Ethio Recap

Ethio Recap Enjoy the Vibes! Ethio Recap Formerly kanatunes is an Ethiopian Digital Media Services founded on July 14, 2013.

Since that time become the premier online entertainment destination for Ethiopians, not only at home but abroad as well. It is one of the few sites, if not the only site, that provide Ethiopians with multidimensional access to the entertainment and information that matters to them.

03/01/2023
ጭራሽ ተይዟል🤔አረ የኛስ ነገር ለጉድ ነው 🤔በቁም እያለን ሰንሞት ለበድናችን ማረፊያ በአስር ሺዎች ከፍለን ቦታ እምናዘጋጅ ጉዶች😔ምናለ በቁማችን ለመቀበሪያችን የከፈልነውን ለመልካም ተግባር ...
07/08/2022

ጭራሽ ተይዟል🤔

አረ የኛስ ነገር ለጉድ ነው 🤔
በቁም እያለን ሰንሞት ለበድናችን ማረፊያ በአስር ሺዎች ከፍለን ቦታ እምናዘጋጅ ጉዶች😔
ምናለ በቁማችን ለመቀበሪያችን የከፈልነውን ለመልካም ተግባር አውለነው ለዘላለም ማረፊያችን ሳንከፍል በደስታ ወደላይኛው ቤታችን ብንጓዝ?

Courtsey : jositsehay

የታክሲ ውስጥ ሿሿ ለጥንቃቄ በተለይ ለሴት እህቶቻችን ሴት እህቶቻችን በታክሲ ዉስጥ  ሿሿ በሚባል የሌብነት አይነት በየቀኑ ማለት በሚቻል  ደረጃ እየተስፋፋ ስለሆነ  ሁሌም ጥንቃቄ አይለያችሁ...
03/08/2022

የታክሲ ውስጥ ሿሿ

ለጥንቃቄ
በተለይ ለሴት እህቶቻችን
ሴት እህቶቻችን በታክሲ ዉስጥ ሿሿ በሚባል የሌብነት አይነት በየቀኑ ማለት በሚቻል ደረጃ እየተስፋፋ ስለሆነ ሁሌም ጥንቃቄ አይለያችሁ
1, እረዳቱ የትነሸ / ናቹ ሲል የሚሄዱበትን ቦታ ቀድሞ አለመናገር
2, ጋቢና አሰገብተው የበሩ ጎሚኒ ለቀቀ አሰተካክይው ሲሉ አለመተባበር
3, አጠገብሸ ያሰቀመጡት ሰው ሴትም ብትሆን የነሱ ተባባሪ ሰለምትሆን ሰልክ ቁጥር በስልክሸ ያዥልኝ ሲልሽ/ስትልሽ የስልክሽን አይነት አይቶ ለመስረቅ ስለሆነ በተቻለ አቅም ፈቃደኛ አለመሆን
4. ሶስት ወይም አራት ሆነው ተነጣጥለው የተቀመጡ ተሳፋሪዎች ሲያጋጥሙ ጥንቃቄ ማድረግ
5. የታክሲዉ ታፔላ እንዲሁም ታርጋው የተሸፈነ የተቆለመመ ከሆነ መጠራጠር
6. ከጎንሽ የተቀመጠው ተሳፋሪ ኮቱን በእጁ ይዞ እጁን ሸፍኖ ሚቁነጠነጥ ከሆነ ጥንቃቄ ማድረግ
7. ታክሲው እየሄደ ጋቢና ከሌላ ሰው ጋር ተቀምጠሽ የጋቢናው መስታወት ክፍት ሆኖ ረዳቱ በደጅ በኩል ሲያዋራሽ ጥንቃቄ ማድረግ ምክንያቱም አንቺ ዞረሽ በየዋህነት እሱን ስታዋሪው ከጎንሽ ያለው ሰው ከቦርሳሽ ውስጥ ሊሰርቅ ስለሚችል
8, አልኮል ሳኒታይዘር ልቀባሽ ሲሉ እንቢ ማለት ምክንያቱም የመርጫውን ጫፍ አዙረው በቀጥታ ወደ አይንሽ በመርጨት አንቺ አይንሽን ስታሺ ቦርሳሽን ወስደው ከታክሲ ውስጥ ሊወረዉሩሽ ስለሚችሉ
ተጠንቀቁ አንድ ሰው አነብቦት ይጠቅመዋል ካላችሁ
ሼር አድርጉላቸው !!

