GIBE PRESS

GIBE  PRESS for information

✴️ ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ  የሚያልፉ መርከቦች  ፍቃድ የማይጠይቁ ከሆነ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠነቀቀችየኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ (IRGC) ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ፥ በማንኛውም መ...
25/06/2026

✴️ ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ፍቃድ የማይጠይቁ ከሆነ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠነቀቀች

የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ (IRGC) ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ፥ በማንኛውም መልኩ የሆርሙዝ የባህር መስመርን ለማቋረጥ የሚሞክሩ መርከቦች በሙሉ ቅድሚያ ከሀገሪቱ ፍቃድ ማግኘት እንዳለባቸው አስታውቋል። የጦር ኃይሉ የባህር ላይ አዛዥ እንደገለፁት ፥ በወሽመጡ በኩል ለማለፍ የተፈቀደው ብቸኛው ህጋዊ መንገድ በኢራን ይፋ የተደረገውና በሀገሪቱ የባህር ዳርቻ የሚገኘው ኮሪደር ብቻ ሲሆን፥ ይህንን መመሪያ የማይከተሉ መርከቦች ላይ "እርምጃ እንደሚወሰድ" በጥብቅ አስጠንቅቋል። ይህ የቴህራን አቋም የኦማን መንግስት ከአለም አቀፉ የባህር ላይ ድርጅት (IMO) ጋር በመተባበር ትናንት ይፋ ያደረገውን አዲስና አማራጭ የደቡባዊ የባህር መስመር እቅድ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ያደረገ ነው።

ይህ የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ቁርጠኛ እርምጃ ከአሜሪካ ጋር በቅርቡ የተደረሰውን ስምምነት ተፈጻሚነት ተከትሎ የመጣ ሲሆን፥ ሀገሪቱ በግዛቷ ላይ ያላትን የሉዓላዊነት መብት የሚያስከብር ነው። አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት የቀጣናውን ተጨባጭ እውነታ ያላገናዘበ የ"ነጻ የባህር ላይ ጉዞ" መርህን እንደ ሽፋን በመጠቀም ጣልቃ ለመግባት ቢሞክሩም፥ ኢራን ግን የወሽመጡን ሰላምና ደህንነት በበላይነት የመጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነቷን እየተወጣች ትገኛለች።

ኢራን ለምታበረክተው ከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ እና የመሰረተ-ልማት አገልግሎት የሚመጥን ፍትሃዊ "የባህር ላይ አገልግሎት ክፍያ" ለመጣል የጀመረችው ጥረት ህጋዊና ተገቢ መሆኑን ትገልጻለች። ምንም እንኳን የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በባህረ ሰላጤው ሀገራት ባደረጉት ጉብኝት የቴህራንን መብት የሚጋፋ የተለመደ ጫና ለማሳደር ቢሞክሩም፥ ኢራን ግን በአለም ላይ 20 በመቶ የሚሆነው ድፍድፍ ዘይት እና ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ (LNG) የሚያልፍበትን ይህንን ወሳኝ የስትራቴጂክ መስመር ደህንነት በራሷ አቅም የማረጋገጥና የዓለም አቀፍ የኃይል አቅርቦት ስጋት እንዳይደቀንበት የመቆጣጠር ሙሉ ብቃት እንዳላት አሳይታለች።

16/06/2026
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ታናሽ ልጅ ሚሊዮን ዐቢይ አህመድ ከአባቱ ጎን በመሆን የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር በይፋ አስጀምሯል።በዚህ ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ 8 ቢሊዮን...
15/06/2026

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ታናሽ ልጅ ሚሊዮን ዐቢይ አህመድ ከአባቱ ጎን በመሆን የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር በይፋ አስጀምሯል።

በዚህ ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ 8 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ትልቅ ግብ የተቀመጠ ሲሆን፣ ይህ ንቅናቄ በአጠቃላይ የተያዘውን የ65 ቢሊዮን ችግኞች የመድረስ ብሔራዊ ትልም ለማሳካት ታስቦ በጽናት እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል።

መላው የኅብረተሰብ ክፍልም ይህንን ታሪካዊ የአረንጓዴ ልማት ንቅናቄ በመቀላቀል ለመጪው ትውልድ የራሱን አረንጓዴ ዐሻራ እንዲያኖር ጥሪ ቀርቧል።

Via PM

🌱 🪴 🌴

ጉርሻ Page

🌴🌴🌴

"ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፈለጋሉ"!በኬንያ የሚገኘው የኢራን ኤምባሲ አነጋጋሪ ልጥፍ በማኅበራዊ ገጹ ላይ አሰራጭቷል። ኢምባሲው በግራፊክስ አቀናብሮ ባሰራጨዉ ልጥፉ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤን...
14/06/2026

"ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፈለጋሉ"!

