VISIT SOUTH OMO

VISIT SOUTH OMO “Making Ethiopia among the top five tourist destinations in Africa by 2025”. Land of origins

‎‎የደቡብ ኦሞ ዞን ቱሪዝም መምሪያ በ2018 ዓ.ም አፈፃፀምና በ2019 ዓ.ም በጀት አመት እቅድ ዙርያ ውይይት አደረገ‎‎ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም (የደቡብ ኦሞ ዞን ቱሪዝም መምሪያ-ዲመካ)‎‎...
13/08/2026

‎‎የደቡብ ኦሞ ዞን ቱሪዝም መምሪያ በ2018 ዓ.ም አፈፃፀምና በ2019 ዓ.ም በጀት አመት እቅድ ዙርያ ውይይት አደረገ

‎ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም (የደቡብ ኦሞ ዞን ቱሪዝም መምሪያ-ዲመካ)

‎የደቡብ ኦም ዞን ቱሪዝም መምሪያ በ2018 ዓ.ም አጠቃይ የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም እና የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ ዙርያ የመምሪያው ኃላፊ አቶ አጉሞ ሎኮርዮ እና አጠቃላይ ሠራተኛ በተገኘበት ተወያይቷል።

‎ በምክር ቤት የኢኮኖሚ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ተቋሙ በጠንካራና ደካማ ጎኖች ዙርያ በተገመገመበት ወቅት እንዲሁም የዞኑ ፐብልክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ በቢሮው በመገኘት ባደረጉት የምዘና ሂደት ውሰጥ መምሪያው በሪፈርም ስራ የተሻለ አፈፃፀም እንዳለው የተገመገመ ሲሆን እንደ ክፍተት በዓመቱ ከህዝብ ክንፍ ጋር ውይይቶች አለመደረጋቸው እንደ ክፍተት የታየ በመሆኑ በቀጣይ በቋሚነት በየሩብ ዓመቱ ከህዝብ ክንፍ ጋር ውይይት ለማድረግ መግባባት ላይ ተደርሷል።

‎በ2019 ዓ.ም በጀት አመት ተቋማዊ የማስፈፀም አቅምን በማሻሻል የአገልግሎት አሰጣጥን ማሣደግ እንደሚገባ ፣የዞኑን የቱሪዝም አለኝታዎች በመለየት መዳረሻዎችን ማልማትና ማስፋፋት፣የፕሮሞሽንና ግብይት ስራዎችን በማጎልበት የጎብኚዎችን ፍሰት መጨመር እንደሚገባ በውይይት ወቅት የተነሱ ሀሳቦች ናቸው። በዞኑ የሚገኙ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጥራታቸውን በማሣደግ ቱሪዝም ለዞኑ እየሠጠ ያለውን የኢኮነሚ ድርሻ በተገቢው እንዲወጣ ለማድረግ መስራት እንደሚገባም መግባባት ላይ ተደርሷል።

‎በውይይቱ ማጠቃላያ የቢሮ መግብያና መውጫ ሰዓትን በማክበር፣የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን እንዱሁም የሰብዓዊ ድጋፍ ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ መስራት እንደሚገባ የመምሪያው ኃላፊ አሳስበዋል።

‎በደቡብ ኦሞ ዞን የሚገኙ የአከባቢ አስጎብኚ ማህበራት የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባርን አጠናክረው ቀጥለዋል‎‎ነሐሴ 6/2018 ዓ.ም( የደቡብ ኦሞ ዞን ቱሪዝም መምሪ...
12/08/2026

‎በደቡብ ኦሞ ዞን የሚገኙ የአከባቢ አስጎብኚ ማህበራት የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባርን አጠናክረው ቀጥለዋል

‎ነሐሴ 6/2018 ዓ.ም( የደቡብ ኦሞ ዞን ቱሪዝም መምሪያ-ዲመካ)

‎በደቡብ ኦሞ ዞን አከባቢን በማስጎብኘት ዘርፍ ተደራጅተው የሚገኙ የኢቫንጋዲ የአከባቢ አስጎብኚ ማህበር ፣ የካራ ቆርጮ የአከባቢ አስጎብኚ ማህበር፣የራቴ የአከባቢ አስጎብኚ ማህበር የአቅመ ደካማ ቤት በመገንባት፣የደም ልገሳ በማድረግ፤በአከባቢ ፅዳት እንዲሁም ለቱሪስቶች ማረፍያ ቤቶችን በማዘጋጀት የዘንድሮውን የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እያከናወኑ ይገኛሉ።
‎የኢቫንጋዲ የአከባቢ አስጎብኚ ማህበር ለአንዲት አቅመ ደካማ ሴት የመኖሪያ ቤት ለመገንባት ከቱርሚ ከተማ አስተዳደር የቤት መስርያ ቦታ በመረከብ የግንባታ ስራውን የጀመሩ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ በመጨረስ ለአቅመ ደካማዋ ቤቱን ለማስረከብ በትጋት ላይ ይገኛሉ።

