14/08/2026
የወላይታ ታሪክ ተንቀሳቃሽ ቅርስ የነበሩት ጋሽ አብርሃም ባቾሬ አርፈዋል😭
የቀድሞ የወላይታ ሶዶ ከንቲባ የነበሩ የታሪክ አዋቂ፣ ምሁር፣ የሀገር ሽማግሌ፣ የዎላይቱማ ተቆርቋሪና የጊፋታ በዓል በዩኔስኮ የዓለም የሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት እንዲመዘገብ ሌሊት ከቀን የደከሙት ትልቁ ዋርካ ጋሽ አብርሃም ባቾሬ ባደረባቸው ድንገተኛ ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይቶ በዛሬ ዕለት ከዚህ አለም ድካም ማረፋቸው ተሰምቷል።
ለቤተሰብ፣ ለወዳጅ ዘመዶች እና ለመላው የዎላይታ ህዝብ ፈጣሪ መፅናናቱን ይስጥልን። የጋሽ አብርሃም ባቾሬ መልካም ስራና ታሪካዊ አሻራ ሁሌም ሲታወስ ይኖራል።
ነፍስህ በሰላም ትረፍ😭