Biniyam asrat getachew

Biniyam asrat getachew personal blogger ዶ/ር ቢኒያም አስራት

06/05/2022

#እድሜያቸው ከ 1-2 አመት ያሉ #ህፃናትን ምን አይነት ምግብ እንመግባቸው❓️ በቀን ስንት ጊዜ❓️
💖🔹🔹🔹🔹💖🔹🔹🔹🔹💖🔹🔹🔹🔹

👉 ህፃናት አንድ አመት ከሞላቸው በኋላ ዕድገታቸው ቀስ ብሎ ስለሚሄድ የምግብ ፍላጎታቸው በመጠኑም ቢሆን ሊቀንስ ይቺላል ይሄ ተፈጥሯዊ ነገር ነው::

👉 ሆኖም ግን በተቻለ መጠን የተለያዩ ጤናማ እና የተመጣጠኑ ምግቦችን እንዲመገቡ ማበረታታት እና አዳዲስ ጣእሞችን እንዲሞክሩ ማድረግ ያስፈልጋል::

👉 አንዳንዴ በዝህ እድሜ ያሉ ህፃናት ከራሳቸው ምግብ ይልቅ የቤተሰቡ ምግብ ሊመርጡ ይቺላሉ :: ይሄም በሳይንሱ የሚመከር የሚጠበቅ ስለሆነ የቤተሰቡን ምግብ ቀስ በቀስ ማስለመድ ተገቢ እና ተፈጥሯዊ ነው❗️

⚠️ ሆኖም የቤተሰቡን ምግብ ብቻ መስጠት ማግኘት ያለባቸውን ንጥር ነገሮች ሊያጡ ስለሚችሉ የራሳቸውን ምግቦች እና የቤተሰቡ ምግብ እያፈራረቁ መሰጠት ይቺላል::

🛑 #በቀን ስንት ጊዜ ነው መብላት ያለባቸው❓️

👉 ከ 1-2 አመት ያሉ ህፃናት በቀን 3 ቋሚ ምግቦች እና 2 እንደ መክሰስ የሚሆኑ ምግቦችን ማግኘት አለባቸው

👉 እነዝህ ከላይ ከተጠቀሱ ምግቦች በተጨማሪ የእናት ጡት ወተት እስከ 2 አመት ቢቀጥሉ የበሽታ መከላከል አቅማቸው ጠንካራ ይሆናል::

🛑 #ጥያቄ: #መጀመርያ ጡት ነው ማጥባት ያለብኝ ወይስ ምግቡን ልስጠው❓️

🛑 #መልሱ : #መጀመርያ ምግቡን በ አግባቡ ይመግቡ ቀጥሎ ደሞ ጡት ያጥቡ ወይም ወተት ይስጡ ❗️

👉 ይሄንን ማድረግ ካልተቻለ ግን የጣሳ(ፎርሙላ)ወይም የላም ወተት(የደም ማነስ ከሌለባቸው እና የጣሳ ወተት ማግኘት ካልተቻለ) መስጠት ይቻላል::

🛑 #ምን #አይነት #ምግቦች እንመግባቸው❓️

👉 በዝህ የእድሜ ክልል ያሉ ህፃናት የተመጣጠነ ምግብ መመገብ አለባቸው::

1. ከ ኃይል ሰጪ ምግቦች(carbohydrate)
🔺 ከተለያዩ የእህል ዘሮች የሚዘጋጀውን ምጥን በገንፎ መልክ ማዘጋጀት እና መመገብ
🔺 ገንፎውን ላይ እንቁላል ወተት እና ቅቤ መጨመር
🔺 የተፈጩ ድንች ካሮት ቀይ ስር ብሮኮሊ መመገብ
🔺 ቤት ዉስጥ የሚዘጋጁ እና ስኳር ያልበዛበት ጁስ
🔺 ለስላሳ መጠጦችን ጣፋጭ ምግቦች እና የታሸጉ ጁሶችን በፍፁም አያስለምዱ❗️

2. ከ ሰውነት ገንቢ(Protein)

