26/08/2026
ፈተና ውጤት ተስፋ ያስቆረጣት ወጣት በቦኖራ ወንዝ ውስጥ ገብታ ህይወቷን አጣች 😭😭😭😭😭😭
በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ዳዬ ከተማ የብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት ማነስ ያስከፋት አንዲት ወጣት በቦኖራ ወንዝ ውስጥ ገብታ ህይወቷን ማጣቷ ተገለጸ።
ወጣቷ እራሷን ወንዝ ውስጥ በመጣል ህይወቷን ማጥፋቷ የተነገረ ቢሆንም፣ አስክሬኗ እስካሁን እንዳልተገኘና የፍለጋ ስራው ቀጣይ መሆኑ ታውቋል።
የትምህርት ውጤት የወጣቶችን ህይወትና የመጨረሻ ዕድላቸው የሚወስን ባለመሆኑ፣ ማህበረሰቡና ቤተሰብ በውጤት ምክንያት ተስፋ የሚቆርጡ ወጣቶችን በስነ-ልቦና የመደገፍና የማጽናት ሃላፊነት እንዳለባቸው ተመላክቷል።