25/03/2026
ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ልታውቋቸው የሚገቡ ሰዎች — አወንታ በርሲሳ (ገዛኸኝ ተሬሳ) 👏🏿👏🏿👏🏿✨
በሶሻል ሚዲያ ስሙ Awnta Bersisa፣ በእውነተኛ ስሙ ገዛኸኝ ተሬሳ ይባላል። የማደንቀው ብቻ ሳይሆን በድፍረቱና ለህዝብ ባለው ተቆርቋሪነት ሁሌም ከልቤ ያለ ሰው ነው!
አወንታ ቀደም ሲል በመንግስት መሥሪያ ቤት በኦዲተርነት ይሰራ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ በማዋል በደልንና ማጭበርበርን በማጋለጥ ይታወቃል።
ለምን ልታውቁት ይገባል?
📍 አጭበርባሪዎችን ነቅቶ ያጋልጣል፦ በቅርቡ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ያጭበረበረውን "ፊንቴክ" ድርጅት ቀድሞ በማጋለጥ የብዙዎችን ገንዘብ ታድጓል። በዚህም የተነሳ ከባድ ዛቻና ማስፈራሪያ ደርሶበታል፤ እንደ መንሱር ጀማል ያሉ አካላት ሳይቀሩ ሊያቃልሉትና ሊሰድቡት ቢሞክሩም እርሱ ግን ከአላማው ፍንክች አላለም።
📍 የጤና ተቋማት ዘረፋ፦ በቅርቡ ደግሞ የግል የጤና ተቋማት ህዝቡን እንዴት እንደሚበዘብዙ በዝርዝር አጋልጧል።
📍 የሰው ንግድ (Human Trafficking)፦ "ውጭ ሀገር እንልካችኋለን" እያሉ የዜጎችን ተስፋና ገንዘብ የሚበዘብዙትን ደላሎች አርቲስቶችና ታዋቂ ሰዎችን ጭምብል እየገለጠ ይገኛል።
አወንታ ለዚህ ስራው እስከ ህይወት መስዋዕትነት ሊያደርስ የሚችል ትልቅ ዋጋ እየከፈለ ነው። እንደነዚህ አይነት ለህዝብ የሚቆረቆሩና እውነትን የሚናገሩ ሰዎች ሊበረታቱና ሊደገፉ ይገባል! 🙌
እናንተስ ስለ አወንታ በርሲሳ ስራዎች ምን ትላላችሁ? ሀሳባችሁን በኮሜንት አጋሩኝ።
❤️Addis🌕ut Media❤️