Visit Hadiyya

Visit Hadiyya ከምክንያት ወደ ውጤት!

ካነበብኳቸው ውስጥ በጣም ያሳቀኝን የአልበርት አንስታይና የቻርሊ ቻፕሊን ወግ ጀባ ልበላቹ እንደ ጎርጎሮሲያኑ የጊዜ ቀመር 1931G.C የ አለማችን የphysics ሊቅ በመባል የሚጠራው አልበር...
05/10/2022

ካነበብኳቸው ውስጥ በጣም ያሳቀኝን የአልበርት አንስታይና የቻርሊ ቻፕሊን ወግ ጀባ ልበላቹ እንደ ጎርጎሮሲያኑ የጊዜ ቀመር 1931G.C የ አለማችን የphysics ሊቅ በመባል የሚጠራው አልበርት አኒስታይን ቻርሊን አግኝቶት እንዲህ ሲል አድናቆቱን ገለጸለት> አለው ቻርሊ ቻፕሊን እንዲህ ሲል መለሰለት > ሲል መለሰለት። ይመቻቹ ሰናይ ቀን

ውድ የምትለውንና በእጅህ የሚገኘውን ነገር ስጠኝ፡፡ እንዲህ አይነቱ የመስጠት ልማድ  ይዞልህ የሚመጣው በረከት ዕልፍ-አእላፍ ነው፡፡
02/10/2022

ውድ የምትለውንና በእጅህ የሚገኘውን ነገር ስጠኝ፡፡ እንዲህ አይነቱ የመስጠት ልማድ ይዞልህ የሚመጣው በረከት ዕልፍ-አእላፍ ነው፡፡

በዛሬው ጊዜ ስለ እኩልነት፣ ስለ መብትና ስለ ነፃነት ብዙ ሲነገር እንሰማለን። በበርካታ የዓለም ክፍሎች ያሉ ሰዎች ከጭቆና፣ ከአድልዎና ከድህነት ነፃ መውጣት ይፈልጋሉ። ሌሎች ደግሞ የመናገር...
01/10/2022

በዛሬው ጊዜ ስለ እኩልነት፣ ስለ መብትና ስለ ነፃነት ብዙ ሲነገር እንሰማለን። በበርካታ የዓለም ክፍሎች ያሉ ሰዎች ከጭቆና፣ ከአድልዎና ከድህነት ነፃ መውጣት ይፈልጋሉ። ሌሎች ደግሞ የመናገርና የመምረጥ እንዲሁም የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ነፃነት እንዲሰጣቸው ይጠይቃሉ። በእርግጥም፣ የፈለጉትን የማድረግ ወይም በፈለጉት መንገድ ሕይወታቸውን የመምራት ነፃነት በየትኛውም ቦታ የሚኖሩ ሰዎች ትልቅ ቦታ የሚሰጡት ጉዳይ ይመስላል።

1ኛ ይህን ፍላጎታቸውን ለማሟላት የሚሞክሩት ግን በምን መንገድ ነው? ከማኅበራዊና ከፖለቲካዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ብዙዎች የሚፈልጉትን ለማግኘት ሲሉ ተቃውሞ ያሰማሉ፤ ሰልፍ ይወጣሉ፤ ዓመፅ ያነሳሳሉ ብሎም አብዮት ያካሂዳሉ። ይሁን እንጂ እንዲህ ያለው አካሄድ የታለመለትን ግብ ማሳካት ችሏል? በፍጹም፤ እንዲያውም አብዛኛውን ጊዜ ለብዙ መከራና ለበርካቶች ሕይወት መጥፋት ምክንያት ይሆናል።

2ኛ በዛሬው ጊዜ ያሉ ብዙ ሰዎች፣ አንድ ሰው እውነተኛ ነፃነት አለው የሚባለው ድርጊቱ ስለሚያስከትለው ውጤት ሳይጨነቅ የፈለገውን ሁሉ ማድረግ ከቻለ ብቻ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ዘ ወርልድ ቡክ ኢንሳይክሎፒዲያ ነፃነት ማለት “የመምረጥና የመረጡትን ነገር የማድረግ ችሎታ” እንደሆነ ይገልጻል። ሆኖም የሚከተለውን ተጨማሪ ማብራሪያም ይሰጣል፦ “ከሕግ አንጻር ሲታይ ሰዎች ነፃ ናቸው የሚባለው ማኅበረሰቡ ፍትሐዊ ያልሆነ፣ አላስፈላጊ ወይም ምክንያታዊነት የጎደለው ገደብ እስካልጣለባቸው ድረስ ነው።” ይህም በማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉ ሰዎች በሙሉ ነፃነት እንዲኖራቸው፣ የተወሰኑ ገደቦች እንደሚያስፈልጉ ይጠቁማል። አሁን የሚነሳው ጥያቄ ‘ፍትሐዊ፣ አስፈላጊና ምክንያታዊ የሚባሉት ገደቦች የትኞቹ እንደሆኑ የመወሰን መብት ያለው ማን ነው?’ የሚል ነው።