‎የካራ ቆርጮ የአከባቢ አስጎብኚ ማህበር የካራ ብሄረሰብ ባህልና ድንቅ የተፈጥሮ ገፅታን ለመጎብኘት ለሚመጡ እንግዶች መጠለያ የሚሆን የሳር ጎጆን በመስራት በጎ ተግባራቸውን ፈፅመዋል። እንዲሁም በአከባቢያቸው የሚገኘውን የሶላር ሀይል አመንጪ ስፍራ ንፁህ እና ፅዱ እንዲሆን የማፅዳት ተግባር አከናውነዋል።

‎በተመሣሣይ የበጎ ተግባር አገልግሎት በዳሰነች ወረዳ የሚገኙ የራቴ የአከባቢ አስጎብኚ ማህበር አባላትም የደም ልገሳ በማድረግ የዜግነት ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል።

10/08/2026
Amazing home at Nyangatom District,Nakule
07/08/2026

Amazing home at Nyangatom District,Nakule

2026, Part Of National Tree-planting Campaigns at Omo Valley
03/08/2026

2026, Part Of National Tree-planting Campaigns at Omo Valley

‎የዱር እንስሳት መመናመን (መጥፋት ወይም ቁጥራቸው መቀነስ) በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያም ሆነ በመላው ዓለም ትልቅ የስነ-ምህዳር ስጋት ነው።‎‎መፍትሄዎች‎‎ደኖችንና ፓርኮችን መጠበቅ፦ ብሔራዊ ...
16/07/2026

‎የዱር እንስሳት መመናመን (መጥፋት ወይም ቁጥራቸው መቀነስ) በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያም ሆነ በመላው ዓለም ትልቅ የስነ-ምህዳር ስጋት ነው።

‎መፍትሄዎች

‎ደኖችንና ፓርኮችን መጠበቅ፦ ብሔራዊ ፓርኮችን ከህገ-ወጥ ሰፈራና ከከብት ስምሪት ነፃ ማድረግ።

‎ህግን ማጥበቅ፦ በህገ-ወጥ አዳኞች እና የዱር እንስሳት ውጤቶች በሚነግዱ አካላት ላይ ከባድ ቅጣት መጣል

‎የህብረተሰብ ግንዛቤ፦ የአካባቢው ማህበረሰብ የዱር እንስሳትን ጠቀሜታ አውቆ እንዲጠብቃቸው ማስተማር።

የደቡብ ኦሞ ዞን ቱሪዝም መምሪያ

2026 Omo Valley Expedition "with Adimasu Tour Company
14/07/2026

2026 Omo Valley Expedition "with Adimasu Tour Company

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሴት ሬንጀሮች ሳምንት እየተከበረ ይገኛልሰኔ 19/2018 ዓ.ም - ዲመካ‎‎ዓለም አቀፍ የሴቶች ሬንጀር ሳምንት (World Female Ranger Week) በየዓመቱ ከሰኔ...
26/06/2026

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሴት ሬንጀሮች ሳምንት እየተከበረ ይገኛል

ሰኔ 19/2018 ዓ.ም - ዲመካ

‎ዓለም አቀፍ የሴቶች ሬንጀር ሳምንት (World Female Ranger Week) በየዓመቱ ከሰኔ 16 ጀምሮ ለአንድ ሳምንት እ የሚከበር ሲሆን፣ የዱር አራዊትና የተፈጥሮ ሀብትን ከአደን እና ጥፋት የሚጠብቁ ጀግኖች ሴት የደን ጠባቂዎችን (ሬንጀሮችን) ሥራ የሚደግፍና የሚያከብር ዓለም አቀፍ ቀን ነው።

‎በዓለም አቀፍ ደረጃ ከጠቅላላው የሬንጀር ኃይል ውስጥ ሴቶች የሚይዙት ከ 11% በታች በመሆኑ ይህ ሳምንት የሴቶችን ሚና ከፍ በማድረግ በዘርፉ ያላቸውን ተሳትፎ ለማበረታታት ያለመ ሲሆን በወንዶች ተይዞ በቆየው በዚህ የጥበቃ ሥራ ሴቶች ለዱር አራዊት ጥበቃ፣ ለአካባቢ ማህበረሰብ ግንኙነት እና ለሰላም ያላቸውን ልዩ አስተዋጽኦ ለማሳየትም ጭምር ነው።

‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኘው እና 1942 ስኩየር ኪሎ ሜትር ስፋት ባለው እንዲሁም ከ20 በላይ ቀበሌዎች በሚያዋስኑት በማጎ ብሔራዊ ፓርክ በቅርብ ጊዜ በሴት ሬንጀርነት ተቀጥራ በመስራት ላይ የምትገኘው ወጣት ሰብሌ ሰብስቤ ከእነዚህ ጀግና ሴቶች ተጠቃሽ ነች።

‎ የደቡብ ኦሞ ዞን ቱሪዝም መሞሪያ
‎ ዲመካ

Address

Hamer
Jinka

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when VISIT SOUTH OMO posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to VISIT SOUTH OMO:

Shortcuts

Share