Hqeslhwega238454

Hqeslhwega238454 I am Endale Hailu self employed

02/05/2024
05/10/2022

/ የፅጌ ፆም

የእመቤታችን ስደት በጾም የድንግል ማርያም የቃልኪዳን ልጆች ከወዲሁ እንኳን አደረሳችሁ

ለጽጌ ጾም ካላቸው ፍቅር የተነሳ አንዳንድ ምዕመናን ጽጌ ጾም መቼ ነው የሚገባው እያሉ የሚጠይቁ ስላሉ ከወዲሁ ለማስታወስ ጾመ ጽጌ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ያለው አንድ ወር ከዐሥር ቀን ወይም 40 ቀን ወርኃ ጽጌ፣ ዘመነ ጸጌ፣ ተብሎ ይጠራል፡፡

በነዚህም ቀናት በየቤተክርስቲያኑ የሚነበቡ ምንባቦች፣ የሚዘመሩት መዝሙሮች፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚቆመው ማኅሌት በጠቅላላው የሚነገረው ስብሐት እግዚአብሔር ሁሉ ሰማይ በከዋክብት ምድር በጽጌያት አሸብርቀው የሚታዩ መሆናቸውን የሚገልጽ ነው፡፡

ወርኃ ጽጌ ለሚከናወነው መንፈሰዊ አገልግሎት መነሻው "መልአኩ ሕፃኑንና እናቱን ወደ ግብፅ ይዘሃቸው ሽሽ፣ የሕፃኑን ነፍስ ሊገድሉት ይፈልጋሉና" ሲል ለዮሴፍ በሕልሙ በነገረው መሠረተ ዮሴፍም ሕፃኑንና እናቱን ድንግል ማርያምን ይዞ ወደ ግብፅ መሰደዱና እመቤታችንና ሕፃኑ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ከኖሩ በኋላ /ራእይ.12፣6/ ወደ አገራቸው ወደ ናዝሬት የመመለሳቸው መታሰቢያ ነው፡፡ /ማቴ 2፣13-23፣ ት.ኢሳ.19፣1፣ እንባቆም 3፣6-7፣ መዝ.83፣3/፡፡

ይህንንም በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሡ አባ ጽጌ ብርሃን ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኝ ሁሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን በአበባና በፍሬ እየመለሰ በሚያስረዳው ድርሰታቸው እንዲህ በማለት ገልጸውለታል፡፡ "አፈወ ሮማን ማርያም ጽጌ ቀናንሞ ወአበሜ፣ እስከ ተጸምሐየየ በጾም ዘመልክዕኪ ጊዜ ድክታሜ፣ እምተመነይኩ ተሳትፎ ከመ አኅትኪ ሰሎሜ፣ ወፍሥሓኪ ዘአልቦ ፍጻሜ"፡፡

ሲተረጎምም የሮማን ሽቱ የቀናንሞ አበባ የምትሆኚ ማርያም ሆይ፣ በርሃብ በጾም አበባ የመሰለ የመልክሽ ደም ግባት እስኪጠወልግ ድረስ በስደትና በልቅሶ የደረሰብሽን ችግርና ድካም መከራሽንም ሁሉ እንደ እኅትሽ እንደ ሰሎሜ አብሬሽ ብቀበል ምኞቴ ነበር፤ በዚህ ፍጻሜ የሌለውን ደስታሽን እሳተፍ ነበር፡፡

እንዲሁም አባ አርክ ሥሉስ በስደቷ የደረሰባትን ኀዘን ፣ ልቅሶና ሰቆቃ አስመልክተው በደረሱት "ሰቆቃወ ድንግል" በሚለው ድርሰታቸው እንዲህ አሉ፣ ፀሐይን የምትለብሽ የብርሃን ልጅ ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ከሄሮድስ ዘንድ ልጅሽን ባሸሸሽ ጊዜ የደረሰብሽን ችግሮች ጨረቃን የሚጫሙ እግሮችሽ በመንገድ ብዛትና በአሸዋ ግለት እንደ ጎበጎቡ ሲሰማ ሰው ይቅርና ድንጋዩም ባለቀሰ ነበር”
የእመቤታችን የስደቷ መታሰቢያ ወር በቤተ ክርስቲያናችን የሚከበረው በማኅሌት፣ በቅዳሴና በዝክር ነው፡፡

በወርኃ ጽጌ ባሉት ሳምንታት ከቅዳሜ ማታ እስከ እሑድ ጠዋት አበው ካህናት የሚያቀርቡት ዝማሬ ከቅዱስ ያሬድ ድጓ፣ ከማኅሌት ጽጌና ከሰቆቃው ድንግል የተውጣጣና ሦስት ወገን ያለው ነው፡፡