በኬንያ የሚገኘው የኢራን ኤምባሲ አነጋጋሪ ልጥፍ በማኅበራዊ ገጹ ላይ አሰራጭቷል። ኢምባሲው በግራፊክስ አቀናብሮ ባሰራጨዉ ልጥፉ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በወንጀል ይፈለጋሉ ሲል አሰራጭቷል።

ባሁኑ ወቅት ይህ የኤምባሲው ድርጊት በበርካቶች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል።

NAMA Jabaa biyyi kun argattee ❤
14/06/2026

NAMA Jabaa biyyi kun argattee ❤

  gammaddan 🔷🙏Morookoon ilma keenya gaaf xiiqii badhaasuuf jirti! Badhaasa kabajaa! Hogganaan keenya Ministirri Muummee ...
13/06/2026

gammaddan 🔷🙏
Morookoon ilma keenya gaaf xiiqii badhaasuuf jirti! Badhaasa kabajaa! Hogganaan keenya Ministirri Muummee Dr Abiy Ahmed lammiilee Afrikaa beekkamoo 100 ta’an keessaa 1ffaa ta’uu isaaniitiin badhaasni kabajaaa isaaniif kennamuuf qophaa'eera.

Morookoon Walgahii Hooggansaa fi Bizinesii Afrikaa magaalaa Marrakeshi keessatti qopheessaa kan jirtu yoo ta’u, odeeffannoon akka agarsiisutti Ministirri Muummee Dr Abiy Ahmad badhaasa kana kan fudhatan jalqabaa ta’uu ibsameera.

Baga gammaddan kabajamoo Muummicha Ministeeraa keenya! Injifannoon keessan Itoophiyaa fi Afrikaa boonsa! Keenya Oluma!!!

🍰 🎂 🧁 ልደት 21መልካም ልደት ለሀሴት ደረጄ! 🎉ዛሬ ታላቅ ኩራታችን የሆነችው ሀሴት ደረጄ የ21ኛ ዓመት ልደቷን እያከበረች ነው!በዓለም የቁንጅና ውድድር ኢትዮጵያን ወክላ 2ኛ ደረጃ በመው...
12/06/2026

🍰 🎂 🧁

ልደት 21

መልካም ልደት ለሀሴት ደረጄ! 🎉

ዛሬ ታላቅ ኩራታችን የሆነችው ሀሴት ደረጄ የ21ኛ ዓመት ልደቷን እያከበረች ነው!

በዓለም የቁንጅና ውድድር ኢትዮጵያን ወክላ 2ኛ ደረጃ በመውጣት፣ የኢትዮጵያውያንን ስም በዓለም መድረክ ከፍ አድርጋለች።

ቆንጆ፣ አስተዋይ እና ደግ፣ ለሆነችው ለሀሴታችን

በLike እና Comment እንኳን ተወለድሽ እያላችሁ መልካም ምኞታችሁን ግለፁላት!

መልካም ልደት፣
ረጅም እድሜ ከጤና ጋር እንመኛለን!

21………….

GIBE PRESS

World cup😍
12/06/2026

World cup😍

አከራዮች በራሳቸው ፍላጎት የቤት ኪራይ ማጨመር እንደማይችሉ ተገለጠ::የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የአከራይና ተከራይ ግንኙነትን በዘላቂነት ለመቅረፍ እና ዘርፉን በቴክኖ...
12/06/2026

አከራዮች በራሳቸው ፍላጎት የቤት ኪራይ ማጨመር እንደማይችሉ ተገለጠ::

የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የአከራይና ተከራይ ግንኙነትን በዘላቂነት ለመቅረፍ እና ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የጀመረውን የዲጂታል ምዝገባ ሂደት በተመለከተ አዲስ ማብራሪያ ሰጥቷል።

