Thanks. Ethiopia

Thanks. Ethiopia ለቀልድ
(1)

24/08/2022
24/08/2022

አንድ ፕሮጀክት አሳክተን የምንረካ አይደለንም!!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
‹‹የስራ ባህላችንን መቀየር አለብን ፤ ስንፍናን እያስወገድን ፤ መታከትን ለአእምሯችን ሳንነግረው የበለጠ እየተጋን ፤ 24/7 የስራ ሰዓታችን አድርገን ፤ በሺፍት ጭምር እየሰራን ፤ ኢትዮጵያን መቀየር አለብን፡፡

ይሄንን አጠናክረን የምንቀጥል እንጂ አንድ ፕሮጀክት አሳክተን የምንረካ አይደለንም፡፡
እንደዛ ካልሆነ መሰረታዊ ለውጥ አናመጣም፡፡ የተወሰኑ ስራዎችን ልናሳካ እንችል ይሆናል፤ ዘላቂ ለውጥ ግን ልናስመዘግብ አንችልም››

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

10  ሰዓትን  በመሲ  ሪዞርት  ወደድኳት ፣  12  ሰዓትን  እየጣፈጠችን  ተቀየምኳት ፣
24/08/2022

10 ሰዓትን በመሲ ሪዞርት ወደድኳት ፣ 12 ሰዓትን እየጣፈጠችን ተቀየምኳት ፣

ነሐሴ 18፤2014-ውድ የመሴ ሪዞርት አድማጮቻችን የፌስቡክ ገፃችንን ላይክ እና ሼር
በማድረግ ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን።
# MesseResort # መሴሪዞርት
የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል ወቅታዊ መረጃዎችን እና
ፕሮግራሞችን ይከታተሉ...
https://bit.ly/3mIehRv

23/08/2022

"በማወቅም ሆነ ባለማወቅም የተዛባ፣ ተገቢና የማይመለከታቸውን ዘገባ የሚዘግቡ የማህበራዊ ሚዲያ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ እናሳስባለን"
- የኢፌዴሪ መከለከያ ሚኒስቴር
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)

ከኢፌዴሪ መከለከያ ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫ

የሠራዊታችንን ወቅታዊ ሁኔታ፣ባልተረጋገጡ፣ ባልተገቡ መረጃዎችና አሉባልታዎች የመዘገብ ወይም የማራገብ አሉታዊ ሙከራዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ በጥብቅ ስለ ማሳሰብ የተሰጠ መግለጫ።

የህዝባችን ድጋፍ እና ተሳትፎ ጠንካራ መሆን፤ መከላከያ ሰራዊት የሀገር ሉዓላዊነትን ለመጠበቅ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት ወሳኝ መሆኑን በፅናት ያምናል፡፡

በህዝባችን እና በሰራዊታችን የተገነባው መተማመንና መደጋገፍ በፅኑ መሰረት ላይ የቆመ በመሆኑ፣ ፈተናዎች በጋራ እያለፍን የሃገራችንን አንድነትና ሉዓላዊነት አስከብረን ቆይተናል፡፡

ወደፊትም ጠላቶቻችን የሚደግሱልንን ሴራ እና ወጥመድ አውቀን በማክሸፍ ለዕኩይ ዓላማቸው የማንበገር መሆናችንን በተግባር እያሳየን እንቀጥላለን፡፡ ይህ የጋራ ታሪካችንና ተስፋችን አይቀሬ ቢሆንም ለድላችን የምንከፍለው ዋጋ እንዲቀንስ ግን ጠንካራ ስራ ያስፈልገናል፡፡

ጠላቶቻችን ከሰሞኑ ግልፅ አደጋ ለመፍጠር አስበው በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ሰርጎ የገባው አልሸባብ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኃይሉ መደምሰሱ ይታወቃል፡፡

በሰሜኑ የሃገራችን ክፍልም አሸባሪው የህወሃት ቡድን የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ ይገኛል፡፡በተለይ የአሸባሪው ህወሓት አፈ ቀላጤዎች ሰሞነኛ ሰበካቸው የሰራዊታችን ስም ማጥፋት ስራዬ ብለው ተያይዘውተዋል፡፡ ተቀባይነት የሌላቸውን ሰበቦች በመደርደር መከላከያ ሰራዊታችንን በመወንጀል ዘመቻ መሰማራታቸው የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡

ለዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ጭምር እየለፈፉ ያሉት፤ "…የሰላም ድርድሩ ቴክኒካል ፈርሷል፣ መከላከያ ኃይሉን እያስጠጋ ነው…፣ መከላከያ በከባድ መሳሪያ እየደበደበን ነው…፣ …ከላይ እስከታች የዕዝ ሰንሰለቱን ጠብቆ እየተፈፀመ ያለ ጥቃት ነው…" ወዘተ በማለት የቅድመ ግጭት ጩኸታቸውን በስሙልኝ ፕሮፖጋንዳቸው እያስተጋቡት ይገኛሉ፡፡

የሃገራችን ሚዲያዎች፣ የጠላትን ሴራ እና አጀንዳ በውል ተገንዝበው የሚሞግቱ የመኖራቸውን ያህል፣ አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ዘገባዎችና መረጃዎች ይህንኑ አፍራሽ ውንጀላ ባልተገባም መልኩ እየተቀባበሉት መሆኑን አስተውለናል፡፡

ያለበቂ መረጃ የጠላትን እንቅስቃሴ መዘገብ በራሱ የህዝባችንን የዕለት ከዕለት ኑሮ ያውካል።ጠላት በዚህ ገባ፣ በዚህ ወጣ ፤ የወገን ሠራዊት በዚህ ገባ፣ በዚህ ወጣ የሚለው ወሬ በፍፁም ዜና እና የዜና ትንታኔ ሊሆን አይችልም።

ጦርነቱን እንዲዘግቡ ፍቃድ ከተሰጣቸው ውጭ በሀገር ህልውና ላይ የተቃጣን ጦርነት የሚያክል ነገር በማህበራዊ ሚዲያ ገቢ ማስገኛነት ተቆጥሮ ምንም የተረጋገጠ መረጃ ሳይኖር ወሬውን ማናፈስ የህዝባችንን መረጋጋት የሚነሳ ጉዳይ ነው ፤ የፀጥታ ሃይሎችን ተግባርንም ያውካል።

የሠራዊታችን ወቅታዊ ሁኔታ እና እንቅስቃሴ አስፈላጊ ሁኖ ሲገኝ ለህዝባችን ይፋ ስናደርግ እንደነበረው ወደፊትም በዚሁ አግባብ የሚከናወን ተግባር ሆኖ ሳለ፤ ሰራዊታችን ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት በፅናትና በጥንቃቄ፤ ተዘጋጅቶ በተጠንቀቅ በቆመበት በአሁኑ ወቅት ጠላት ባሰናዳው ፕሮፖጋንዳ ወጥመድ የተጠለፉ አሉታዊ መረጃዎች በማስተጋባት እና በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች የሰራዊታችንን እንቅስቃሴ በማሰራጨት ኃላፊነት የጎደላቸው አካላት እንዳሉም አይተናል፡፡ ይህ ድርጊት በሰራዊታችን የግዳጅ አፈፃፀም ላይ ምንም አወንታዊ ተፅኖ ሊኖረው አማይችልም።

በመሆኑም ይህን አሉታዊ ተግባር በማወቅም ሆነ ባለማወቅም የተዛባ፣ ተገቢና የማይመለከታቸውን ዘገባ የሚዘግቡ የማህበራዊ ሚዲያ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

ይህንን ተግባር በግዴለሽነት ወይም በማንአለብኝነት የሚቀጥሉና የማይታረሙ ካሉ መከላከያ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ ከመሆኑም በላይ የሰራዊቱን ምስጢር በመንዛት፣ የጠላትን አጀንዳ በማራገብ የሃገር ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥሉትን እንደ አስፈላጊነቱ የወንጀል ክስ በመመስረት ተጠያቂ ለማድረግ እንደምንገደድ በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡

የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

23/08/2022
23/08/2022



፡፡ እንደተባረክ ሆነህ ተራመድ፡፡ እንደ ተባረክ ሆነህ አስብ፡፡ እንደተባረክ ሆነህ ሥራ፡፡ ትባረካለህ፡፡


ብዙውን ጊዜ አብዝቶ የሚጎዳን የራሳችን አስተሳሰብ ነው፡፡ ራስህን የምታስርበት ምንም ምክንያት የለህም፡፡ ከሣጥኑ ውጭ ለማሰብ መሞከር ብቻ ሳይሆን ይልቁንም ምንም ሳጥን እንደሌለ ቆጥረህ አስብ፡፡