ዝክሩም፣ በአሁኑ ወቅት በከተሞች አካባቢ እየተረሳ ቢመጣም፣ ዘወትር እሑድ የአንድ አካባቢ ሰዎች ማዕከላዊ በሆነ ቦታ ተሰባስበው በእመቤታችን ስም የሚዘክሩት ነው፡፡

ዐቅመ ደካሞች፣ ድሆችና መንገደኞች ተጠርተው በእመቤታችን ስም እንዲበሉና እንዲጠጡ ይደረጋል፡፡

ይህም ትውፊት እመቤታችን ወደ ኢትዮጵያ በመጣች ጊዜ ኢትዮጵያውያን አባቶችና እናቶች ያደረጉላትን መስተንግዶ ለማሰብ ነው፡፡
ከእመቤታችን በረከት ያሳትፈን አሜን!!!

04/10/2022

⛪️" የጻድቃን መንገድ ቅን ናት፤ አንተ ቅን የሆንህ የጻድቃንን መንገድ ታቃናለህ።" ት.ኢሳ ፳፮፥፯

➱" ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።" ማቴ ፲፥፵፩

✝️ገድሉ ተአምራት ✝️
ገድሉ ተአምራቱ እጅግ ብዙ ነው
ጣኦትን አዋርዶ የተሸለመው
የተዋሕዶ ኮከብ ተክለሐዋርያ
አባ ተክለ ሃይማኖት ዘኢትዮጵያ
🙏🙏🙏
ዳግማዊ ዮሐንስ ጠፈር የታጠቀ
ንጹሕ ባህታዊ ጠላት ያስጨነቀ
የጸጋ ዘአብ ፍሬ ዛፍ ሆኖ በቀለ
በደብረ ሊባኖስ መናኝ አስከተለ
🙏🙏🙏
ደካማ መስሏቸው በአንድ እግሩ ቢያዩት
ባላስድስት ክንፉ ጻድቁ የእኔ አባት
እርሱስ አንበሳ ነው ትናገር ደብረ አስቦ
ሌጌዎን ሲዋረድ እፍረት ተከናንቦ
🙏🙏🙏
ከካህናት መካከል ኅሩይ ነው አቡዬ
መጣው ከገዳምህ ልሳለለምህ ብዬ
ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አባ ተክለሃይማኖት
ወልድ ዋሕድ ብለህ ምድሪቱን ቀደስካት
🙏🙏🙏
የባረከው ውኃ የረገጥከው መሬት
ጥላህ ያረፈበት ሆንዋል ጸበል እምነት
ኑና ተመልከቱ ድውያን ሲፈቱ
ይሰብካል ተክለአብ ዛሬም እንደጥንቱ

✍️" የጌታ ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና፥ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል፥ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው።" ፩ኛ ጴጥ ፫፥፲፪

✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥
ለበለጠ መረጃ "ዲያቆን ሙሉቀን ግርማ" ፔጁን ላይክ በማድረግ እለት እለት የቅዱሳኑን፣የጻድቃን፣የሰማዕታትን፣የነብያትን፣የሐዋርያትን ገድል ተአምራት ይከታተላሉ እንዲሁም ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳዮች ላይ እንወያይ መልዕክት ይላኩ......ስለጎበኙን እግዚአብሔር አምላክ በረድኤት ይጎብኝልን፤ የእመቤታችን የድንግል ማርያም አማላጅነት፤የጻድቃን የሰማዕታት ተራዳኝነት አይለየን አሜን።✟

03/10/2022

እንኳን ለሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ መታሰቢያ ክበረ በዓል በሰላም አደረሰን።

ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በጥር 20 ቀን በ277 ዓ.ም ተወለደ።

ሐገሩ ፍልስጤም አሁን (እስራኤል )ሲሆን ልዩ ስሟ ልዳ አሁን (ሉድ) ይባላል።

ጊዮርጊስ ማለት «ኮከብ፣ ብሩህ፣ ሐረገወይን፣ ፀሐይ» ማለት ነው።

ሊቀ ሰማእት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰባ ነገሥታትን ያስጨነቀ፣ ቤሩታዊቷን ከዘንዶ አፍ ያዳነ፣ የመበለቷን ቤት ምሰሶ ያለመለመ፣ ሰባት ዓመት በፅኑ ተጋድሎ የተጋደለ በኋላ በ27 ዓመቱ በ304 ዓ/ም ሚያዚያ 23 ቀን ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት ሲሆን ነፍሱን የሰጠ ፅኑ ሰማእት ነው።

የቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ቅዱስ ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን አሜን። ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይሰውረን አሜን።

ፎቶ (አራዳ)ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የተዋህዶ ቤተሰብዎች ሊንኩን በመጫን
Subscribe በማድረግ አዲሱ የ አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ you tube ቻናል ቤተሰብ ይሁኑ እናመሰግናለን::👇
https://youtube.com/playlist?list=PLZWWfiI3viLHWDNmXaYmM3DuAywdkU2fo

27/09/2022
26/09/2022

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ!

