03/07/2026
በአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተደራጁና የልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ ዋና መምሪያ ኃላፊ የነበሩት ኮማንደር መስፍን በላቸው ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የቀብር ስነ ስርዓታቸውም ዕሁድ ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 5:00 በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የሚፈጸም ይሆናል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በአመራሩ ህልፈት የተሠማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለስራ ባልደረቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል።
Addis Ababa Police