Africa Citizen

Africa Citizen የጥበብ ማዕድ የሚቀርብበት ገፅ ሙዚቃ ግጥም ስዕል ኮርኳሪ ገ?

ምኒሊክ አደባባይAfrica Citizen
02/03/2022

ምኒሊክ አደባባይ
Africa Citizen

Africa Citizen
01/03/2022

Africa Citizen

AfricaCitizen
01/03/2022

AfricaCitizen

የሰው ልጅ ክቡርሰው መሆን ክቡርሰው ሞቷል ሰው ሊያድንሰውን ሲያከብርበደግነት  በፍቅር በክብር ተጠርቶ በክብር ይሄዳል  ሰው ሊኖር ሰውሞቶ የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት ሰው ተከፍሎበታል ከ...
28/02/2022

የሰው ልጅ ክቡር
ሰው መሆን ክቡር
ሰው ሞቷል ሰው ሊያድን
ሰውን ሲያከብር
በደግነት በፍቅር በክብር ተጠርቶ
በክብር ይሄዳል ሰው ሊኖር ሰውሞቶ
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ከአጥንት
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር
ትናገር አድዋ ትናገር ትመስክር
ትናገር አድዋ ትናገር አገሬ
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ
በኩራት በክብር በደስታ በፍቅር በድል እኖራለሁ ይኸው በቀን በቀን
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትናንት
መቼ ተነሱና የወዳደቁት
ምስጋና ለእነሱ ለአድዋ ጀግኖች
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች
የጥቁር ድል አምባ አድዋአፍሪካ
እምዬ ኢትዮጵያ ተናገሪ
የድል ታሪክሽን አውሪ
እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ)
Africa Citizen

26/02/2022
ተችሏል!!! ይሄ ተውልድ የራሱን ታሪክ በላቡ ሰርቷልAfrica Citizen
20/02/2022

ተችሏል!!!
ይሄ ተውልድ የራሱን ታሪክ በላቡ ሰርቷል
Africa Citizen

የፍቅር ፍልስፍናጅረቶች ከወንዞች ጋርየሙጥን ብለው….. ተጣምረውወንዞችም ውቅያኖሶችን አቅፈውየሰማየ ሰማያት ንፋስጣፋጭ ስሜት ሲዋሃደው….ተመልከችውከቶ አንድም ነገርበአለም ላይ ያላቻ ጓደኛሆኖ...
13/02/2022

የፍቅር ፍልስፍና

ጅረቶች ከወንዞች ጋር
የሙጥን ብለው….. ተጣምረው
ወንዞችም ውቅያኖሶችን አቅፈው
የሰማየ ሰማያት ንፋስ
ጣፋጭ ስሜት ሲዋሃደው….
ተመልከችው
ከቶ አንድም ነገር
በአለም ላይ ያላቻ ጓደኛ
ሆኖ አይገኝም ብቸኛ
በውስጠ ሚስጥር ህላዌው
ይጣመራል ሁሉም በውል
በአንድ መንፈስ በአንድ ቃና
ስጋና ደሙን ሲያዋውል፡፡
እኔና አንቺስ ምን አለበት
አንድ ብንሆን ብናውቅበት
እንደመሶብ ከግጣሙ
ሰማያት ምድርን ሲስሙ…..
እይው ጣእሙ፡፡
ማዕበሎችን እያቸው
ባህር ላይ ሲሽኮረመሙ
ሲላላሱ አንዱ ባንዱ ውስጥ ሲሟሙ
አንዱ ማእበል አንደኛውን
አቅፎት ሲሄድ አቻውን….
እይው በሞቴ ጣእሙን፡፡
ደሞም የፍቅር ጡር ጣጣ
ሴቴ አበባ ያለወንዱ፤
አበባነቷ ቅጥ ሲያጣ
ወንዴ አበባም ያለሴቷ
በፀሀይ ሀሩር ሲቀጣ
እይው ቆንጅት እይውማ
ልቦና ፍቅር ሲጠማ
የፀሀይ ብርሀን ጠዋት የመሬትን ከንፈር ሲስም
በሙቀት እየዳበሰ ፈገግታዋን ሲያለመልም
ለዛው ሲፈካ ሲተም
የጨረቃ ጨረር ሞገድ
የባህርን ራቁት ገላ
በምሽት የእንቅልፍ ሰዓት
ይደበዝዛል እያጠላ
ስለዚህ አስተውይው
እኔን ሁኝ አንቺን ልሁን
በደም ስርሽ ደሜ ይፍሰስ፤
በደም ስርሽ ደሜ ይሁን፤
አንድ እንሁን፡፡
ገጣሚና ሰአሊ ገብረ ክርስቶስ ደስታ

