Delanta Tube.com

Delanta Tube.com share trusted news videos and photo

02/01/2025

📷 Face of Lalibela

16/10/2023

😂🤣🤣

02/07/2022

ከ‹‹እከሌን ፍቱት!›› ወደ ‹‹እከሌን የት አደረሳችሁት!››? (ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)

ዛሬ እህቴ በጠዋት ከሀዋሳ ደውላ፣ ‹‹ትዝ ይልሀል በወያኔ ጊዜ፣ ያኔ አንተ በፍትህ ጋዜጣ ላይ በምትጽፍበት ዘመን?›› ስትለኝ፤ ‹‹ምኑ ነው ትዝ የሚለኝ?›› አልኳት፡፡ ‹‹እከሌ ይፈታ! እያላችሁ ነበር የምትጽፉት፤ ዛሬ የፌስቡኩና ዩቲዩቡ ቅኝት ‹‹የት አደረሳችሁት? ሆኗል›› አለችኝ፡፡ . . . . ሀዘን ተጫነኝ፤ ተከዝኩ፤ ጠዋቴን በተብሰልስሎት አሳለፍኩ፡፡ . . . .

በላይ በቀለ ወያ ከጠፋ ቀናት እየተቆጠሩ ነው፡፡ ብዙዎች ‹‹መንግስት አፍኖታል›› ብለው እየከሰሱና ምላሽ እንዲሰጥ እየወተወቱ ነው፡፡ ‹‹ለምን መንግስት ባልተረጋገጠ ጉዳይ ይከሰሳል?›› የሚሉም አሉ፡፡ በሁለት ምክንያቶች የተነሳ የመንግስትን ከሳሾች ሀሳብ እጋራለሁ፡፡

የመጀመሪያው ምክንያት፤
መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወንጀል የሚጠረጥራቸውን ሰዎች የሚያስረው ህግን ተከትሎ ሳይሆን፣ ካሉበት ሄዶ በማፈን ነው፡፡ ህግን ለማስከበርና ወንጀልን ለመከላከል እንኳን ቢሆን ህገወጥ መንገድ መከተል እራሱ ህገወጥነት ነው፡፡ ስለዚህ ዛሬ አንድ ዜጋ (በተለይ መንግስት ላይ የተቃውሞ ሀሳብ የሰነዘረ) ሲጠፋ የመጀመሪያው ተጠርጣሪ መንግስት እንዲሆን አድርጓል፡፡ ህግን ተከትሎ ተጠርጣሪን መያዝ የሚችል መንግስት ህገወጥነትን የሚመርጥበት ምክንያት አይገባኝም፡፡

ሁለተኛው ምክንያት፤
መንግስት ዜጎች ሲጠፉ የሚያሳየው ዝምታ ነው፡፡ ልጅ ሲጠፋ ቀድሞ የሚጮኸው፣ የሚፈልገው፣ አፋልጉኝ የሚለው የቤተሰብ አስተዳዳሪው (አባወራ ወይም እማወራ) ነው፡፡ ዜጎች ሲጠፉ መጮህና ፍለጋ መውጣት የፖሊስ (መንግስት) ሀላፊነት ነው፤ ዋና ፈላጊው መሆን ያለበት እሱ ነው! ቤተሰብና ዜጎች አፈላላጊ ናቸው፡፡ እንዴት ነው አንድ ሰው ጠፋ ሲባል ፖሊስ ‹‹የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ›› የሚለው? እና መንግስት ተከሳሽ የሚሆንበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው፡፡

‹‹ሳይቃጠል በቅጠል›› - ይህ ድርጊት የመንግስት ባህርይ ሆኖ መቀጠልም፤ መወሰድም የለበትም፡፡ እዚሁ ላይ መስተካከል አለበት፡፡ ይህ የማይሆንና የመንግስት አፋኝነት በዜጎች ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት ካገኝ፣ ነገ ማንኛውም ቡድን ዜጎችን እያፈነ ለመውሰድና ለማሰቃየት ብሎም ለመሰወር ትልቅ ቀዳዳ ይፈጥራል፡፡ . . .. . . መንግስት ይህን ድርጊት ማቆም አለበት፡፡

