ኢትኤል TUBE

ኢትኤል TUBE Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ኢትኤል TUBE, Arts and entertainment, Addis Ababa.

ድምጽ አልባ ፊደላትፀጉሩን አንጨብሮ ፂሙን አጎፍሮጥግ ተቀምጦ ለሚታየኝ ወጣት፣ሂድና ታዘዘው ስጠው አንድ ድራፍት፣ቅዳለት ደብል ጂን ሃሳቡን ይርሳበት።በፂሙ መጎፈር በፀጉሩ መንጨብረር፣ቁጥር ፈ...
05/07/2021

ድምጽ አልባ ፊደላት

ፀጉሩን አንጨብሮ ፂሙን አጎፍሮ
ጥግ ተቀምጦ ለሚታየኝ ወጣት፣
ሂድና ታዘዘው ስጠው አንድ ድራፍት፣
ቅዳለት ደብል ጂን ሃሳቡን ይርሳበት።
በፂሙ መጎፈር በፀጉሩ መንጨብረር፣
ቁጥር ፈታ በሚል በግንባሩ መስመር፣
ይታየኛል ቋንቃ ይታየኛል ነገር።
እዛም ከጨለማው ብቸኝነት ውጧት፣
ሲጋራዋን ይዛ ለቆመችው ወጣት፣
ሂድና ታዘዛት የሚጠጣ ስጣት።
ምጋ በተፋችው በጭሶቹ መሃል፣
ሴትነት ሲበደል እህትነት ሲጣል፣
እናትነት ሲጎድል፣
ይታየኛል ቋንቃ ይታየኛል ፊደል።

ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም

13/06/2021

ሁለቱ መላጦች

ሁለት በራ ሠዎች ሲያልፉ በጎዳና
ዕቃ መሬት ወድቆ ብልጭ ሲል ያዩና
ተሽቀዳድመው ሄደው ከቦታው ሲደርሱ
ተፎካከሩበት ሁለቱም ሊያነሱ።

በኀላም ተማተው በጥፊ በጡጫ
አንደኛው ነጠቀ በጉልበቱ ብልጫ
አገላበጠና ቢመለከት ፈጥኖ
ዕቃውን አገኘው ማበጠሪያ ሆኖ።

እስኪ ሁላችሁም በሉ ፍረዱት
እሱ ራሱ በራ ፀጉር የለበት
ሮጦ ተማቶ ቀምቶ ቢያመጣ
ምን ያደርግለታል ሚዶ ለመላጣ?
ሰዎች ይፋጃሉ አስበው ሳይፈርዱ
የተጣሉበትን ጥቅሙን ሣይረዱ
ከመጣላት በፊት ከመቀያየም
የነገሩን ፍሬ መረዳት መልካም።

ከ(ዶ/ር ከበደ ሚካኤል)

Like & Share our Page

ደሥታ ቢራቢሮደስታ  ቢራ  ቢሮ                    እኔ  ጀብደኛ  አዳኝ  ስትከንፊ  ስከተል             እድሜ መንገድ ከዳኝሳሎኔ  ዱር  ሆኖ በግንድ በቅርንጫፍ በሣር ተሸ...
12/06/2021

ደሥታ ቢራቢሮ

ደስታ ቢራ ቢሮ
እኔ ጀብደኛ አዳኝ
ስትከንፊ ስከተል
እድሜ መንገድ ከዳኝ
ሳሎኔ ዱር ሆኖ
በግንድ በቅርንጫፍ በሣር ተሸፍኖ
ከኮርኒሴ በታች ወፍራም
ጭጋግ ሰፍኖ
እኔም እድሜ ልኬን የማላድግ ህፃን
እድገቱ
ቁመቱ
ባሥማት የተገታ
ነጋ ጠባ ዝላይ ፤ሁለዜ ጨዋታ
በሄደበት ለማጅ
ነፋሥን በወንፊት ፤
ዉሀን በጨርቅ አጥማጅ
አመት ታመት ጮርቃ
ለሹመት ማይታጭ፤
ለዋሥ የማይበቃ
ሆኜ ቀረሁ በቃ ?

ደስታ ቢራቢሮ
በጣቶቼ መሀል ቀለምሽ ተነነ፣
ተከትየሽ ስከንፍ ላባዬ በነነ፣
ክንፌ ተመለጠ፣
ጥላሽን ሳሳድድ ዘመኔ አመለጠ።

በዕዉቀቱ ስዩም

Like & Share our Page

የኢትዮጵያ ጸሐፊ እና ፖለቲከኛ.. ...ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ) ከአባታቸው ከቄስ ዓለማየሁ ሰለሞን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ደስታ ዓለሙ በደብረ ማርቆስ አውራጃ በጎዛመ...
22/05/2021

