Hamak attention

Hamak attention ከመፅሀፍ አለም እየገባን ድንቅ ሀሳቦችን እንካፈል

https://youtu.be/NO7nQVRnyCU
24/06/2022

https://youtu.be/NO7nQVRnyCU

ኧረ አምሳለby Hamakኧረ አምሳለ እቴ እንዴት ነሽአለች በመከራ እንባዋን ስትዘራእኔን እኔን ይክፋኝበሞላ ማድጋ ባልጎደለ መሶብ ጦም ማደርሽ ከፋኝ

22/03/2022

በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ ፣ ሰዎች ላይቀበሉህ
ይችላሉ ፣ ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ ፣ ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ ፣ በእጅህ ላይ
ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ ፣ ሰዎች ሊጠሉህ ፣
ሊያሙህ ፣ ወይ ስም ሊያወጡልህ ፣ አሊያም ሊስቁብህ ፣ ይችላሉ።
:
" በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት
መሞከር ነው። መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል። አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች
ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል። ብርሃናዊ ራዕይ
ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል። ነፃ
አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል።
:
ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም።
ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር! ከምንም በላይ
በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!"
አንድ ነገር ልንገራችሁ!
:
በህይወታችሁ ማንንም አትውቀሱ
ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጡዃችሀል
መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኑዃችሀል
ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆኑዃችሀል
ምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኑዃችሀል

‹‹….የሀገሬ ሰው ከአሁን ቀደም የበደልኩህ አይመስለኝም፤ አንተምአላስቀየምኝም፡፡ ጉልበት ያለህ በጉልበትህ ዕርዳኝ፤ ጉልበት የሌለህ ለልጅህለሚስትህ ለሃይማኖትህ ስትል በሐዘን ዕርዳኝ፡፡ ወስ...
27/02/2022

‹‹….የሀገሬ ሰው ከአሁን ቀደም የበደልኩህ አይመስለኝም፤ አንተም
አላስቀየምኝም፡፡ ጉልበት ያለህ በጉልበትህ ዕርዳኝ፤ ጉልበት የሌለህ ለልጅህ
ለሚስትህ ለሃይማኖትህ ስትል በሐዘን ዕርዳኝ፡፡ ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ
ትጣላኛለህ፤ አልተውህም፡፡ ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም..ዘመቻዬ
በጥቅምት ነው እና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ድረስ ወረይሉ ከተህ
ላግኝህ፡፡››

Amaizing story - ሀይማኖት እንጂ እምነት የላችሁም !! - እመጓ - New Ethiopian
24/09/2021

Amaizing story - ሀይማኖት እንጂ እምነት የላችሁም !! - እመጓ - New Ethiopian

እመጓ ( Emegua )ደራሲ - አለማየሁ ዋሴ ( Alemayehu wase )ትረካ - Hamak

16/09/2021

#የሚያሳስበን ችግሩ ሳይሆን ችግሩን የምናይበት መንገድ ቢሆንስ? #

⚜ምንም እንኳን ስለመልካም አስተሳሰብ እና ስለ ቀና ኑሮ ደጋግመን ብንደሰኩርም አንድ መዋጥ ያለብን እውነት ግን አለ። ይህም ህይወት ነጭ እና ጥቁር አይደለችም። የጠበቅናቸው የማይከሰቱባት ያልጠበቅናቸው የሚከሰቱባት የማትተነበይ እንጂ። ችግር የማይደርስበት ኑሮ፤ ከመከራ ከሃዘን የራቀ ህይወት ለማንም አልተሰጠም። ማንም ሰው ሁሉ ተሳክቶለት እና ሞልቶለት የሚኖር አይኖርም (ምንም እንኳን ከላይ በምናያቸው ነገሮች ሁሉ ነገር የተሳካላቸው ሰዎች ያሉ ቢመስሉንም)። አነሰም በዛ እያንዳችን የምናምርርባቸው ነገሮች በህይወታችን ውስጥ አሉ።

መማረር ማለት ያለውን እውነታ መቀበል አለመቻል ነው ይላል። የምናማርረው ኑሮዋችን እኛ በፈለግነው መንገድ ስላልሄደ አልያም እንዲከሰቱ የማንፈልጋቸው ነገሮች ስለተከሰቱ ነው። እንዲህ አይነት ችግሮች ሲፈጠሩ እራሳችንን የምናወጣባቸው መፍትሄዎች አሉ። ለዚህች አጭር ጽሁፍ “The power of Now” ከተሰኘው መጻህፉ ላይ ያገኘኋቸውን ሶስት ነጥቦች ሰፋ አድርጌ ላካፍላችሁ ወደድኩኝ።

