ከመጻሕፍት ዓለም

ከመጻሕፍት ዓለም ከመጻሕፍት የተጣሩ ድንቅ ድንቅ መረጃዎችን እናደርሳለን።

ደራሲ በዓሉ ግርማ በኢሊባቡር ክፍለ ሀገር ሱጴ በምትባል ሥፍራ በ1928 ዓ.ም. ተወለዱ። ዕድሜያቸው ለትምሕርት ሲደርስ የአንደኛ ደረጃ ትምሕርታቸውን በልዕልት ዘነበወርቅ ትምሕርት ቤት ፤ ሁ...
08/10/2025

ደራሲ በዓሉ ግርማ በኢሊባቡር ክፍለ ሀገር ሱጴ በምትባል ሥፍራ በ1928 ዓ.ም. ተወለዱ። ዕድሜያቸው ለትምሕርት ሲደርስ የአንደኛ ደረጃ ትምሕርታቸውን በልዕልት ዘነበወርቅ ትምሕርት ቤት ፤ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርታቸውን ደግሞ በጄኔራል ዊንጌት ትምሕርት ቤት አጠናቀዋል። ከዚያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖሊቲካል ሳይንስ እና ኢንተርናሽናል ሪሌሽንስ የ ቢ.ኤ. ዲግሪ ያገኙ ሲሆን፤ በዚሁ ተመሳሳይ መስክ ከአውሮፓ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።
ደራሲ በዓሉ ግርማ በተለይ በልብ ወለድ እና በፈጠራ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ከታወቁት የኢትዮጵያ የዘመኑ ደራሲዎች መካከል ተወዳጅነትና ዝናን ያተረፉ ዕውቅ ደራሲ ነበሩ። ከጻፏቸው በርካታ ድርሰቶቻቸው ውስጥ «ከአድማስ ባሻገር» የተሰኘው መጽሐፋቸው በሩስኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በቀድሞዋ የሶቪየት ሶሽያሊስት ሕብረት ሪፑብሊክ ቀርቧል። በተጨማሪም በጋዜጠኝነት ሙያም ስማቸውን ያስጠሩ፤ ሙያቸውንም ያስከበሩ ደራሲ ነበሩ። «የዛሬይቱ ኢትዮጵያ» ጋዜጣ፤ የመነን መጽሔት፤ የአዲስ ሪፖርተር መጽሔት፤ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በመሆን ከመሥራታቸውም ባሻገር፤ ብዙ ወጣት ጋዜጠኞችን ለማፍራት ጥረት አድርገዋል። አዲስ ሪፖርተር የተባለውን መጽሔትም ደረጃው ከፍ እንዲልና በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲገመገም አድርገዋል። በጋዜጠኝነት ሙያቸው በኢትዮጵያ ራዲዮ ሠርተዋል።
ደራሲ በዓሉ ግርማ ለኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱና ብዙ ሥራዎችን ያቀረቡ ሲሆን፤ የመጨረሻው መጽሐፋቸው «ኦሮማይ» በመባል ይታወቃል። ይኼውም መጽሐፍ በወቅቱ በነበረው የደርግ መንግሥት ሊደገፍ ባለመቻሉ በ1976 ዓ.ም. ለደራሲው ሕይወት መጥፋት መንስኤ ሊሆን በቅቷል።

ሞባይል ስልክ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ አገልግሎቱን ለማግኘት ያስፈልጉ የነበሩት አስገራሚ መስፈርቶች (wassihun Tesfaye...............ግንቦት 9 \ 1991 ዓ.ም ፡   ቴሌ.  ...
07/04/2025

ሞባይል ስልክ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ አገልግሎቱን ለማግኘት ያስፈልጉ የነበሩት አስገራሚ መስፈርቶች (wassihun Tesfaye...............
ግንቦት 9 \ 1991 ዓ.ም ፡ ቴሌ. ለወራት ሲያስተዋውቅ የከረመውን የሞባይል ስልክ አገልግሎት መስጠት የሚጀምርበት ቀን ነበር ...........
እና በዚያን እለት ግንዛቤው የነበራቸው ባለሃብቶች ለ ኢትዮጵያ አዲስ የሆነውን ሞባይል ስልክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን ወደ ቴሌ ቢሮዎች በጠዋት መምጣት ጀምረዋል ።........
በቢሮው መግቢያ ላይ አንድ ማስታወቂያ ተለጥፎአል .. .. ሲም ካርድ ለመውሰድ ሲመጡ ኦሪጅናል እና ኮፒ የመኖሪያ ቤት ካርታ .. ይዘው መምጣት እንዳለባቸውና የ አገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን የቤት ካርታቸውን ማስያዝ እንዳለባቸው የሚገልጽ ማስታወቂያ ።