Shewit Mezgebo - Tsemaekani | ሽዊት ምዝገቦ - ጸማእካኒ Tigrigna Ethio Recap Presents
03/08/2022

Shewit Mezgebo - Tsemaekani | ሽዊት ምዝገቦ - ጸማእካኒ Tigrigna Ethio Recap Presents

Ethiopian Music : Shewit Mezgebo - Tsemaekani | ሽዊት ምዝገቦ - ጸማእካኒ Tigrigna Ethio Recap PresentsFacebook : https://www.facebook.com/EthioRecap Twitter : https:...

Minalush Reta - Ethio-Sudanise Music ምናሉሽ ረታ - ሱዳንኛ ሙዚቃ |music 2022 Recap Presents
02/08/2022

Minalush Reta - Ethio-Sudanise Music ምናሉሽ ረታ - ሱዳንኛ ሙዚቃ |music 2022 Recap Presents

Ethiopian Music : Ethio-Sudanise Music | old music 2022 Ethio Recap | old music 2022 Ethio Recap PresentsFacebook : https://www.facebook.com/EthioRecap Twit...

Aboneshe Adinew - Dera | አቦነሽ አድነው - ደራ | old music 2022 Ethio Recap Presents
02/08/2022

Aboneshe Adinew - Dera | አቦነሽ አድነው - ደራ | old music 2022 Ethio Recap Presents

Ethiopian Music : Aboneshe Adinew - Dera | አቦነሽ አድነው - ደራ | old music 2022 Ethio Recap PresentsFacebook : https://www.facebook.com/EthioRecap Twitter : https...

Dagi D Bayish ዳጊ ዲ ባይሽ New Ethiopian Music video 2022 will be released via Antsar
02/08/2022

Dagi D Bayish ዳጊ ዲ ባይሽ New Ethiopian Music video 2022 will be released via Antsar

Ethiopian Music : Dagi D Bayish ዳጊ ዲ ባይሽ New Ethiopian Music video 2022 Ethio Recap PresentsFacebook : https://www.facebook.com/EthioRecap Twitter : ...

Best Ethiopian Hot and Slow Music Collection Mix 2022 Ethio Recap Presents
02/08/2022

Best Ethiopian Hot and Slow Music Collection Mix 2022 Ethio Recap Presents

Ethiopian Music : Best Ethiopian Hot and Slow Music Collection Mix 2022 Ethio Recap PresentsFacebook : https://www.facebook.com/EthioRecap Twitter : https://...

የእርዳታ ጥሪየ27 አመት ወጣት የሆነችው ሳምራዊት ደስታ ላለፉት አምስት ወራት በማህፀን በር ካንሠር ህመም ስትሰቃይ ቆይታለች።ወጣት ሳምራዊት የዩንቨርስቲ ትምህርቷን በወለጋ ዩንቨርስቲ በአር...
01/08/2022