የኢትዮጵያ ጸሐፊ እና ፖለቲከኛ.. ...
ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ) ከአባታቸው ከቄስ ዓለማየሁ ሰለሞን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ደስታ ዓለሙ በደብረ ማርቆስ አውራጃ በጎዛመን ወረዳ በእንጾር ኪዳነ ምኅረት ቀበሌ በጥቅምት ፯ ቀን 1902 ዓ.ም. ተወለዱ። ገና በጨቅላ እድሜያቸው በቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን ትምህርት በቤተሰባቸው አጠገብና ባባታቸው አገር ደብረኤልያስ ሄደው የግእዝ ትምሕርት ቤት ቅኔ ተቀኝተዋል። የቤተክርስቲያን ስርዐታትንና መንፈሳዊ ትምህርትን በጎጃም ገዳማት በደብረ ኤልያስ፣ በደብረ ወርቅና በዲማ ከቀሰሙ በኋላ ወደ በ፲፱፻፲፰ ዓ.ም.
አዲስ አበባ በመሄድ በ ስዊድን ሚሽነሪ ትምህርት ቤት በኋላም በራስ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታተሉ። ለትንሽ ጊዜ በአስተማሪነት ሥራ ተሰማርተው እንዳገለገሉ የፋሽስት ጣሊያን ወረራ ተከሰተ።
የ ኢጣልያ ወረራ ሲከሰት ከልዑል ራስ ዕምሩ ኃይለ ሥላሴ ጦር ጋር በምዕራብ ኢትዮጵያ በአርበኝነት ሲዋጉ ቆይተው በመያዛቸው ጣሊያን ከልዑል ራስ ዕምሩ ጋር በግዞት ለሰባት ዓመታት በፖንዞ ደሴት ና በ ሊፓሪ ደሴት ታስረው ቆይተዋል።
ከዚያም የተባባሪ ኃያላት ወታደሮች በ 1935 ዓ.ም. ሲያስመልጧቸው በተመለሱበት ጊዜ በትምህርታቸው እንደገና በኦክስፎርድ ከገፉ በኋላ በተለያዩ የ መንግስት ተቋማት በተለይም በትምህርት ሚኒስቴር ለረጅም ጊዜ አገልግለዋል።
1936 - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሠራተኛ
1937 - 1938 - የኢትዮጵያ ቆንሱል በኢየሩሳሌም
1938 - በ International Telecommunications Conference
አትላንቲክ ከተማ፣ ኒው ጄርዚ ወኪል
1938- 1942 - በተባበሩት መንግሥታት ቢሮ ኒው ዮርክ ሠራተኛ
1942- 1948 - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዳይረክተርና ምክትል
1948- 1952 - የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሰደር
1952 - የትምህርት ሚኒስትር
1952- 1957 - የኢትዮጵያ አምባሰደር ወደ
እንግሊዝና ሆላንድ
1957- 1958 - የልማት ሚኒስትር
1960 - 1966 - ሴናቶር
ሀዲስ ዓለማየሁ በርካታ የስነጽሑፍ ሥራዋችን አበርክተዋል። ከነዚህም ውስጥ ታላቅ አድናቆትንና እውቅናን ያተረፈው ሥራቸው ፍቅር እስከ መቃብር ( 1958) በሁለት የተለያዩ መደቦች ውስጥ የሚገኙ የሁለት ሰዎች የፍቅር ታሪክ ላይ ሲያተኩር፤ በጊዜው የነበረውን ወግና ልማድ ይገልጻል። እንዲሁም በ1970 ወንጀለኛው ዳኛ በ 1980 ደግሞ ስለ ማህበራዊ ጉዳዮችና ስለ ጣሊያን ውርስ የሚዳስሰውን የልም እዣት የተሰኙትን ልብ ወለድ ታሪኮች ለንባብ አቅርባዋል።
ከዚህ ባሻገር:
የአበሻና የወደኋላ ጋብቻ - ተውኔት
ተረት ተረት የመሰረት
ትዝታ
የተሰኙት ጽሁፎችና የሌሎች በርካታ ሥራዎች ባለቤት ናቸው።
ሀዲስ ዓለማየሁ በኢትዮጵያ የስነ ጽሑፍ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማበርከታቸው ከ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዶክቶርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል። ደራሲው በ ኅዳር 26 ቀን 1996 ዓ.ም. በ94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ሃዲስ በዝነኛው መጽሓፋቸው ያስተዋወቁትን የሞክሼ ፊደላት ቅነሳ ከተቃወሙት ኣንዱ ዶ/ር
ኣበራ ሞላ ናቸው።
ፍቅር እስከ መቃብር ዋቢ መጻሕፍት
Like & Share
TUBE

የዛሬው ቅኝታችን በአለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ ISS ላይ ያተኮረ ነው።ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን ሙሉ ቪዲዮውን ይመልከቱ።Like & Share👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇ETHEL TUBE
17/05/2021

የዛሬው ቅኝታችን በአለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ ISS ላይ ያተኮረ ነው።
ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን ሙሉ ቪዲዮውን ይመልከቱ።
Like & Share
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

ETHEL TUBE

LIKE,SHARE AND SUBSCRIBE

ስለ UFO ምን ያህል ያውቃሉ?
01/03/2021

ስለ UFO ምን ያህል ያውቃሉ?

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢትኤል TUBE posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share