በነገሩ የተስማሙና ቀድመው መረጃውን ያገኙ ሰዎች ፡ የቤት ካርታቸውን እያስያዙ ለሲም ካርዱና ፡ ቴሌ በብቸኝነት ያስመጣው የነበረውን ይህን በፎቶው የሚታየውን ትልቅ የ ኢሪክሰን ቀፎ 5,000 ሺህ ብር አካባቢ እየከፈሉ መውሰድ ጀመሩ .. የዚያኑ እለትም የመጀመሪያዎቹ ባለሞባይሎች በአዲስ አበባ ከተማ ይታዩ ጀመር ።............
እነዚህ ጥቂት የከተማችን ባለሞባይሎች በሱሪያቸው ቀበቶ ላይ በታሰረ የቆዳ ቦርሳ ያንጠለጠሉትን ትልቅ ሞባይል እያየ ማን ያልተገረመ ነበር ... በነገራችን ላይ ከነዚህ ቴሌ ከሚያስመጣቸው ስልኮች ውጭ በሌላ ቀፎ መጠቀም ፈፅሞ የተከለከለ ሲሆን በኢትዮጵያ ብቸኛው የሞባይል ቀፎ ሻጭ ቴሌ ብቻ ነበር ። ...............
ቆየት ብሎ ታድያ የሞባይል ስልክ መጠቀም ፈልገው ነገር ግን የቤት ካርታ የሌላቸው ባለሃብቶች ቅር መሰኘታቸውን የተረዳው ቴሌ ፡ የቤት ካርታ ላላቸው የተመዘገቡ ባለሃብቶች ስልክ ሰጥቶ እንደጨረሰ ፡ ካርታ ለሌላቸው መስመር ፈላጊዎች 50 ሺህ ብር በማስያዝ ሲም ካርድ መውሰድ እንደሚችሉ አስታወቀ ።.............
በጥቂት ወራት እድሚው የሞባይል ስልክን አስፈላጊነቱን የተረዱ ሰዎች በርከት በማለታቸው 50 ሺ ብር አስይዞ ሞባይል የሚወስደው የ አዲስ አበባ ባለሃብት ተበራከተ ። ....
በዚያን ጊዜ የሞባይል አገልግሎት የሚሰራው በ 100 ኪሚ ራዲየስ ብቻ ነበረና የሞባይል ስልክ ብቸኛ መናሃሪያ አዲስ አበባ ከተማ ብቻ ነበረች ። ( ከአዲስ አበባ ከመቶ ኪሎ ሜትር በላይ ከራቀ ሞባይሉ አይሰራም ) 🤔..........
ከዚህ በሁዋላ ቴሌ ለብዙ ወራት ሲም ካርድ መሸጥ አቁሞ ላሉት ጥቂት ባለሞባይሎች አገልገሎቱን ለማዳረስ ኔት ወርክ በማስፋፋት ሰራ ላይ ተጠምዶ ከቆየ በሁዋላ ከአዲስ ማስታወቂያ ጋር ብቅ አለ ።....... ቴሌ በአዲሱ ማስታወቂያው ብዛት ያላቸውን ሲም ካርዶች ያለምንም ማስያዣ በቀበሌ መታወቂያ ብቻ መስጠት ሊጀምር እንደሆነና በተጨማሪም ፡ የሞባይል ተጠቃሚው ቴሌ በብቸኝነት ከሚሸጠው ኤሪክሰን ስልክ ውጭ በፈለገው ስልክ መጠቀም እንደሚችል ገልጾ ምዝገባ ጀመረ ። በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች አገልግሎቱን ለማገኘት በመመዝገባቸውም ሲም ካርድ ለማገኘት ከ 6 ወር እስከ አንድ አመት መጠበቅ ግድ ነበር ። ...
በዚህ ወቅት የሲምካርድ ዋጋ ከአምስት ሺህ ብር ወርዶ 550 ብር ፡ ከዚያም 440 ብር 365 ብር ፡ 169 ብር ይሸጥ ነበር ። ይህን ተከትሎም የሞባይል ቀፎዎች በግለሰብ ሱቆች ውስጥ መሸጥ ጀመሩ ። .....

