Makbel Afomiya

Makbel Afomiya some musician personal information and image

15/12/2019
My 2nd new single music.
16/05/2018

My 2nd new single music.

23/09/2017
07/07/2017

ቆንጂት አረፋፍዳ መጣች ከመሻሸ፣
ልቤ ሌላ ወዶ ከሷ እንደሸሸ፣
ስፈልጋት ኖሬ ስትርቀኝ ስጎዳ፣
ፍቅሬ በሷ ብሶ መጣች አረፋፍዳ፡
ወለም ካለው ልብሽ ድንገት ከዘመመ፣
በፍቅር ተወግቶ ጸንቶ ከታመመ፣
አይገኝ ወጌሻ ለልብ ስብራት፣
አሽቶ የሚመልስ ከቀደመው ድነት፣
ከተጎዳ ልብሽ ፍቅር ካቆሰለው፣
ደግመሽ አፍቅሪበት እሾህን በሾህ ነው፡፡

ማክ ለ ውዴ

19/12/2016

ወንድ ልጅ አራሱን ነጥሎ ይኖር ዘንድ ፣
ፈፅሞ አይቻለዉም ፈጣሪዉም አይወድ፤
ካለ ግራ ጎኑ ኑሮዉንም አይለምድ ፤
ብለህ የፃፍከዉን ትዛዝክን ሰምቼ ፤
ግራ ጎኔን ላገኝ ልኖር ተደስቼ፤
ምድሪቷን በሙሉ ፍለጋ ጀመርኩኝ ፤
ሺዎችን ቀርቤ ሺዎችን አራኩኝ፤
ሺዎችን ወድጄ ሺዎችን ጠላሁኝ ፤
ግና ብቸኝነቴን የምታስረሳ ከኔነቴ የምትጥም፤ አንድ አነኳን አጣሁኝ ከ እኔ የምትገጥም ፤
ግና በዚህ የተነሳ
አፈር እንደበላው አንደ ዛገ ብረት፤
ምስጥ አንደበላዉ አንደቆነቆነ አንጨት፤
ልቤ ወስጡ ዘጉኖ በሸር አና ክህደት ፤
አራሡን ደብቆ ሺ ዘመን አልፍታል፤
አንኳን ለሠዉ ሊኖር ለራሡም ከብዶታል ፤
እናማ እናማ ፈጣሪ
በልቤ ሰብራት ሀዘን ካዘንክልኝ፤
አባክህ ፈጣሪ ዉለታ ዋልልኝ ፤
ነፍሴ አንድትለመልም ልበሰም አነዲበረታ፤
ያቺ ግራ ጎኔን የኑሮዬን ዋልታ ፤
ፈልገክ ላክልኝ ካለችበት ቦታ፡፡
ማክ(ብቸኛው ናፋቂሽ)

28/09/2016

የፍቅር ምክንያት ክፍተትን መሙላት ነው ኣዳሞች የግራ ኣጥንታቸውን ስንፈልጉ ሄዋኖች ደሞ መነሻችንን እንፈልጋለን ሲሉ ......................የፍለጋችን መጨረሻ ደሞ ፍቅር ይሆናል

11/08/2016

((((((ጨረቃን ምንቃኛት))))))
እንደ ምን ደስ ይላል የልጅነት ፍቅር
ካንቺም ከኔ ልብ ወስጥ ሁሌ ማይቀየር፤
ያኔ ልጅ እያለን ድሮ ስንጫወት
አንገቴን ስታቅፊው የነበረኝ ስሜት፤
በስስ ከንፈሮችሽ ጉንጮቼን ስትስሚኝ
ከፊት ካፍጫዬ ላብ ች-ፍ ሲልብኝ፡፡
ሮጠሸ ስታመልጪኝ እኔ ሳባርርሽ
ቃል ስትጠብቂ አይን አይኔን እያየሽ፤
እጄ ሲንቀጠቀጥ አንቺም ስትፈሪ
አፌ ሲርበተበት ልትሄጂ ስትዞሪ፤
ቃል ካፌ ሳይወጣ ባፍረት ተተብትቤ
ሳልነግርሽ ተለየሽ ሳላይሽ ጠግቤ፡፡
(((***ቁጭት!!!***)))
ያ ፍቅር ያ ደስታ በውስጥ የሰወረነው
ፈንድቶ ሳይወጣ በሀፍረት የገደብነው፤
ምነው በነበረ እድሜ ልክ በኖረ እያኩኝ በምኞት
ዘመን ተቆጠረ ዳግም ላልመልሰው እድሌን ስረግማት፡፡
እናማ፡-
በህይወት አጋጣሚ እንዲህ ተለያይተን
ካላሰብነው እቅፍ ጎጆ ውስጥ ተከተን፤
ወጥተን ምሽት ምሽት ጨረቃን ምንቃኛት
ቢመለስ ብለን ነው ውዴ ያኔው ህይወት
አብረን ያሳለፍነው አይናችን ሲከፈት፡፡

10/08/2016

***ወድጄ አላነባው***
ወድጄ አላነባው ፈልጌ አልተከዝኩ፣
ፍቅር አሳውሮኝ የሰው ሰው አፈቀርኩ፣
አይወጡበት ገባው እንዳይደክሙት ደከምኩ፣
ላልነሳ ወደኩ፣
ላልረታ ተሸነፍኩ፣
በክፉ ተለከፍኩ፣
አይ ፍቅር ክፋቱ ከምን ወስዶ ጣለኝ፣
ደስታ ፈገግታዬን ጨክኖ ነጠቀኝ፣
ላልደርስ አስከተለኝ፣
ብኩን ሰው አረገኝ፣
ቀን አጨለመብኝ፣
ተስፋ አጠለሸብኝ፣
የኔ ባይ ያላትን የኔ ትሁን አልኩኝ፣
ላላገኝ ተመኘው ላልነካው አለምኩት፣
ተቀብዬ ኖርኩኝ ፍቅርን በሽንፈት፣
እንዴት መከራ ነው የሰው ሰው ማፈቀሩ፣
የራስ ላያረጉ ሲያስሱ መኖሩ፣
ከእጅ ላይገባ ሰርክ አለም መዞሩ፣
አይ ፍቅር ድብቁ ፍቅር ጉራንጉሩ፣
ያገሌን ሲያስመኘኝ ወይ አለማፈሩ፣
ምን ብዬ አወራለው ከማንስ መክራለው፣
ለምላስ የሚፋጅ ለጆሮ መርዶ ነው፣
ፍቅር የቱጋነው ቀዝቅዛህ አሳየኝ፣
አልቻልኩም ራራልኝ የእስካሁኑ ፈጀኝ፣
አረርኩ አደበንከኝ፣
ሰነፍኩ ከንቱ አደረከኝ፣
ባይበስሌ እንጀራ በጠኔ ታረዝኩኝ፣
በልቤ ዕንቅቡ ሀዘንን ሰፈርኩኝ፣
ከጎተራዬ ውስጥ አላከማቸሁኝ፣
የጎረቤቴን ሳይ ይኸው በርሀብ ሞትኩኝ፣
አታንባ አትበሉኝ ፈልጌ አላነባው፣
እንዲ ምብከነከን በሰው ሰው ፍቅር ነው፡፡

Address

Addis Abeba
Addis Ababa

Telephone

+251913850372

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Makbel Afomiya posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share