አፍሪካዊውን ኮከብ በወፍ በረር"ጊታር ስትጫወት ሰማዩ ይከፈታል እውቀት እና ኃይል ወደ ውስጥህ ይገባል"ማሊያዊዉ ሙዚቀኛ አሊ ፋልካ ቱሬ  በ1939 በማሊ ሰሜናዊ ክፍል ትንሽ መንደር ውስጥ ተ...
10/02/2022

አፍሪካዊውን ኮከብ በወፍ በረር
"ጊታር ስትጫወት ሰማዩ ይከፈታል እውቀት እና ኃይል ወደ ውስጥህ ይገባል"
ማሊያዊዉ ሙዚቀኛ አሊ ፋልካ ቱሬ
በ1939 በማሊ ሰሜናዊ ክፍል ትንሽ መንደር ውስጥ ተወለደ ብዙ የሙዚቃ መሳሪያ እንደሚጫወት ይነገራል በአፍሪካም በአለምም ተደማጭና ተወዳጅ ድምፃዊም መሆኑ ተመስክሮለታል፡፡
የማሊን የሀገረሰብ ሙዚቃ በአለም ተደማጭና ተወዳጅ አድርጎታል የማሊ ሙዚቃ በአለም አቀፍ አድማጭ ዘንድ እንዲታወቅ ፈር ቀዳጅ መሆኑ ይነገራል
በ1990 ወቹ ለአስራ አንድ ሳምንታት የቢልቦርድ የአለም የ ሙዚቃ ሰንጠረዥ ላይ አንደኛ ሆኖም ነበር
ካገኛቸው ሽልማቶች ውስጥ
በሮሊንግ ስቶን የምንጊዜውም 100 ምርጥ ጊታሪስቶች ስም ዝርዝር ውስጥ ነበር በስፔን መጋዚን የምንጊዜውም 100 ምርጥ ጊታሪስቶች ውስጥ ስሙ በጉልህ ተፅፎም ነበር
በ2006 ከአለም ምርጥ የአገረሰብ ሙዚቃ ዘርፍ አሸናፊም ሆኖም ነበር::
Africa Citizen

Grand pአነጋጋሪው በመድረክ ስሙ ግራንድ ፒ(ሙሳ ሳንዲያና )ፕሮጄሪያ ( progeria disease)በተባለ በሽታ ተጠቂ ነው ያልተለመደ የጄኔቲክ በሽታ ሲሆን ከተወለደ ጀምሮ እርጅናን ይጀ...
09/02/2022

Grand p
አነጋጋሪው በመድረክ ስሙ ግራንድ ፒ
(ሙሳ ሳንዲያና )ፕሮጄሪያ ( progeria disease)በተባለ በሽታ ተጠቂ ነው ያልተለመደ የጄኔቲክ በሽታ ሲሆን ከተወለደ ጀምሮ እርጅናን ይጀምራል የጤንነቱ ሁኔታ ቁመቱን ወደ 1.2 ሜትር ብቻ እንዲሆን አድርጎታል ግራንድ ፒ ታዋቂ የጊኒ ዘፋኝ፣ ተዋናይ፣ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂ እና ፖለቲከኛ ነው።
በጊኒ የመዝናኛ ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ ስም ካላቸው ታዋቂ ሰወች ውስጥ አንዱ ነው የጄኔቲክ ችግር ቢኖርበትም ዝናና ሀብት ለማፍራት
አልገደበውም የሙዚቃ አልበምና ነጠላ ዜማወች ሰርቷል
ከአይቮሪኮስታዊ ሞዴል Eudoxie Yao ጋር የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ነው ለገንዘቡ ነው ብትባልም እሷ ግን በተደጋጋሚ ስለምታፈቅረው መሆኑን ትናገራለች
ግራንፒ በማህበራዊ ሚዲያ ብዙ ተከታይ አፍርቷል በፌስ ቡክ ብቻ
ከ6.1 ሚሊየን በላይ ተከታይ አለው::
Africa Citizen