መተው ማለት መርሳት ማለት ሳይሆን ያለ ፍርሀት ማስታወስ ማለት ነው፡፡ አእምሮን ይዞ እና ትምህርቱን ቀስሞ ወደፊት መጓዝ ማለት ነው፡፡


ባህሪያችን ብዙውን ጊዜ ቁልጭ ብለው የሚታዩት ከፍ እና ዝቅ በምንል ጊዜ ነው፡፡ ከተራራው ጫፍ ላይ ስትሆን ትሁት፣ በሸለቆዎቹ ውስጥ ስታልፍ ብርቱ እና በመሀላቸውም ስትሆን ታማኝ ሁን፡፡


በአንድ ወቅት አጥተነው መኖር አንችልም ያልነውን ነገር አልፈነው አድገን እንደምንፈልገው እንኳ በቅጡ የማናውቀው ነገር ጋር በፍቅር ተወዳጅተን መቅረታችን በጣም ያስገርማል፡፡ የሕይወትን ዘገምተኛ ለውጥ ተቀበል. . .

- ምንም ያህል የውጫዊው ዓለምን ፈተናዎች ብትጋፈጥ፣ በጣም ትልቁ እና ውስብስቡ ማለፍ ያለብህ መሰናክል ግን የራስህን አእምሮ ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ በሕይወትህ ውስጥ ለሚደርሱብህ ነገሮች ሁሉ ተጠያቂው አንተ አይደለህም፤ ነገር ግን እነዚህን አላስፈላጊ ተሞክሮዎችን የፈጠሩትን የሽንፈት አስተሳሰቦች ባለማሸነፍህ ግን ትጠየቃለህ፡፡

መጽሐፍ በገበያ ላይ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል።

📗📒📕
በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)
👇

Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/

23/08/2022

ዎላይታ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ የተሰኘ አዲስ መፀሀፍ በልዩ ሁኔታ ይመረቃል
መስከረም 7/1//2015 በአብርሆት ቤተ መጻሃፍት ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ምሁራን ታዋቂ ግለሰቦች የተለያዩ ሚዲያዎች በተገኙበት በድምቀት ይመረቃል።

ይሄ "ዎላይታ በዘመናዊ ኢትዮጵያ" የተሰኘው የታሪክ መጻሐፍ በአማርኛ ቋንቋ ስለዎላይታ ህዝብ ታሪክና በኢትዮጵያ ሀገር ግንባታ ላይ ህዝቡ ስላበረከተው አስተዋፅኦ ያትታል። የታሪክ ጸሐፊው አማኑኤል አብርሃም ባባንቶ እጅግ ባማረ አጻጻፍ እንደሚያቀርብ እተማመናለሁ። ፀሐፊው ከዚህ ቀደምም የመረጃ ነፃነት በኢትዮጵያ በሚለው መጽሐፉ በኢትዮጵያ የተጀመረው ለውጥ በምን መልኩ መጠናከር እንዳለበት የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል።
በጋዜጠኝነት፣ በፖለቲካ አመራርነት አሁን ደግሞ በዲፕሎማሲው ረገድ ያካበተውን ልምድ ተጠቅሞ ታሪካችንን የሚያድስ ገፀ በረከት ይዞ እንደሚመጣ አስባለሁ ። ለአካባቢው ልማት ለወሰደው ተነሳሽነትም ክብር አለኝ!!!
ገዝተው እንዲያነቡት ለወዳጅ ዘመድም እንዲያጋሩት ተጋብዘዋል። መልካም ንባብ!🙏

ሀገሩን  ደሞቹንና   በፈተናዎች   የታጠበች  ነፍስ  ጋሀነምን  እንጂ  ማንንም   ❤አትፈራም❤
23/08/2022

ሀገሩን ደሞቹንና በፈተናዎች የታጠበች ነፍስ ጋሀነምን እንጂ ማንንም ❤አትፈራም❤

Abiy Yilma Media ....ሣድስ ቲቪ .......በጠቅላላ ዕውቀት እና የሥነምግባር ሳይንስ ላይ የሚያተኩር የቴሌቪዢን ፕሮግራም ነው፡፡ በአሐዱ ቲቪ ዘወትር እሁድ ምሽት ከ2፡00-3፡00 እጅግ አስተማሪ ፕሮግራ.....

Address

`Alem Gena

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Thanks. Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category