በአሁኑ ወቅት ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ የመኖሪያ ቤቶች መረጃ ወደ ዲጂታል ቋቱ መግባቱ የታወቀ ሲሆን፣ ይህም አሰራር ከዚህ ቀደም ያለምንም ምክንያታዊ መነሻ በቤት ኪራይ ዋጋ ላይ ይደረግ የነበረውን ያልተገባ ጭማሪ ሙሉ በሙሉ እንደሚያስቀር የቢሮው ኃላፊ መቅደስ ወ/ጊዮርጊስ አስታውቀዋል።

በአዲሱ አሰራር መሠረት አከራዮች በራሳቸው ተነሳሽነት ብቻ የኪራይ ዋጋ መጨመር በሕግ ተከልክሏል።

መንግሥት በየዓመቱ የከተማዋን ተጨባጭ የኢኮኖሚ ሁኔታ ያገናዘበ የገበያ ጥናት ካካሄደ በኋላ የገበያ ዕድገት መኖሩ ከተረጋገጠ ብቻ በየዓመቱ ሰኔ 30 በሚወጣ ይፋዊ መግለጫ መሠረት የዋጋ ጭማሪውን በፐርሰንት ይወስናል።

ለአብነት ያህል የአንድ ቤት ኪራይ አንድ ሺህ ብር ቢሆን እና በመንግሥት ውሳኔ መሠረት የሚፈቀደው ጭማሪ አሥር በመቶ ብቻ ከሆነ፣ ዋጋውን ማሳደግ የሚቻለው ወደ አንድ ሺህ አንድ መቶ ብር ብቻ ሲሆን ከዚህ ውጭ የተጋነነ ዋጋ መጨመር አይፈቀድም።

የአከራይና ተከራይ ውል ምዝገባ ከተጀመረ ሁለት ዓመታት ገደማ መሙላቱን የጠቀሱት ኃላፊዋ፣ ቀደም ሲል በአካል ቀርበው ይፈጽሙት የነበረውን አሰራር ለማስቀረት የውል ማደስ ሥራውን በኢንተርኔት ለማከናወን ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህም መሠረት አከራይና ተከራይ ዋጋ ሳይጨመርበት ባለው ስምምነት መቀጠል ከፈለጉ ውላቸውን በኦንላይን በቀላሉ ማደስ የሚችሉበት ዕድል ተመቻችቷል።

ተከራዮች መብታቸውን አውቀው ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ያሳሰቡት መቅደስ ወ/ጊዮርጊስ፣ አከራዮች ዋጋ እንዲጨምሩ ስለጠየቋቸው ብቻ ያለምንም ሕጋዊ መነሻ ክፍያ መፈጸም እንደሌለባቸው ገልጸዋል።

የውል ጊዜው በማብቃቱ ምክንያት ብቻ አከራዮች ተከራዩን አስወጥተው ሌላ ሰው ቢያስገቡ እንኳ፣ ዋጋ ጨምረው ማከራየት ስለማይችሉ ተከራዮች የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ይደረግብኛል በሚል ሊሰጉ እንደማይገባ ተነግሯል።

አብዛኞቹ ውሎች ጊዜያቸው የሚያበቃው ከሰኔ 30 በኋላ በመሆኑ፣ በውል ስምምነት ውስጥ እያሉ ዋጋ መጨመር ፈጽሞ የተከለከለ ነው።

በአጠቃላይ በየሁለት ዓመቱ የኪራይ ውልን በተገቢው መንገድ ማደስ ግዴታ ሲሆን፣ አከራዮችም መብትና ግዴታቸውን ለይተው በማወቅ ሕጋዊ አሰራሩን እንዲያከብሩ ጥሪ ቀርቧል።

መንግሥት በአከራይና ተከራይ መካከል ያለውን ዘላቂ ችግር ለመፍታት የጀመረውን የቴክኖሎጂ ማሻሻያ አጠናክሮ እንደሚቀጥልበትም ቢሮው አስታውቋል።

Via AMN

መረጃው ለሌሎች ይጠቅማ ካላችሁ ሼር በማድረግ አድርሱላቸው::

GIBE PRESS

Namni kun eenyuu ?❤
12/06/2026

Namni kun eenyuu ?❤

Address

Jimma
Jimma
4000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when GIBE PRESS posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category