🔹 የተቀቀለ እንቁላል
🔹 በደንብ የሰለ ስጋ (የበግ የበሬ የአሳ እና የዶሮ)
🔹 ወተት (የእናት> የ ጣሳ> የላም )
🔹 አተር ሽንበራ ባቄላ ቦሎቄ በተለያየ አዘገጃጀት ይመግቡ

⚠️ #አስተውሉ⚠️

🛑 ህፃናት የጣሳም ይሁን የላም ወተት በቀን ከ 500 ሲሲ (ከ 3 ኩባያ)በላይ መውሰድ የለባቸውም‼️ ምክንያቱም የደም ማነስ ድርቀት እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ሊያመጡ ይቺላሉ‼️

3. ቅባት /ዘይት
🔸 ቅቤ እና ዘይት ከተለያዩ ምግቦች ዉስጥ መጨመር
🔸 ጤናማ ያልሆኑ ክባቶች (የሚረጉ እና ከእንስሳት ስብ የሚገኙትን ) ያስወግዱ‼️
🔸 ጤናማ ቅባቶችን ከወተት እና ከአቦካዶ ማግኘት ይቻላል

🛑 🛑 #የአሳ #ዘይት መቼ ነው መጀመር ያለብን❓️

👉 የአሳ ዘይት ለአይምሮ እና ለሰውነት እድገት በጣም ጠቃሚ ነው :: ይሄ ማለት ግን ሁሉም ህፃናት የታሸገ እና የሚሸጥውን የአሳ ዘይት ግዴታ መጠቀም አለባቸው ማለት አይደልም ❗️

👉 የአሳውን ዘይት ከ አሳ ስጋ ዉስጥ ማግኘትም ይቻላል❗️ እና ለልጆዎ የአሳን ስጋ ከ 6 ወር ጀምሮ መስጠት ማለማመድ ይመከራል ::

4. ቫይታሚኖች እና ሚንራሎች(ዋና ዋናዎቹ)

✔️ ቫይታሚን ኤ: ከድንች ካሮት ብሮኮሊ ጎመን ወተት
✔️ ቫይታሚን ቢ: ከአትክልቶች ወተት እና
✔️ ቫይታሚን ሲ:ከአረንጉአዴ እና ቢጫ የጓሮ አትክልት ከተለያዩ ፍራፍሬዎች )
✔️ ቫይታሚን ዲ :ከፀሐይ እና እንስሳት ተዋፆዎች
✔️ ፎሌት : ከአቦካዶ ጎመን ምስር እና እንስሳት ተዋፆዎች
✔️ አይረን : እንስሳት ተዋፆዎች በተለይ ቀይ የበሬ ስጋ ጉበት እና ኩላሊት ስጋ

5. ፋይበር(ቃጮነት ያላቸው ምግቦች)

👉 ፋይበር እስከ መጨረሻው የማያደቅ የእፅዋት ክፍል ሲሆን ከትኛዉም አትክልት እና ፍራፍሬ ዉስጥ የሚገኝ ሲሆን ዋና ጥቅሙ ድርቀትን መከላከል እና የ አንጀት ስራን ማፋጠን ነው::
👉 ካሮት ድንች ጎመን ሙዝ አቦካዶ.... ዉስጥ ይገኛል

🛑 ከ 1-2 አመት አሉ #ህፃናት በአንድ ጊዜ ምን ያህል #ምግብ ነው መመገብ ያለባቸው❓️ እምቢ ሲሉስ ምንድነው የምናረገው❓️

✍️ በዝህ እድሜ ክልል ዉስጥ ያሉ ህፃናት 70 ሲሲ የሚይዝ ኩባያ ሙሉውን ወይም 3/4ኛውን እንዲወስዱ ይመከራል::
✍️ ይሄ ግን ሁሌ ይሳካል ማለት አይደልም❗️ቀስ ብለው በትዕግስት በጨዋታ ይሞክሩ ጊዜ ይስጡት::
✍️ በፍቅር እንጂ በ ማስገደድ መሆን የለበትም‼️
✍️ የህፃናት የምግብ ፍላጎት ከ ቀን ቀን ሊለያይ ይቺላል እና ብዙ መጨነቅ ተገቢ አይደልም