ዛሬ ላይ ሁሉ ነገር ቀላል ሆኖ. . ከየትኛውም ሱቅ ልንገዛው የምንችል እቃ ከመሆኑ በፊት .. ... ሲም ካርድ ተመዝገበው ደርሷቸው የቀፎ መግዣ ካጡ ሰዎች ሲሙን በወር ከ 70 እስከ 100 ብር መከራየት ይቻልም ነበር ።................
እናንተስ መጀመሪያ የያዛችሁት ስልክ ምን አይነት ነበር ? ለመጀመሪያ ቀን ስልክ ስታወጡ የነበራችሁ ስሜት ?
በመጀመሪያ ቀን የት ደወላችሁ ? ከሞባይል ጋር በተያያዘ ያጋጠማችሁ ምን ነበር?

ምንጭ ፦Etio Times

💥💥"መቀየር በማትችለው ነገር ላይ ወደኋላ ተመልሶ መቆዘም ነገህን ያበላሻል። ነገ የተሻለ እንደሚሆን ማመን አለብህ። ነገ ይሻላል ብለህ ካመንህ ደግሞ ዛሬ ላይ መከራን መሸከም ትችላለህ። በሕ...
06/01/2025

💥💥"መቀየር በማትችለው ነገር ላይ ወደኋላ ተመልሶ መቆዘም ነገህን ያበላሻል። ነገ የተሻለ እንደሚሆን ማመን አለብህ። ነገ ይሻላል ብለህ ካመንህ ደግሞ ዛሬ ላይ መከራን መሸከም ትችላለህ። በሕይወትህ ውስጥ የሚመጡ መስናክሎችን እየሰባበርህ ወደፊት ለመጓዝ ሞክር እንጅ በእነሱ ተሰብረህ አንድ ቦታ ላይ ሽባ ሆነህ አትቁም። ብዙ ጊዜ የሕይወት ታላላቅ ትምህርቶችን የምንማረው በከባድና በመጥፎ ጊዜያቶች ውስጥ በፅናት ጎዳና ላይ ተራምደን ስናልፍ ነው። በሕይወታችን ውስጥ የፅናትን ያህል ጉልህ ድርሻ የሚወስድ ምንም ነገር የለም። ህልማችን እውን ለማድረግ ሕይወት የምትሰነዝርብንን ፈተና ሁሉ በፅናት መቋቋም ግድ ይለናል።".......
#ስሙር
በረደድ ከፃፈው የተወሰደ

28/08/2024

!

ውሎህ ይህን ከመሰለ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ነህና ንቃ!

- ትነሳለህ
- ቡና ትጠጣለህ
- ስራ ትጀምራለህ
- ምሳ ትበላለህ
- ከስራ ትወጣለህ
- ስለስራህ ታማርራለህ
- ሶሻል ሚዳያ ላይ ትጣዳለህ
- በሌሎች ሰዎች ትቀናለህ
- እያለቃቀስክ ትተኛለህ

ነገም ይሄ ይቀጥላል!!

ንቃ ወንድሜ ንቃ! ሕይወት ለአልቃሾች ቦታ የላትም!!

መጽሐፍ

💥ቢዝነስ ጥበብ ይፈልጋል፤ መጽሐፍ ደግሞ የሚያስፈልገውን ጥበብ ሁሉ ይለግስሀል።

👉ይህንን መጽሐፍ በማንበብ የምታገኙትን እውቀት ከእውነተኛው ዓለም ልምድ ጋር በማቆራኘት ከተጠቀማችሁበት ውጤቱን በቀሪ ዘመናችሁ ሁሉ ታገኙታላችሁ።

መጽሐፍ
(በእንግሊዝኛ)
2ተኛ ዕትም

ሶስቱም መጽሐፍት ጥራታቸውን ጠብቀው፣ በታጣፊ ከቨር ጭምር በውጭ ስታንዳርድ ታትመው በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛሉ።

📖ሌሎች ምርጥ ከቢዝነስና ሀብት ከማፍራት ጋር የተያያዙ መጻሕፍት፦
👌👌👌

መጽሐፍ 2ተኛ ዕትም
2ተኛ ዕትም
መጽሐፍ 12ተኛ ዕትም
መጽሐፍ 8ተኛ ዕትም
መጽሐፍ 2ተኛ ዕትም
መጽሐፍ

ሁሉም በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛሉ።

📕📕📕
(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)

ቴሌግራም👉 https://t.me/teklu_tilahun
ፌስቡክ ገጽ👉 https://bit.ly/3sNq5Kd
ፌስቡክ ግሩፕ👉 https://tinyurl.com/35h95dnt
ከአንቂ መጽሐፍት ገጾች👇https://tinyurl.com/59kr77px
ቲክቶክ👉 tiktok.com/
ዩቲዩብ👉 http://bit.ly/3ygCER3

23/08/2024

Address

Ephrata
Abba
79

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ከመጻሕፍት ዓለም posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category