The Ambo Post

The Ambo Post መፅሐፍ የእውቀት ሙዳይ ነው

29/12/2025

አይ እኔ Wasihun H Diribsa ለካ ይህም ፔጅ የኔ ነበር😂

የአፋልጉኝ ተማጽኖ   | ስም ፦ ካንቺወድያ ዉብነህእድሜ፦ 60በአእለቱ የለበሰችዉ፦ ነጭ በቡኒ ዥጉርጉር ቀሚስ እና አረንጓዴ ጥለት ያለዉ ነጭ ነጠላ ነዉትናንትና 10/06/2017 ጠዋት 12:...
18/02/2025

የአፋልጉኝ ተማጽኖ

| ስም ፦ ካንቺወድያ ዉብነህ
እድሜ፦ 60
በአእለቱ የለበሰችዉ፦ ነጭ በቡኒ ዥጉርጉር ቀሚስ እና አረንጓዴ ጥለት ያለዉ ነጭ ነጠላ ነዉ

ትናንትና 10/06/2017 ጠዋት 12:00 ሰአት ላይ ቦሌ ቡልቡላ ከሚገኘው ቤታቸዉ ወደ ቡልቡላ ማርያም ቤተ ክርስትያን በሄደችበት አልተመለሰችም። እናታቻን የአይምሮ ህመም ስላለባት ልናገኛት አልቻልንም

መጥፋቷን ቡልቡላ ማርያም ማዞርያ ጤና ጣቢያዉ ጀርባ ያለዉ ፖሊስ ጣቢያ አመልክተን እነሱም የሚችሉትን እያደረጉልን ይገኛሉ።

እናንተም በተቻላቹ አቅም ተባበሩን

ኢትዮጵያውያን በፈጣሪ ስም ይሁንባችሁ እናታችንን እፋልጉን።

ስልክ:-

ልጅ :- 0941145551
0920603574

እናንት ደጋግ ኢትዮጵያውያን እባካችሁ ሼር አድርጉት 🙏🙏🙏 እባካችሁ

ሰላም ለኢትዮጵያ  #ሼር በማድረግ ሰላምን አብስሩልዩ ዜና ትግራይ “ በሃይማኖት አባቶች የተጀመረው የሽምግል እና የእርቅ እንዲሁም የካቲት 11 በጋራ የማክበር እንቅስቃሴ አልተሳካም አሉ “ ...
18/02/2025

ሰላም ለኢትዮጵያ #ሼር በማድረግ ሰላምን አብስሩ
ልዩ ዜና ትግራይ

“ በሃይማኖት አባቶች የተጀመረው የሽምግል እና የእርቅ እንዲሁም የካቲት 11 በጋራ የማክበር እንቅስቃሴ አልተሳካም አሉ “ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ።

ፕሬዜዳንቱ ለእርቅ እና ሽምግልና አለመሳካት “ ቡድን “ ሲሉ የጠሩትን አካል ተጠያቂ አድርገዋል።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባወጡት መግለጫ “ መንግስት የማያውቀው ርችት በመተኮስ የሚያጋጥም ችግር ካለ ተጠያቂው ቡድኑ ነው “ ብለዋል።

አላስፈላጊ የአመፅ እንቅስቃሴዎች እየታዩ መሆናቸው የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ፤ ህዝቡ አከባቢውን በልዩ ሁኔታ በመጠበቅ በዓሉ እንዲያከብር አሳስበዋል።

ከቀናት በፊት ለእርቅና ሽምግልና ፍቃደኛ መሆናቸው በትግራይ የሃይማኖት አባቶች መግለጫ የተሰጠባቸው ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳና የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በትናንቱ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እጅ ለእጅ ሲጨባበጡ የሚያሳይ ፎቶ መለቀቁ ብዙዎች አስደስቶ ነበር።

ዋና ዋና ምክንያቶች...-የሆድ ቁርጠት ካለ -ከራባቸው -የአጥንት ሕመም ካላቸው -የአፍንጫ መታፈን ካለ-ከመጠን በላይ ልብስ ካለበስናቸው -መልበስ ካለባቸው በታች ካለበስናቸው -የሆድ ውስጥ ...
18/02/2025

ዋና ዋና ምክንያቶች...
-የሆድ ቁርጠት ካለ
-ከራባቸው
-የአጥንት ሕመም ካላቸው
-የአፍንጫ መታፈን ካለ
-ከመጠን በላይ ልብስ ካለበስናቸው
-መልበስ ካለባቸው በታች ካለበስናቸው
-የሆድ ውስጥ ጥገኛ ትላትል ካላቸው
-ዳይፐር የሚታሰርበት ቦታ ላይ ሽፍታ ካለ
-ነፍሳት ከነከሳቸው
-የሚረብሽ ድምፅ ከሰሙ
-የታችኛው የመተንፈሻ አካል መጥበብ ካለው
-ከፍተኛ የሆነ ብርሀን ካዩ