እጅግ በጣም የተከበሩ የአለም ሎሬት ሜተር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ በጥቅምት 1932 በሰሜን ሸዋ አንኮበር ከተማ ተወለዱ  በ1947 ዓ/ም ገና በአሥራ አምስት ዓመታቸው  ለከፍተኛ ትምህርት ...
09/02/2022

እጅግ በጣም የተከበሩ የአለም ሎሬት ሜተር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ በጥቅምት 1932 በሰሜን ሸዋ አንኮበር ከተማ ተወለዱ በ1947 ዓ/ም ገና በአሥራ አምስት ዓመታቸው ለከፍተኛ ትምህርት ተመርጠው የምሕንድስና ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደእንግሊዝ አገር ለመሄድ ሲሰናበቱ
ጃንሆይ የሰጧቸውን ምክር ሁሌም እንደሚያስታውሱት ይናገራሉ። “ንጉሠ ነገሥቱ ተግታችሁ አጥኑ፣ ተማሩ ብለው ከመከሩን በኋላ ጠንክራችሁ መሥራት እና ሀገራችሁ ኢትዮጵያን የምትገነቡበትን ዕውቀት ይዛችሁ ተመለሱ። ስትመለሱ አዕምሯችሁ ዝግጁ የሆነ እውቀታችሁም ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚችል ጥበብን ሸምቶ እንዲመለስ ነው እንጂ አውሮፓ ውስጥ እንዴት ያሉ ረዣዥም ፎቅ ቤቶች እንዳሉ ወይም መንገዶቻቸው የቱን ያህል ስፋት እንዳላቸው እንድትነግሩን አይደለም።” ነበር ያሏቸው።በተለይም በሒሣብ፣ በኬሚስትሪ እና በታሪክ ትምሕርቶች ጥሩ ውጤት በማምጣት ተማሩ። ነገር ግን አስተማሪዎቻቸው የተፈጥሮ ስጦታቸው ኪነ ጥበብ እንደሆነ ለመገንዘብ ብዙ ጊዜም አልወሰደባቸው በሎንዶን የኪነ ጥበብ ማእከላዊ ትምሕርት ቤት (Central school of Arts & Crafts) ተመዝግበው ገቡ:: እዚህ ትምህርት ቤት ትምሕርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለከፍተኛ ጥናት በስመ ጥሩው የሎንዶን ዩኒቨርሲቲ የስሌድ ኪነ ጥበብ ማዕከል (Faculty of Fie Arts at Slade) የመጀመሪያው አፍሪካዊ ተማሪ ነበሩ ከሳቸው ጋር የሱዳን ተወላጁ ኢብራሂም ኤል ሳላሂ ም ነበሩ።
በስዕል፣ ቅርጻቅርጽ ጥናቶች ላይ ተምረው ተመረቁ። አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው የስዐሎቻቸውን ለዕይታ አቅርበው በሀገር ውስጥም በውጭ አለም ጭምር ዝናቸው ከፍ በሎም ነበር
መጀመሪያ ላይ ምንም ሥዕሎችን መሸጥ አልቻሉም ነበር በመጨረሻ ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለት ሥዕሎችን ገዙ። የሚገርመው ንጉሠ ነገሥቱ የኅብረተሰቡ አባላት አርቲስቱን እንዲደግፉና ሥዕሎችን እንዲገዙ አሳስበዋል ። በመቀጠልም ሰባት ተጨማሪ ሥዕሎች በተለያዩ ግለሰቦች ተወስደዋል፣ነገር ግን ምንም ክፍያ አልፈጸሙም ነበር። በስተመጨረሻ ንጉሠ ነገሥቱ ትኩረት ሰተውና ወይ ክፍያ እንዲፈጸም ወይም ሥዕሎቹ እንዲመለሱ ጠየቁ። ሰባቱም ሥዕሎች ለአርቲስቱ ተመለሱ።
ያ በአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው ኤግዚቢሽን በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላው አለም የአርቲስቱ አነጋጋሪና አሰደናቂ መሆኑ ተዘግቦ ነበር።
አፈወርቅ ተክሌ ስራዎች ኤርትራን ጨምሮ በመላው ኢትዮጵያ እና በናይጄሪያ፣ ግብፅ፣ ኮንጎ (ዛየር) ኬኒያ፣ ጋና፣ ሴኔጋል እና አልጄሪያ በእንግሊዝ ፣አየርላንድ ፣ጣሊያን ፣ ፈረንሳይስ ፣ፔን ፣ሩሲያ ፣ጀርመን ፣ ቼኮዝሎቫኪያ ፣ቡልጋሪያ ፣ግሪክ ፣ ዩጎዝላቪያ ፣ካናዳ ፣ አሜሪካ ፣ ሜክሲኮ ፣ ብራዚል ፣ አርጀንቲና ፣ ህንድ እና ጃፓን ። ስራዎቻቸው በአውስትራሊያ፣ ቬንዙዌላ እና ሱዳንን ጨምሮ በእነዚህ ሁሉ አገሮች እና በሌሎችም ይገኛሉ።
ከ 82 በላይ ሽልማቶች እንዳገኙ ይነገራል
ከንግሥት ኤልዛቤት II እና ልዑል ፊሊፕ፣ የስፔን ንጉስ እና ንግስት፣ የቤልጂየም ንግሥት፣ ፕሬዚዳንት ክዋሜ ንክሩማህ፣ ፕሬዚዳንት ጆሞ ኬንያታ፣ ፕሬዚዳንት ኬኔት ካውንዳ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢንድራ ጋንዲ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ፣ ወዘተ... ይህን ያህል እውቅና ያገኘ ሌላ ኢትዮጵያዊ አርቲስት የለም፣ በዓለም አቀፍ ደረጃም ብዙ አርቲስቶች መኖራቸውን እጠራጠራለሁ ብለው
ፕ/ር ሪቻርድ ፖንክረስ እንደተናገሩ ይነገራል
ሚያዚያ 2 ቀን 2004 ዓ/ም አርፈዋል
ምንጭ የተለያዩ ድህረ ገፆችና መፅሄት ቶች
Africa Citizen

