10/09/2019
እኛ ኢትዬጲያኖች ተፋቅረው: ተዋደው በደማቸው አና በአጥንታቸው ባቆዩልን በአንዲት ነፃነቷ በታወጀ ሀገረ እየኖርን : ትላንት መተን ምንም ባላደረግንላት ሀገረ ኢትዬጺያ መኖር በጀመርን አንድ ቀን ሳይሞላን እኛው እራሳችን በቀኝ ግዛት ለመያዝ እና እምየ ኢትዮጵያ የሚባለውን የወርቅ ስሟን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ሌት ተቀን ይፏድዳሉ። እስቲ አስቡት የምንከተለው እምነት ይለይ እንጂ: የተፈጠርውን ከ አንድ ፈጣሪ: የመጣንበትም የዘር ሀረጋችን ከ አንድ አዳምና ህይዋን። ታዲያ አዳም ና ህይዋን አማራ: ኦሮሞ:ትግራይ: አፋር: ሀረር: ጋምቤላ: ሶማሌ: ቤንሻንጉል ወይስ ደቡቤ ነበሩ? መቶ ላይሞላ አመት ይዘን ከእንሰሳ አንሰን ተባላን: እንደወራጅ ውሀ በፓለቲካው ተነዳን: ሰብአዊ ልባችንን ማዳመጥ ተሳነን: መጠቀሚያ ስንሆን ማሰብና ማየት ተሳነን። ውድ መላ ኢትዬጺያዊያን ፈጣሪ ማሰቢያ አእምሮ አስተዋይ ልብ ያድለን። ሲነዱን ከመነዳት ይጠብቀን። እንደሰው ሰው ያስብለለን