28/04/2026
📚💐 የምታስበውን ትሆናለህ!📚💐
✍️ ምን እያሰብክ ነው?
ሰው የአስተሳሰቡ ውጤት ነው ይባላል፤ አንተም የምታስበው ነገር ውጤት ነህ፤ መጥፎ ብታስብ መጥፎ ትሆናለህ፤ መልካም ብታስብ መልካም ትሆናለህ። ለመሆኑ የምታስበው ምንድነው?
👉ሰው ቀኑን ሙሉ የሚያስበውን ያንኑ ነው እንደሚባለው፣ ቀኑን ሙሉ እንዴት የብርታት፣ የድፍረት፣ የስኬት ሀሳቦችን ማሰብ እንዳለብህ ትማራለህ።
✍️ የምትመገበውን ነህ!
አእምሮህን ምን እየመገብከው ነው? የሚያበረታቱ፣ ጉልበት የሚሆኑ፣ አይዞህ፣ በርታ፣ ጀግን የሚሉ ሀሳቦችን ወይስ የሚያደክሙ፣ የሚያዝሉ፣ አትችልም የሚሉ ሀሳቦችን ነው?
👉ሰውነትህ በምትመግበው እንደሚዳብረው ሁሉ፣ አእምሮህም በምትመግበው ይፋፋል። አእምሮህን እንዴት እንደምትመግበውና እንደምታደልበው ትማራለህ!
✍️የምትናገረውን ነህ!
የምታስበው የምትናገረው ይሆናል። ምን እየተናገርክ ነው? ውድቀት፣ ሽንፈትና አሉታዊ ወይስ ብርታት፣ ጀግንነት፣ ድፍረትና አዎንታዊ? ንግግርህ ሰዎችን የሚሰብር ነው ወይስ የሚጠግን?
👉የአፍህን ፍሬ ትበላለህና ልክ እንደምትናገረው እንደዚያው ስለምትሆን አንደበትህ መልካም ፍሬ እንዲያፈራ ትማራለህ!
✍️የምታምነውን ነህ!
እምነትህ እንዴት ነው? በራስህ፣ በስራህ፣ በፈጣሪህ፣ በነገሮች ላይ ያለህ እምነት እንዴት ነው? የምታምነው ነገር አካል ይዞ፣ ነፍስ ገዝቶ በእውኑ ይገለጣል። እምነትህ ያለ ጥርጥር ያድንሃል። ጥያቄው ምን እና እንዴት እያመንክ ነው የሚለው ነው።
👉እንዴት የምታምነውን ያንኑ እንደምትሆንና እንደምታገኝ ትማራለህ።
✍️ትናንትናህን ነህ!
የትናንት ሀሳቦችህ፣ ምግቦችህ፣ እምነቶችህና ንግግሮችህ ውጤት ነህ! ትናንት ራስህን ምን ትመግበው ነበር? ትናንትናህ ነው የዛሬውን አንተን የፈጠረህ። የዛሬህ ደግሞ የነገውን አንተን ይፈጥራል።
👉እንዴት ትናትናህ ዛሬህን እንደፈጠረና እንዴት ዛሬህ ነገህን እንደሚፈጥር ትማራለህ።
✍️ቆም ብለህ አስብ
ምን እያደረግክ ነው? ትናንትን እንዴት ነው የመጣኸው? ዛሬስ ምን እያሰብክ፣ ምን እያደረግክ፣ ምን እየሆንክ ነው? ወርቃማውን አሁንና ነገንስ እንዴት እያሰብከው ነው?
👉ይህች ቅጽበት ቆም ብለህ በፍጥነት የምታስብባት ቅጽበት ናት፤ ለምን ያልክ እንደሆነ ምክንያቱም ከዚህች ቅጽበት ጀምሮ የምታስበውን ትሆናለህና!
አዎ ያለጥርጥር የምታስበውን ትሆናለህ!🫵 እወቀው፤ አሁን የምታስበውን አሁንና ነገ ትሆናለህ፤ አሁን አስተሳሰብህን ብትቀይር አሁንህና ነገህ ይቀየራል። የምታስበውን በመቀየር ራስህን እስከ ወዲያኛው ቀይር!!