አቅምና ሀብት በአፍሪካአፍሪካ በእርሻ መሬት፣ በውሃ፣ በዘይት፣ በተፈጥሮ ጋዝ፣ በማዕድን፣ በደን እና በዱር አራዊት በሚገኙ የተፈጥሮ ሃብቶች የበለፀገች ነች።  አፍሪካ -30 በመቶውየዓለምየማ...
09/02/2022

አቅምና ሀብት በአፍሪካ
አፍሪካ በእርሻ መሬት፣ በውሃ፣ በዘይት፣ በተፈጥሮ ጋዝ፣ በማዕድን፣ በደን እና በዱር አራዊት በሚገኙ የተፈጥሮ ሃብቶች የበለፀገች ነች።
አፍሪካ
-30 በመቶውየዓለምየማዕድንክምችት፣
-8 በመቶው የዓለም የተፈጥሮ ጋዝ እና -12 በመቶው የዓለም የነዳጅ ክምችት ባለቤት ናት
አህጉሪቱ
- 40 በመቶው የአለም ወርቅ እና እስከ -90 በመቶው ክሮሚየም እና ፕላቲነም አላት በዓለም ላይ ትልቁ የኮባልት፣ የአልማዝ፣ የፕላቲኒየም እና የዩራኒየም ክምችት የሚገኘው በአፍሪካ ነው።
በአለም ላይ 65 ከመቶ ሊታረስ የሚችል መሬት እና ብዙ በውሀ የተሸፈነ መልከአምድር የታደለች ነት:::
Africa Citizen

Address

A. A
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Africa Citizen posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to Africa Citizen:

Share