መልካም ልደት እማቹ
26/09/2022

መልካም ልደት እማቹ

24/09/2022

እንኳን ለቅዱስ አቡነ አረጋዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።

ስነ ስዕሉ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ደብረ ገነት ኪዳነ ምህረት ገዳም ውስጥ የሚገኝ ጥንታዊ ስነ ስዕል ነው

አቡነ አረጋዊ አባታቸው ይስሐቅ የሮም ንጉስ ነበሩ፡፡ እናታቸው ንግስት እድና ትባላለች፡፡
አቡነ አረጋዊ የመጀመሪያ ስማቸው «ዘሚካኤል»ነው፡፡ ጥበብ እና መንፈሳዊ ትምህርት ሲማሩ አድገው ወደ እስክንድሪያ ገዳም ኮብልለው ገቡ፡፡

ቅዱስ አቡነ አረጋዊ በ480 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያ እናታቸው ቅድስት እድናን ደቀመዝሙራቸውን ማትያስን ጨምሮ ዘጠኝ ሁነው ገቡ። እግረመንገዳቸውን እያስተማሩና ድውያንን እየፈወሱ ደብረ ዳሞ ደረሱ፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈቀ ሌሊት ተገልጾ ከድካም ወደ እረፍት ከኃዘን ደስታ ወዳለበት ከአሣር ወደ ክብር ቦታ በታላቅ ደስታ እወስድህ ዘንድ ወደ አንተ መጣሁ፡፡

መታሰቢያህን ያደረገ በፀሎትህም የተማመነውን ሁሉ እኔ በመላአክት ፊት ሞገስን ባለሟልነትን እሰጠዋለሁ፣ በስምህ በተሰራው ቤተ መቅደስህ ውስጥ የፀለየ የለመነ ፈጥኜ ፀሎቱን እሰማዋለሁ፡፡

ቤተ ክርስቲያንህን ለሰራ አስራ ሁለት የብርሃን አዳራሽ አዘጋጅለታለሁ፣ የገድልህን መጽሐፍ በመታመን በንጽህና አድርጎ በቤቱ ያስቀመጠ የወረርሽኝ በሽታ ወይም ቸነፈር በቤቱ አይገባም፡፡

ድንገተኛም የሰውና የእንስሳ ሞት አይደርስበትም የእህል ችግርም አይኖርበትም፣ ከሁሉም ይልቅ የሞት ጥላ አያርፍብህም መልአከ ሞትም ሊያስደነግጥህ አይችልም እንደ ነቢያቶቼ ኤልያስና ሄኖክ ትሰወራለህ ብሎ ብዙ ቃል ኪዳኖች ገባለት፡፡

አባታችንም ጌታ ሆይ መታሰቢያዬን ያደረገ የገድሌን መጽሐፍ የፃፈ በፀሎቴ የተማመነ እስከ ስንት ትውልድ ትምርልኛለህ አለው ጌታም እስከ አስራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ገባለት፡፡

ይህን ቃልኪዳን ከሰጣቸው በኃላ በክብር አረገ።

አባታችን ቅዱስ አቡነ አረጋዊ ደብረ ዳሞ ላይ በፍጹም ተጋድሎ ኖረው ለኢትዮጵያ ብርሃን ሆነው በ 99 ዓመት ከሦስት ቀናቸውጥቅምት 14 ቀን ተሰወሩ።

የአቡነ አረጋዊ እናት ንግስት እድና ንግስናዋን ትታ ልጇን ተከትላ መጥታ ደብረ ዳሞ ተራራው ስር በ89 ዓመቷ አርፋለች።
የአባታችን ረድኤት፣ በረከትና ምልጃቸው አይለየን አሜን።
https://youtu.be/kIfnGPZ51fk

23/09/2022

እንኳን አደረሳችሁ
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሩፋኤል በተራዳኢነቱ ይቁምልን በአማላጅነቱ አይለየን አሜን።
https://youtu.be/kIfnGPZ51fk

Address

Abiy Adi

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hqeslhwega238454 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share