❤️ደስተኛ ለመሆን ነፃ ሁን፣በፍቅር ውስጥ ወጥመድ የለም፡፡ ደስተኛ ከሆንክ ሁሉም ድርጊትህ ደስታን መፍጠር ይችላል፣ ስቃይን ከመረጥክ፣ሁሌም በውስጥህ ስቃይን ታመርታለህ ፣የአዕምሮህ መጥፎ ሀ...
01/10/2022

❤️ደስተኛ ለመሆን ነፃ ሁን፣በፍቅር ውስጥ ወጥመድ የለም፡፡ ደስተኛ ከሆንክ ሁሉም ድርጊትህ ደስታን መፍጠር ይችላል፣ ስቃይን ከመረጥክ፣ሁሌም በውስጥህ ስቃይን ታመርታለህ ፣የአዕምሮህ መጥፎ ሀሳብ ካሸነፈ አንተንም ሆነ ሌሎችን ይመርዛል።

❤️እራስህን በሰላም ፣ በብርሃን ፣ በጥበብ ፣ በንቃተ-ህሊና ሸፍነው፡፡ የአንተ ሃላፊነት ይህ ነው ፡፡ደስታ እና ርህራሄ በህይወት መንገድህ አይለዩህ፣ ከተፈጥሮ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘህ ኑር ፡፡ ይህን ለማድረግ ሁሌም ከልብህ ጀምር።
ሁሌም ይህን አድርግ፣ሁሌም ይህንን ሁን ፡፡
ዉብ አሁን❤️

ኢሬቻ የምስጋና በዓልኢሬቻ የምስጋና በዓል ነው። የኦሮሞ ሕዝብ ምድር እና ሰማይን ለፈጠረው ፈጣሪው ዋቃ ምስጋናውን ለማድረስ የኢሬቻ በዓልን ያከብራል ይላሉ የማኅበረሰቡ ባህላዊ መሪዎች። የኦ...
01/10/2022

ኢሬቻ የምስጋና በዓል

ኢሬቻ የምስጋና በዓል ነው። የኦሮሞ ሕዝብ ምድር እና ሰማይን ለፈጠረው ፈጣሪው ዋቃ ምስጋናውን ለማድረስ የኢሬቻ በዓልን ያከብራል ይላሉ የማኅበረሰቡ ባህላዊ መሪዎች። የኦሮሞ ሕዝብ ከዘመን ወደ ዘመን በሰላም ላሸጋገረው አምላክ ምስጋና የሚያቀርብበት በዓል ነው፤ ኢሬቻ። የኦሮሞ ታሪክ ምሁሩ ዲሪቢ ደምሴ፤ "ኢሬቻ ማለት ዋቃ (ፈጣሪ) የፈጠረውን ማመስገን ማለት ነው" ይላሉ። ማኅበራዊ ደረጃ እና የእድሜ ልዩነት ሳይፈጠር የኦሮሞ ሕዝብ የኢሬቻ በዓልን ለዘመናት በጋራ ሲያከብር ቆይቷል። ኢሬቻ የዘመን መለወጫ በዓልም ነው። የኦሮሞ ሕዝብ ክረምቱ በማለፉ በኢሬቻ ቀን ምስጋናውን ለፈጣሪ ያቀርባል። በክረምት ወራት ተራርቆ ሳይገናኝ የቆየ ዘመድ አዝማድ መስከረም ላይ ይገናኛል። ሕዝቡም ክረምቱን በፈጣሪ ፍቃድ የሞላው ውሃ ጎድሎ ከዘመድ አዝማድ አገናኝን ብሎ ምስጋና ያቀርባል።

Address

Hossana
Shewa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit Hadiyya posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to Visit Hadiyya:

Share

Category