ልጅ በሚያልቅስበት ጊዜ ምን ማድረግ አለብን...?
-ከመጠን በላይ ልብስ ካለበስናቸው ያንን መቀነስ
-ዳይፐራቸውን ማየት
-ጡት ማጥባት
-የሚረብሻቸው ድምጽ ካለ ያንን መቀነስ
-የክፍሉን ብርሃን ማመጣጠን
-ጡት ብቻ የሚያጠቡ ከሆነ ቡና እና ሻይ አለመጠጣት

ህፃናት ሲታመሙ ሊያሳዩዋቸው የሚችሉት ምልክቶች...
-ትኩሳት
-የማያቆርጥ ለቅሶ
-ጡት ለመጥባት መቸገር
-ከፍተኛ የሆነ ላብ
-ለመተንፈስ መቸገር
-የሰገራ ከለር መለወጥ
-መወራጨት

ህፃን ልጆዎ ሳያቋርጡ የሚያለቅሱ ከሆነ ምን ያደርጋሉ?ቢያጋሩን!

 #ያሳፍራል😭😭 ምን አይነት ሰዎች ትሆኑ??ይህች ታዳጊ   ትባላለች!የ9ኛ ክፍል ተማሪ ናት!በጣም የምትወደው አባቷን በአንድ ቀን ህመም በድንገት በሞት ካጣች 7ወር ሆኗታል!እሮብ የካቲት5 ም...
18/02/2025

#ያሳፍራል😭😭 ምን አይነት ሰዎች ትሆኑ??

ይህች ታዳጊ ትባላለች!የ9ኛ ክፍል ተማሪ ናት!በጣም የምትወደው አባቷን በአንድ ቀን ህመም በድንገት በሞት ካጣች 7ወር ሆኗታል!

እሮብ የካቲት5 ምንም ነገር ሳትናገር ቃሊቲ አካባቢ ከሚገኘው ቤታቸው ድንገት ወጥታ ጠፍታ እናት በለቅሶና በመንከራተት ለቀናት እየፈለገቻት ትላንት እሁድ የካቲት9 በ0920751657 አንድ ስልክ ይደወልላታል:-

"ፖሊስ ነኝ፣የምደውለው ከአዳማ ነው፣ልጅሽ ከመኪና ላይ ልጆች ወርውረዋት በጣም ተጎድታለች፣ ጭንቅላቷ ውስጥ ደም ፈሷል፣አሁን የምትገኘው አዳማ አጠቃላይ ሆስፒታል ነው ሪፈር ወደ አዲስ አበባ ተፅፎላታል፣...." እያላት እናት ተደናግጣ በእንባ ማውራት ስላልቻለች ልጇ ሙሉቀን ስልኩን ይቀበላታል!
ምንድነው ሲላቸው?"በህይወት እንድትተርፍ በግል ትራንስፖርትም ቢሆን በአስቸኳይ ወደ አዲስ አበባ መምጣት አለባት"ብሎ የሹፌር ስልክ ሰጣቸው፣

ሹፌር ነኝ ባዩ በ0951948455 ደውሎ በ3000ብር ተስማምቶ ፅዮን አብርሀም በሚል ቴሌብር ብሩን እንዲያስገቡ አስጠንቅቆ በመጨረሻም መንገድ እንደጀመሩና ጥቁር አንበሳ እንዲጠብቁት ነግሯቸው ወዲያውኑ ጎረቤት ወዳጅ ዘመድ ተጨማምረው እያለቀሱ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ደረሱ!!

ከደቂቃዎች በኋላ "የት ደረሳችሁ?" ለማለት ስልክ ሲደውሉ ዝግ ሆነ፣ፖሊስ የተባለው ጋርም ሲሞክሩ አይሰራም፣እንደገና ደውለው ጎማቸው እንደተበላሸና በሌላ መኪና እንዲመጡ ገንዘብ እንዲልኩላቸው ሲጠይቋቸው እያታለሏቸው ሊሆን እንደሚችል ጠረጠሩ!አዳማ ያለ ዘመድ ጋር ደውለው ወደ ሆስፒታል ሲሄዱ በዕለቱ የተመዘገበ አደጋ እንደሌለና እንዲህ የምትባልም ታማሚ እንደሌለች ሰሙ!!ጉዳዩ ሿሿ እንደሆነ አወቁ‼️

አስቡት በጭንቀታችሁ ላይ ገንዘብ ለማግኘት ብለው በውሸት ፈጠራ ወሬ ሌላን ሰው ለማሳመምና ለመግደል የሚሞክሩ እንደነዚህ ያሉ ብዙ ነውረኞች አሉ! #ተጠንቀቁ🙏 ልቧ የተሰበረው እናት #ሼር በማድረግና በፀሎት ቢያንስ የጠፋችውን ልጇን በማገናኘት ወደ ሳቋ እንመልሳት🙏 እናንተ ነውረኞችም የትም አታመልጡም!
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

0913151226-
0912072849

እሰይ ነጋ ተመስገንእሰይ ነጋ እሰይ ነጋ ላመሰግንህ ነው አይኔን የከደንኩት አንተን አምኜ ነው አይኔን የከደንኩት አንተን አምኜ ነው በበደሌ ሳትፈርድ ትጠብቀኛለህ ከእኔ በላይ ለእኔ ታስብልኛ...
18/02/2025