🛑" ግን #ልጄ #በትክክል የሚበቃውን ያህል እየተመገበ መሆኑን እና አለመሆኑን ግን በምን አውቃለሁ❓️ ጡቴስ ለልጄ በቂ መሆኑን እና አለመሆኑ በምን አውቃለሁ❓️
🛑 መልሱን በነገው ዕለተ በቴሌግራም ቻናላችን ላይ እናቀርባለን:: ቴሌግራማችንን Join ያርጉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
🔹 ቴሌግራም : t.me/doctorfasil

🔷 ፌስ ቡክ: fb.me/drfasilpediatrician

✍️ አዘጋጅ: ዶ/ር ፋሲል መንበረ
(በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም ሜድካል ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር እና የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም)

👨‍⚕️ ለልጆዎ ማንኛዉም አይነት ሕክምና ለማድረግ ወይም ክትትል ለማድረግ ከፈለጉ በእዝህ ስልክ ቁጥር ደውለው ቀጠሮ ያስይዙ ::👇👇👇

☎️ +251984650912

👉 ወይም ዶ/ር ፋሲልን ለማማከር ከፈለጉ በ "Wecare ET patient" Application(መተግበሪያ) ከ google play ላይ download አርገው በመጠቀም እና ማማከር ይቺላሉ ::

🔷 መተግበርያውን ለማውረድ ከታች ያለውን link ይጫኑ👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient

🛑 ስለ መተግበርያው አጠቃቀም ለመጠየቅ እና ቀጠሮ ለማስያዝ 9394 ደውለው ይጠይቁ::

የኩላሊት ጠጠርየጤና መረጃዎች እንዲደርስዎsubscribe to our YouTube channel
07/09/2021

የኩላሊት ጠጠር
የጤና መረጃዎች እንዲደርስዎ
subscribe to our YouTube channel

የ ኩላሊት ጠጠር መንስኤ፣ ምልክቶች እና ህክምና kidney stone |NERI TENA ኔሪ ጤና|ሰላም፨ የ ኔሪ ጤና ቲዩብ ቤተሰቦች ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማደርግ በየወቅቱ የሚወጡ የጤና መረጃዎችን ያግኙ.....

የ YouTube ቻናሉን subscribe በማድረግ የጤና መረጃዎችን ያግኙ
29/08/2021

የ YouTube ቻናሉን subscribe በማድረግ የጤና መረጃዎችን ያግኙ

ሰላም፨ የ ኔሪ ጤና ቲዩብ ቤተሰቦች ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማደርግ በየወቅቱ የሚወጡ የጤና መረጃዎችን ያግኙ። ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር ያድርጉት።Hello family! subscribe and share our YOU TUBE channel ...

Hi friends This is my new simple educational channel Please subscribe and share 🙏🙏🙏
19/07/2021

Hi friends
This is my new simple educational channel
Please subscribe and share 🙏🙏🙏

ሰላም፨ የ ኔሪ ጤና ቲዩብ ቤተሰቦች ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማደርግ በየወቅቱ የሚወጡ የጤና መረጃዎችን ያግኙ። ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር ያድርጉት።Hello family! subscribe and share our YOU TUBE channel

ለፈጣን የጤና መረጃ ኔሪ ጤና NERI TENA TUBEsubscribe my youtube
18/07/2021

ለፈጣን የጤና መረጃ
ኔሪ ጤና NERI TENA TUBE
subscribe my youtube

የአስም በሽታ መንስኤ እና ምልክቶቹ ASTHMA ኔሪ ጤና NERI TENA TUBE

መልካም ስቅለት
30/04/2021

መልካም ስቅለት

Coming soon 👌👌👍Aster Abebe በዘመኔ አያለሁ !!❤🔊Can't wait
27/11/2020

Coming soon 👌👌👍
Aster Abebe
በዘመኔ አያለሁ !!❤🔊
Can't wait

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Biniyam asrat getachew posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share