10/07/2026
OpenAI launches new GPT-5.6 models.
ከአሜሪካ መንግስት ጋር ለ12 ቀናት በደህንነት ፍተሻ ዙሪያ በነበረው ውይይት ምክንያት ውስን ለሆኑ ተቋማት ብቻ ተለቆ የነበረው GPT-5.6 አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ተፈቅዶ ለአለም አቀፍ ተጠቃሚዎች ይፋ ሆኗል።
ይህ አዲሱ ሞዴል በሶስት የተለያዩ ስሪቶች (Variants) የቀረበ ሲሆን እያንዳንዳቸው ለተለያዩ የስራ አይነቶችና የክፍያ መጠን አላቸው።
1️⃣ GPT-5.6 SOL - የOpenAI ዋናውና ትልቁ Flagship ሞደል ሲሆን በተለይ ራሳቸውን ችለው ለሚሰሩ የኮዲንግ ስራዎች (Agentic Coding)፣ በCybersecurityና በባዮሎጂ ምርምሮች ላይ ከፍተኛ አቅም አለው ተብሏል። ከዋና ተፎካካሪው Claude Fable 5 የላቀ ውጤት ያሳየ ቢሆንም በ3 እጥፍ ያነሰ ዋጋ የሚጠይቅና እጅግ ፈጣን ነው።
2️⃣GPT-5.6 Terra - ለዕለታዊ የቢሮና የፈጠራ ስራዎች የተሰራ ሲሆን የቀድሞው የGPT-5.5ን ያህል ጠንካራ አቅም አለው ነገር ግን ዋጋው በግማሽ የቀነሰ እና ወጪ ቆጣቢ ነው።
3️⃣GPT-5.6 Luna - Budget-friendly ሞዴል ሲሆን በጣም ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ እና በዋጋ ደረጃ እጅግ በጣም ርካሹ model ነው።
✨ Main Features
በኮዲንግ ስራዎች ላይ የቶከን አጠቃቀም ቅልጥፍናን በ54% ያሻሻለ ሲሆን፣ ድርጅቶች ለሶፍትዌር ማበልጸጊያ የሚያወጡትን ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል።
ከተለያዩ ሰነዶች እንዲሁም እንደ Slack, Notion, Microsoft 365 እና Google Drive ካሉ አፕሊኬሽኖች ላይ መረጃዎችን በመውሰድ በራሱ ጊዜ ሙሉ የPowerPoint Presentation፣ ፋይናንሻል ሞዴሎችን እና የኤክሴል ስፕሬድሺቶችን ያዘጋጃል።
ቀደም ሲል ከነበሩት ሞዴሎች በ10 እጥፍ በበለጠ ሁኔታ አደገኛ እና ጎጂ የሆኑ የሳይበር ጥቃቶችን የመከላከል አቅም አለው።
ይህንን ሞዴል አሁን ላይ በChatGPT፣ በOpenAI APIና በCodex ላይ መጠቀም ይችላላል።
================
👉 Join us 👈
👇 Telegram 👇
https://t.me/pvaeducationEt
Telegram Discussion Group 👇
https://t.me/PVA_Education_Chat
YouTube 👇
https://youtube.com/
Tiktok 👇
tiktok.com/