ጤናማ ማህበረሰብ የሚቆመው በህግ የበላይነት ብቻ ነው፡፡ በነገራችን ላይ አንድ ሰው በወንጀል ከተጠረጠረ በህጋዊ መንገድ በህግ እንዲጠየቅ የህዝብም ፍላጎት ነው፡፡ በመሆኑም፣ መንግስት በወንጀል የሚጠረጥራቸውን በግልጽና በህግ መሰረት መጠየቅ አለበት፡፡ ይህ ሲሆን ከእሱ እውቅና ውጭ የሚሰወሩ/የሚታፈኑ ሰዎችን ጉዳት ሳይደርስባቸው በፊት ሊታደጋቸው ይችላል፡፡ አይበለውና በላይ በቀለ ወያ የታፈነው በወንጀለኛ ቡድን ቢሆን እኮ ያለ ፖሊስ ክትትል ባለፈው ሶስት ቀን የፈለጉትን ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡
እባካችሁ!

27/03/2022
ዶ/ር ይልቃል ከፋለ አስረስ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተመረጡ************************************የአማራ ክልል ምክር ቤት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ አስረስ የክልሉ...
30/09/2021

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ አስረስ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተመረጡ
************************************

የአማራ ክልል ምክር ቤት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ አስረስ የክልሉ ርዕሠ-መስተዳድር አድርጎ መርጧል፡፡

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በተለያዩ ትምህርት ኮሌጆች በመምህርነት፣ ዲን በመሆንና በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ም/ፕሬዝዳንትና ፕሬዝዳንት በመሆን ውጤታማ ሀላፊነትን የተወጡ አመራር መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በራሄል ፍሬው

ከጀነራል አበባው ወቅታዊ ንግግር የተወሰደ..!"..የእነሱ ትልቁ ሀይል  #ዘር ሲሆን የእኛ ትልቁ ሞተራችን  #ኢትጵያዊነት ነው...!!" ሌተናል ጄኔራል አበባው ታደሰ[የጦር ሀይሎች ም/ጠቅላ...
26/09/2021

ከጀነራል አበባው ወቅታዊ ንግግር የተወሰደ..!

"..የእነሱ ትልቁ ሀይል #ዘር ሲሆን የእኛ ትልቁ ሞተራችን #ኢትጵያዊነት ነው...!!"
ሌተናል ጄኔራል አበባው ታደሰ
[የጦር ሀይሎች ም/ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ]

አሸባሪዎቹ ህወሓቶች ከጦርነቱ በፊት ከጀርባ ይዘውት የነበረው ዓላማ የእነሱን ጥቅም በኢትዮጵያ ላይ መጫን የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ካለ አብሮ ለመስራትና የኢትዮጵያን ህዝብና መንግስት በጉልበት ጠምዝዘው የራሳቸውን ፍላጎት ማሟላት የሚል ነው፤ ይሄ የማይሳካ ከሆነ ደግሞ ኢትዮጵያን ማፍረስ ነበር ዓላማቸው...።

ለዚህ ዓላማ መሳካት ደግሞ ወታደር ያስፈልገናል ብለው ህጋዊ የሆነውን ልዩ ሀይል እንደ ሽፋን ተጠቅመው ከ200 ሺህ በላይ ሰው ያለበት ሀይል አደራጅተው ነበር..።

የጀመረው ጦርነት ዓላማውም ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው፤ እኛ ደግሞ የተከተልነው ስትራቴጂ ኢትዮጵያን ከብተና የማዳን ነው፤ የጦርነቱ ፍትሀዊነት የሚመነጨውም ከዚህ ነው...።