1⃣ Remove yourself from the situation–
አንዳንዴ ችግር ብለን የምንወስዳቸው ወይም የምጨነቅባቸው ነገሮች ከኛ ውጪ በሆኑ ነገሮች የሚከሰቱ ናቸው ። የሰው ልጅ ደግሞ እራሱን ከመለውጥ ባለፈ የሌላውን ሰው አስተሳሰብ እና ማንነት ለመለወጥ አይቻለውም። ስለዚህ የምንማረርባቸው ነገሮች ከኛ የመነጩ ካልሆኑ ፤ከሁኔታው አልያም ከአካባቢው እራሳችንን በማራቅ ሰላማችንን ማግኘት እንችላለን። በዙሪያችን ያሉ ነገሮች የሚያደርሱብንን ተጽዕኖ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ባንችልም፤ ሁኔታዎቹ ግን ሰላም እና ደስታችንን እንዳያናውጡ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን።

2⃣ Change it– የማንፈልገውን ነገር ለመለወጥ መጣር- ብዙዎቻችን ስለችግሮቻችን ቀን እና ማታ እናወርለን ነገ ግን ለምፍትሄ የሚሆን ጊዜ የለንም። ለምሳሌ ስራ በማጣቱ የሚማረር ወጣት ቀን እና ማታ ስለስራ አጥነት ቢይወራ ምንም መፍትሄ የለውም። ከሱ የሚጠበቀው ሳይታክት ማመልከቻዎቹን ማሰራጨት ፤ ክህሎቶቹን ማዳበር እና ስራ ሊያገኝባቸው የሚችልባቸውን መንገዶች ማጤን ነው። ስለኑሮዋችን ብናማርር፤ ሌሎችን ብንወቅስ፤ እንዲህ ቢሆን ኖር እያልን በሃዘን ብንብሰከሰክ፤ ሁኔታውን ለመለወጥ ሙከራ እስካላደርግን ድረስ ምንም ጠብ የሚል ነገር የለም።

3⃣ Accept it totally– በልጅነቴ የሰማሁት ጸሎት እስካሁን ድረስም አብሮኝ አለ። ለኔ ትልቅ ትርጉም ስላለው ችግሮች ሲገጥሙኝ ሁሌም አስታውሰዋለው። ጸሎቱ እንዲህ የሚል ነው “በህይወቴ ልለውጣቸው የምችላቸውን ነገሮች እንድለውጥ ብርታቱን ስጠኝ፤ ልለውጣቸው የማልችላቸውን ነገሮች እንድቀበል ጽናቱን ስጠኝ፤ እናም በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት እንዳስተውል ጠቢብነቱን አድለኝ” ይላል። አዎ ልንለውጣቸው የምንችላቸው ነገሮች ላይ ጉልበት እና ጊዜያችንን በጭንቀት ከማሳለፍ ይልቅ መፍትሄው ላይ ማተኮር ይኖርብናል። በሌላ በኩል ከኛ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ነገሮችን መለወጥ ካልቻልን ተቀብለናቸው መኖርን መልመድ አለብን።

🔑ከላይ የሰፈሩት መፍትሄዎች እንዳሉ ሆነው ችግሮቻችንን ይበልጥ ግልጽ በሆነ እና ቀለል ባለ መልኩ እንድናይ የሚረዳንን አንድ ትልቅ ነጥብ ላክል እሻለው። ይኸውም ችግሮችን የምናይበትን መንገድ በተመለከተ ነው።በብዛት የሚያሳስበን ችግሩ ሳይሆን ችግሩን የምናይበት መንገድ ነው። አይምሮዋችን እንደ እሳት ነው ለበጎ ነገር ከተጠቀምንበት ህልውናችን ፤ለመጥፎ ነገር ከተጠቀምንበት ደግሞ መጥፊ

14/09/2021

ሰላም እና የሚያምርብን ፍቅራችንን ይመልስልን

ነብስ ይማር.....ስለ አለማየሁ እሸቴ በጥቂቱ (ethiopian musician Alemayehu eshete )
14/09/2021

ነብስ ይማር.....ስለ አለማየሁ እሸቴ በጥቂቱ (ethiopian musician Alemayehu eshete )

አለማየሁ እሸቴ ወደሙዚቃው እንዴት ገባ ህይወቱስ ምን ይመስል ነበር

አዲስ አማሪኛ የፍቅር ግጥም ''መለያየት ሞት ነው" (new amharic romantic poem-meleyayet mot new)
14/09/2021

አዲስ አማሪኛ የፍቅር ግጥም ''መለያየት ሞት ነው" (new amharic romantic poem-meleyayet mot new)

እንኳን ወደ ፟ሐ-mak attention በሰላም መጣቹ በዚ ቻናል -ታላላከቅ የሙዙክቃ ባለሞያዎች ኢንተርቪዩ (ጥበብን እንወቃት) ...

New ግጥም "ትዝታ" (Tizta amharic romantic poim with lyrics)
14/09/2021

New ግጥም "ትዝታ" (Tizta amharic romantic poim with lyrics)

New ethiopian poim "ቀይ አደይ አበባ" Ethiopian new year
14/09/2021

New ethiopian poim "ቀይ አደይ አበባ" Ethiopian new year

አንቺ የመስቀል ወፍ በሀገሬ ሰማይ ላይ ደምቀሽ ምትበሪምድሯን ከፋው ብለሽ አንቺም በተስፋ አደራ እንዳትቀሪ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hamak attention posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to Hamak attention:

Share