፒኤስጂን ማስቆም የሚችለው ብቸኛው ቡድን አርሰናል ብቻ ነው!»ማንችስተር ሲቲ በሜዳው ኢቲሃድ በፓሪስ ሴንት ዠርሜይን 4 ለ 2 በሆነ ውጤት መሸነፉን ...
15/10/2026

🔴 የጂሚ ካራገር አነጋጋሪ አስተያየት፦ «ፒኤስጂን ማስቆም የሚችለው ብቸኛው ቡድን አርሰናል ብቻ ነው!»

ማንችስተር ሲቲ በሜዳው ኢቲሃድ በፓሪስ ሴንት ዠርሜይን 4 ለ 2 በሆነ ውጤት መሸነፉን ተከትሎ፣ የስካይ ስፖርትስ እግር ኳስ ተንታኝ ጂሚ ካራገር ማንችስተር ሲቲን እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦችን አጥብቆ የሚወቅስና አርሰናልን የሚያሞግስ አስተያየት ሰጥቷል።

🎙️ የጂሚ ካራገር ሙሉ አስተያየት፦

"አርሰናል በቡዳፔስት ከዚሁ ፒኤስጂ ጋር አቻ ከተለያየ በኋላ፣ ፒኤስጂዎች ፔፕ ጋርዲዮላ ባሉበት ኢቲሃድ ላይ ማንችስተር ሲቲን በታትነውታል። ሁሉም ሰው አርሰናል ከፒኤስጂ ጋር ሲወዳደር ደካማ ቡድን ነው ብሎ አስቦ ነበር፤ ነገር ግን አሁን ላይ እውነታው ቁልጭ ብሎ እየታየ ነው — ይህንን ፒኤስጂ ማስቆም የሚችለው ብቸኛው ቡድን አርሰናል ብቻ ነው። አርሰናል በፔናሊቲ በፒኤስጂ ተሸንፎ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ሲያጣ ያፌዙባቸው የነበሩት ሲቲዎች፣ ራሳቸው ዛሬ በኢቲሃድ በመጀመሪያው አጋማሽ 3 ለ 0 ሲቀጡ ታይተዋል።

ማንችስተር ሲቲ በሜዳው እየተጫወተ የሜዳውን ብልጫ መጠቀም አልቻለም፤ ይህ በእርግጥም አሳፋሪ ነው! የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ከዚህ ፒኤስጂ ጋር ሲጫወቱ ጠንከር ማለት አለባቸው። ይሄው ያው ፒኤስጂ ነው — ባለፈው የውድድር ዓመት ቼልሲን አሸንፈው በአንድ ጨዋታ ስድስት ግቦችን አስቆጥረዋል፤ ሊቨርፑልም በዚሁ ፒኤስጂ እጅ መከራውን አይቷል።

በእኔ እምነት ከፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ፒኤስጂን ማሸነፍ የሚችለው አርሰናል ብቻ ነው፤ ምክንያቱም ቀደም ሲል አድርገውታል እና እኛንም ማሳመን የሚችሉት እነሱ ብቻ ናቸው። ሁሉም ሰው ማንችስተር ሲቲ ባለው ስብስብ ፒኤስጂን ማስቆም ይችላል ብሎ አስቦ ነበር። ነገር ግን ፔፕን አሳፍረውታል፤ ፔፕ በኢቲሃድ ስታዲየም የሚያየውን ነገር ማመን የሚችል አይመስለኝም፤ ይህ ለፔፕ ጋርዲዮላ በጣም መጥፎ አቀባበል እና አሳፋሪ ምሽት ነበር።"
Via።FS sport

“ሪያል ማድሪዶች በእኛ ደረጃ ላይ አልነበሩም። ከደረጃ  በታች ነበሩ። በሁሉም ነገር ላይ ከእነሱ የተሻልን ነበርን።ይበልጥ በርካታ ጎሎችን ማስቆጠር እንችል ነበር። እነሱ ጎሎቹን አስቆጥረዋል...
15/10/2026

“ሪያል ማድሪዶች በእኛ ደረጃ ላይ አልነበሩም። ከደረጃ በታች ነበሩ። በሁሉም ነገር ላይ ከእነሱ የተሻልን ነበርን።

ይበልጥ በርካታ ጎሎችን ማስቆጠር እንችል ነበር። እነሱ ጎሎቹን አስቆጥረዋል፣ ያ ደግሞ ተገቢ ነው፤ እንዲሁም አካላዊ ጥንካሬን ይዘው ለመቅረብ ተሳክቶላቸዋል፣ ነገር ግን ነገሩ በቃ ይኸው ብቻ ነው።

ሞሪንሆ መጨረሻ ላይ ነዳጅ/ ጨርሰው ነው አሉ? እኔ እንደማስበው የደከመውና ያለቀለት ሰው ካለ እነሱ እንጂ እኛ አይደለንም።”
የሮማው አሰልጣኝ

ከሁለተኛ ሳምንት የአውሮፓ ቻምፒዬን ሊግ ጫወታ በኋላ የደረጃ ሰንጠረዣ
15/10/2026

ከሁለተኛ ሳምንት የአውሮፓ ቻምፒዬን ሊግ ጫወታ በኋላ የደረጃ ሰንጠረዣ

ኤርሊንግ ብራውት ሀላንድ በማንችስተር ሲቲ ቤት  በአጉዮሮ ተይዞ የነበረውን በሻምፒዮንስ ሊግ 38 ጎል የማስቆጠር ክብረ ወሰን ሰብሮታል
15/10/2026

ኤርሊንግ ብራውት ሀላንድ በማንችስተር ሲቲ ቤት በአጉዮሮ ተይዞ የነበረውን በሻምፒዮንስ ሊግ 38 ጎል የማስቆጠር ክብረ ወሰን ሰብሮታል

“የዛሬው ሁለተኛው አጋማሽ አጫወታችን? በቀሪው የውድድር ዘመን በዛ መልክ ከተጫወትን፡ በርካታ ጨዋታዎችን እናሸንፋለን።”ማርክ ጉኤሂ (Marc Guéhi)
14/10/2026

“የዛሬው ሁለተኛው አጋማሽ አጫወታችን? በቀሪው የውድድር ዘመን በዛ መልክ ከተጫወትን፡ በርካታ ጨዋታዎችን እናሸንፋለን።”

ማርክ ጉኤሂ (Marc Guéhi)

ዛሬ ሀላንድ ለማሸነፍ የተቻለውን ያህል ጥሮ ነበር..በተለይ ከረፍት በኋላ ....
14/10/2026

ዛሬ ሀላንድ ለማሸነፍ የተቻለውን ያህል ጥሮ ነበር..በተለይ ከረፍት በኋላ ....

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Soccerr bet posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share