የጦርነቱን ዋነኛ ማዕከል መቀሌን አድርገን በፍጥነት በመሄድ ከሁለት ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ መቀሌን መቆጣጠር አለብን ካልሆነ አደጋ ነው ብለን አንድ ሰው እንደ አስር እየተዋጋ በፍጥነት ጨርሰናል...።

በሰው ሀይል ማደራጀት እነሱ ይበልጡን ነበር፤ ነገር ግን የእነሱ ትልቁ ሀይል ዘር ሲሆን የእኛ ትልቁ ሞተራችን ኢትጵያዊነት ነው...።

የኢትዮጵያዊነቱ መንፈስ እንደገና ደግሞ ዩኒፎርም ለብሰህ ዩኒፎርም የለበሰህ ጓደኛህ ከኋላህ ሲመታህ የሚፈጥረው መንፈስ አለ ያንን ጉልበት ይዘን ነው የተዋጋነው...።

ከሰራዊት አንጻር ያስቀመጥነው ግብ አሳክተናል፤ የታገቱብንን አባሎቻችንን አስለቅቀናል፤ የተወሰዱብንን ብረትና ተተኳሽ አስመልሰናል፤ ኢትዮጵያን አድነናል...።

ህወሓትን እንደ ድርጅት በትነነዋል፤ የሚደመሰሰውን ደምስሰናል፤ ኢትዮጵያን ሊያፈርስ የነበረውን የድርጅቱን አስኳል በትነን ለሰባትና ስምንት ወራት ዋሻ ውስጥ ከተናል፤ የቀረውን ደምስሰናል...።

ኢትዮጵያን ሁሌም የሚወጋት የእኛ የራሳችን ሰው ከውጭ ሃይል ጋር በመሆን ነው..!!

የውጭ ሃይል ቀጥታ አይመጣም፤ የውስጥ ሰውን እየያዘ ነው እየተዋጋን ያለው፤ ከውጭ የሚመጣው ጠላት በግልጽ ቢመጣማ ኖሮ ምንም ችግር አልነበረም...።

ኢትዮጵያ ውስጥ ማንም ሰው የፈለገውን አስተሳሰብ፣ የትኛውንም እምነት ይከተል፤ የትኛውንም ፖለቲካ ይከተል እኛ አያገባንም..!!

ኢትዮጵያን ከነኩ ግን ከውጩ ሰው ሳይሆን የምንጀምረው ከራሱ ነው፤ የራሳችንን ቤት ቆሻሻ ካላጸዳን ኢትዮጵያን ማቆም አንችልም...።

በአሁኑ ወቅት መከላከያ በስፋት ነው እየተጠናከረ ያለው በትጥቅ፣ በአየር ሃይላችን፣ በእግረኛ ሃይላችን፣ ሊገመት በማይችል አይነት መልኩ ነው እየተዘጋጀን ያለነው...።

መከላከያን ማጠናከር ለማንኛው ኢትዮጵያዊ በሩ ክፍትነው፤ ማንም ሰው መከላከያን መቀላቀል ይችላል፤ መደገፍ ይችላል፤ ማረም ይችላል ምክንያቱም የራሱ ሀብት ነው...።
የውስጥ እና የውጭ ስጋት አለብን፤ የውስጥ ስጋቱ ጊዜ የሚፈጅ አይደለም በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚስተካከል ነው....።

ለውጩ ስጋት ጠንክረን መዘጋጀት አለብን፤ በዚህ ሁለት አመት መከላከያ ፍጹም ሙሉ ለሙሉ ይቀየራል...።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ይሄ ጊዜ መለማመጃችን ይሆናል።

እኛ የሚያስፈልገን ዘር አይደለም፤ ሰውነታችን ነው፤ ሰውነታችን ካለ አገር አለ...።

አብዛኞቹ የሰበአዊ አርዳታ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ከመቐለ አልተመለሱም - የዓለም ምግብ ፕሮግራምአዲስ አበባ ፣መስከረም 6፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰበአዊ አርዳታ ጭነው መቐለ የገቡ አብዛኞቹ ተሽ...
17/09/2021