እሰይ ነጋ ተመስገን

እሰይ ነጋ እሰይ ነጋ ላመሰግንህ ነው
አይኔን የከደንኩት አንተን አምኜ ነው
አይኔን የከደንኩት አንተን አምኜ ነው

በበደሌ ሳትፈርድ ትጠብቀኛለህ
ከእኔ በላይ ለእኔ ታስብልኛለህ
የማታንቀላፋው ቸሩ እረኛዬ
ብርሃኑን ያየሁት ባንተ ነው ጌታዬ
አዝ...
ቀናቶቼን ሰጠሁ ላንተው አሳልፌ
በሰላም እተኛለሁ በክንድህ አርፌ
ተመስገን ማለትን በብርሃን ጨለማ
ታስተምረኛለህ በወፎቹ ዜማ
አዝ...
ትናንትናን ታልፎ ስላየሁ አዲስ ቀን
ከእንቅልፌ ስነቃ እላለሁ ተመስገን
አንተ ባታነጋው የጨለመውን
አልኖርም ነበረ ዛሬ ባልኩት ቀን
አዝ...
ሁሉም የሚሆነው እንደየሥራቱ
በአንተ ብቻ እኮ ነው መጨለም መንጋቱ
ስለ አደረክልኝ ምኔን ልክፈልህ
ተመስገን ብቻ ነው ሥላሴ ዋጋህ
አዝ..
በብርሃን ተተካ አስፈሪው ጨለማ
እንደኔማ ሳይሆን ምህረትህ ቀድማ
የእኔ ያልኳት ዛሬ ነግታ የምትመሸው
በጥበቤ አይደለም በበጎነትህ ነው

ስታመሰግኑ በደስታ ዋሉ!

Warra   Kun eenyu?
17/02/2025

Warra Kun eenyu?

አምቦዎች ከዚህ ውስጥ ማንን ታውቃላችሁ ??
17/02/2025

አምቦዎች ከዚህ ውስጥ ማንን ታውቃላችሁ ??

+++ የማርያም መንገድ +++ ድሮ በልጅነት ከባልንጀሮች ጋርበየጎዳናው ላይ ስንበር ስንባረር አባራሪው ደርሶ መንገዱን ከዘጋከግራና ከቀኝ ማምለጫ ካሳጣ ተባራሪ ምስኪን መንገድ የጠበበውበጭንቁ...
17/02/2025

+++ የማርያም መንገድ +++

ድሮ በልጅነት ከባልንጀሮች ጋር
በየጎዳናው ላይ ስንበር ስንባረር

አባራሪው ደርሶ መንገዱን ከዘጋ
ከግራና ከቀኝ ማምለጫ ካሳጣ

ተባራሪ ምስኪን መንገድ የጠበበው
በጭንቁ 'ሚጠራት አንዲት ዋስ አለችው

የእርሷን ስም ካነሣ የጠበበ ይሰፋል
የተዘጋው ሁሉ መንገድ ይከፈታል

ቀን በጎደለበት ባገኘው መከራ
በጨነቀው ስዱድ ስሟ የሚጠራ
ማርያም እርሷ ነች ሁሉን 'ምታራራ።

እናታችን እመቤታችን ድንግል ማርያም የምሕረት ቃል ኪዳን ለተቀበለችበት እለት እንኳን በሰላም አደረሰን። ጭንቅ እና መከራ በተሞላ ዓለም ውስጥ ከክፋ ቀን ሁሉ የምንወጣበትን "የማርያም መንገድ" የሰጠን አምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

"እኔ 'ፈንድቼ' ሴት ለመሳም ስደርስ፣ መጀመሪያ የሳምኳት ሴት የአሁኗ ሚስቴ ናት፡፡ እንዴት ጐበዝ ሴት መሰለችሽ? በጣም ነው የምወዳት፡፡ ከፍታውንም ዝቅታውንም በፍቅር አልፈን፣ ሁለት ልጆች...
17/02/2025

"እኔ 'ፈንድቼ' ሴት ለመሳም ስደርስ፣ መጀመሪያ የሳምኳት ሴት የአሁኗ ሚስቴ ናት፡፡ እንዴት ጐበዝ ሴት መሰለችሽ? በጣም ነው የምወዳት፡፡ ከፍታውንም ዝቅታውንም በፍቅር አልፈን፣ ሁለት ልጆች ወልደን አብረን በሰላም እየኖርን ነው፡፡ እቴ የልጅነቴ እንዴት ነሽ (በድምፁ እያንጐራጐረ) የሚለው ዘፈኔ የተዘፈነው ለእሷ ነው፡፡ ሁለታችንም እድለኞች ነን፤ ደስተኞች ነን፡፡ በሙያዋም ጐበዝ ነርስ ነች፡፡"
- ድምጻዊ አብዱ ኪያር በአንድ ወቅት ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ ከተናገረው

Address

Ambo
Shewa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when The Ambo Post posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to The Ambo Post:

Share

Category