የእርዳታ ጥሪ
የ27 አመት ወጣት የሆነችው ሳምራዊት ደስታ ላለፉት አምስት ወራት በማህፀን በር ካንሠር ህመም ስትሰቃይ ቆይታለች።
ወጣት ሳምራዊት የዩንቨርስቲ ትምህርቷን በወለጋ ዩንቨርስቲ በአርክቴክቸር ኢንጂነሪንግ ተመርቃ ዳግም በአዲስ አበባ እናት ሀገሯን የምታገለግል ባለትዳር እና የአንድ ወንድ ልጅ እናት ስትሆን ነገን ሰርታ ቤተሰቦቿን መደገፍ ህልሟ ነበር።
ነገር ግን አሁን ላይ ይህን የማህፀን በር ካንሠር በሽታን ወደ ውጭ ሀገር ሄዳ ህክምና እንድታገኝ በጥቁር አንበሳ የህክምና ቦርድ ተወስኗል።
ላለፉት አምስት ወራት በተለያየ የህክምና ማእከል ህክምና ስትከታተል የነበረችው ሳምራዊት ቀጣዩ ህክምና የሚሰጠው በህንድ ሀገር ሲሆን ህክምናውንም ለማድረግ አቅም ስላጠራት ባለን አቅም ሁሉ በመረባረብ ህይወቷን እንታደግ። ለልጇ እናትርፉት!!!
ዘወትር ለበጎ ሀሳ የማትታክቱ ኢትዮጵያውያን ወገኖች የአቅማችሁን እንድታደርጉ በእግዚአብሔር ስም እንማፀናለን። ይላሉ ቤተሰቦቿ።
ንግድ ባንክ
Commercial Bank of Ethiopia (CBE)
1000180776145 ገነት ጀምበሩ ዳምጠው (እናቷ)
ለተጨማሪ መረጃ +251 91 038 4728 / +251 91 337 9447

ጌትነት እንየውን የራሱን ቲያትር ከፍሎ ሊመለከት  ነው::(ለበጎ ተግባር ነውና ሼር ይደረግ)* ከፍተኛውን የመግቢያ ትኬት ነው የገዛው:: እናመሰግናለን እባካችሁ እናንተም አመስግኑልን::***...
27/07/2022

ጌትነት እንየውን የራሱን ቲያትር ከፍሎ ሊመለከት ነው::
(ለበጎ ተግባር ነውና ሼር ይደረግ)
* ከፍተኛውን የመግቢያ ትኬት ነው የገዛው:: እናመሰግናለን እባካችሁ እናንተም አመስግኑልን::
*********
(ይትባረክ ዋለልኝ)
ተወዳጁ የጥበብ ሰው ጌትነት እንየው "የቴዎድሮስ ራዕይ" ቲያትር ደራሲና አዘጋጅ ነው::ጌትነት እንየው ተናጋሪ የላቁ የጥበብ ስራዎቹን ይሰራል እንጂ የአደባባይ ሰው አይደለም:: ዝምተኛ የጥበብ ሰው ነው:: የዳይሬክተር አሸብር ካብታሙ ህይወትን እንታደግ ብለን በጠየቅነው ማግስት ግን ቀዳሚ ሆነው አለን ብለው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የአሸብርን ህይወት ለመታደግ የቆሙት ጌትነትና እንየውና ፕሮዲውሰሩ ተስፉ የቲያትር ኢንተርፕራይዝ ናቸው:: ኪነጥበብ የኪነጥበብ ሰውን ህይወት መታደግ ይችላል ብለው "የቴዎድሮስ ራዕይ" ቲያትርን ሙሉ ገቢ የአሸብርን ህይወት ሊታደጉ ካጠገቡ ቆሙ:: ዛሬ ደግሞ ሌላ የአለሁለት ድምፅ ከተወዳጁ የጥበብ ሰው ደረሰን::
ጌትነት እንየው ከቴአትሩ የሚያገኝውን ገቢ መስጠቱ ሳያንስ ለተፈራ ወርቁ አሁን ደውሎ "ተፈራ የጥበብ አጋሬን የአሸብር ካብታሙ ህይወት ለመታደግ እንደማንኛውም የጥበብ ሰው "የቴዎድሮስ ራዕይ" ቲያትሬን ለመመልከት የሁለት ሺህ ብር ትኬት እገዛለሁ" በተጨማሪም "የቴዎድሮስ ራዕይ" ቲአትሬን ነገ ረቡዕ ሐምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም በ11:00 ተገኝቼ ከበርካታ የጥበብ ወንድሞቼና ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እመለከታለሁ ብሎናል::
ጌትነት እግዚአብሔር ይስጥህ ሌላ ምን ማለት እችላለሁ:: እባካችሁ እናንተም አመስግኑልን።
መልዕክቱን ያጋራን ይትባረክ ዋለልኝ ነው።
የከያኒ አሸብር ካብታሙን ሕይወት ለመታደግ ሁላችንም እንሳተፍ።

Address

Kebena
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Recap posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share