አብዛኞቹ የሰበአዊ አርዳታ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ከመቐለ አልተመለሱም - የዓለም ምግብ ፕሮግራም

አዲስ አበባ ፣መስከረም 6፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰበአዊ አርዳታ ጭነው መቐለ የገቡ አብዛኞቹ ተሽከርካሪዎች አልተመለሱም ሲል የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ።

በዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ቢሮ እንዳስታወቀው የዕርዳታ እህል እንዲያደርሱ 466 የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ መቐለ ቢላኩም የተመለሱት 38ቱ ብቻ ናቸው።

ቢሮ እንደሚለው ለትግራይ ህዝብ የሰበአዊ አርዳታ ለማድረስ ተሽከርካሪዎች እንደሚያስፈልጉት ገልጾ ጉዳዩ እንዳሳሰበው አስታውቋል።

አሸባሪው ህወሓት ተሽከርካሪዎችን በመውሰድ ለጥፋት ተግባሩ መፈፀሚያ እያዋላቸው እንደሆነ የሚያሳዪ መረጃዎች ከሳምንታት በፊት ሲወጡ ነበር።

 #ወሎ፦=> ወሎ የተራበው የሚበላው ስላልነበረው አይደለም፣=> ወሎ የተራበው ስላላረሰ አይደለም ፣ ወይም=> በድርቅና በተፈጥሮ አደጋ ጥሪቱ ወድሞበት አይደለም።ይልቁንም ኢትዮጵን ለማጥፋት የ...
16/09/2021

#ወሎ፦
=> ወሎ የተራበው የሚበላው ስላልነበረው አይደለም፣
=> ወሎ የተራበው ስላላረሰ አይደለም ፣ ወይም
=> በድርቅና በተፈጥሮ አደጋ ጥሪቱ ወድሞበት አይደለም።
ይልቁንም ኢትዮጵን ለማጥፋት የመጣን የጠላት ኃይል ሲጋፈጥ
የደረሰበት ጉዳት እንጂ። ወሎ ለሁላችንም የመጣውን የመከራ
ሸክም ነው የተሸከመልን። ለወሎ ረሀብ ሁላችንም ዕዳ አለብን፣
በወሎ ህዝብ የተከፈለልንን ዕዳችንን እንወጣ።
© ጋዜጠኛ Yonas Abiye
#ሼር በማድረግ የወሎ ሕዝብ ድምጽ ይሁኑ!!!

"የእኛ ዝግጅት ለጁንታው ሳይሆን እነሱን ለሚጋልቧቸው ገዢዎቻቸው ነው" - ሌ/ጄ ባጫ ደበሌየኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የሚያደርገው የሰራዊት ግንባታ ሂደት አላማው አሸባሪው ህወሓትን ማሸነፍ እ...
16/09/2021

"የእኛ ዝግጅት ለጁንታው ሳይሆን እነሱን ለሚጋልቧቸው ገዢዎቻቸው ነው" - ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የሚያደርገው የሰራዊት ግንባታ ሂደት አላማው አሸባሪው ህወሓትን ማሸነፍ እንዳልሆነና ይልቁንም ዝግጅቱ እነሡን ለሚጋልቧቸው ሀይሎች እንደሆነ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የሰራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ ተናገሩ፡፡

#ኢፕድ

አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ከተፈናቀሉ ወገኖች ጎን መሆኑን ለመግለጽና ድጋፍ ለማድረግ ዛሬ ኮምቦልቻ ከተማ ገብቷል። አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ከሰሜን ወሎ ዞን ተፈናቅለው በኮምቦልቻ...
16/09/2021

አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ከተፈናቀሉ ወገኖች ጎን መሆኑን ለመግለጽና ድጋፍ ለማድረግ ዛሬ ኮምቦልቻ ከተማ ገብቷል።

አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ከሰሜን ወሎ ዞን ተፈናቅለው በኮምቦልቻ ለተጠለሉ ወገኖች አጋርነቱን ይገልጻል፤ ድጋፍ ያደርጋል ነው የተባለው።
የዜና ምንጭ :- ደቡብ ወሎ ኮሚኒኬሽን

በጸጥታው ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የወጣው መግለጫ የኢትዮጵያን አቋም የሚደግፍ መሆኑ ተገለጸአዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ፕ...
16/09/2021

በጸጥታው ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የወጣው መግለጫ የኢትዮጵያን አቋም የሚደግፍ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የወጣው መግለጫ የኢትዮጵያን አቋም የሚደግፍ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገለጸ።

በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ጽህፈት ቤት አሉ በተባሉ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ የተጠናቀረው ሪፖርት በመጪው ጥቅምት ይፋ እንደሚደረግም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ገልጸዋል።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን÷ በመግለጫቸውም በሳምንቱ የተከወኑ የተለያዩ ጉዳዮችን አስመልክተው አብራርተዋል።

ቱኒዚያ የታላቁ ህዳሴ ግድብን ጉዳይ ወደ ጸጥታው ምክር ቤት ብትወስደውም ምክር ቤቱ ጉዳዩ የልማት ብቻ መሆኑን እንዳሰመረበትም ነው አምባሳደር ዲና የገለጹት።

የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፌ ሉቱንዱላ ከኢትዮጵያ አቻቸው አቶ ደመቀ መኮንን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም የታላቁ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

የኮንጎ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ ለዓባይ ፍትሃዊ አጠቃቀም ሆነ ለድርድሩ ያላትን ጽናት አድንቀው÷ የአፍሪካን ችግር በአፍሪካውያን የሚለውን መርህ ሃገራቸው አጥብቃ እንደምትደግፈው ተናግረዋል።

በሌላ በኩል አምባሳደር ዲና ቱኒዚያ የህዳሴው ግድቡን ጉዳይ ወደ ጸጥታው ምክር ቤት ብትወስደውም ምክር ቤቱ ጉዳዩ የልማት ብቻ መሆኑን አስምሮበታል ብለዋል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ እና ኬንያ መካከል የሃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የውሃ የመስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ጅቡቲን እና ኢትዮጵያን በሃይል ማስተሳሰር በሚቻልበት ጉዳይ ዙሪያ ከጅቡቲ አቻቸው ጋር መወያየታቸውንም አንስተዋል።

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር በጋራ ያካሄደው የሰብዓዊ መብት ጥናት የተጠናቀቀ ሲሆን÷ በመጪው ጥቅምት 22 ላይ ይፋ እንደሚደረግም አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ልዑክ ከተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ጽህፈት ቤት ጋር ተወያይቷል።

ሆኖም ግን ሪፖርቱ ከመውጣቱ በፊት በአሸባሪው የህወሓትቡድን እና በሌሎች አካላት እየተናፈሱ ያሉ አሉባልታዎች ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የኢትዮጵያ መንግስት አስታውቋል።

ኢትዮጵያ አሸባሪው የህውሓት ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች እየፈጸማቸው ያላቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በአለም ዓቀፍ አካላት እና ሚዲያዎች ሽፋን እያገኙ አለመሆኑን ማሳወቋንም በመግለጫቸው ዳሰዋል።

የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የለውጥ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን እና በአሁኑ ወቅት ለዲፕሎማቶች፥ ቆንስላዎች እና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች እየተሰጠ ያለው የአስር ቀን ስልጠና የዚሁ አካል መሆኑን አምባሳደሩ አስረድተዋል።

በወንደሰን አረጋህኝ

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ምንጭ FBC

የሀገር ውስጥ ዜና ጀግንነት የታጋይነት፣ የጽናትና የአሸናፊነት ውጤት ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ Sep 9, 2021

Address

Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Delanta Tube.com posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to Delanta Tube.com:

Share