Moseb

Call Contact the establishment

Moseb My name is samson I am from ethiopia and i interest waching different enducated moves and creative ideologies.

03/10/2026

🌟 Do not give up; remain committed to pursuing your goals.

🔥 The effort you invest today will contribute to the achievements you can take pride in tomorrow.

💪 Challenges are not merely obstacles; they are opportunities that lead to growth and success.

✨ Believe in your abilities, and work toward achieving what may initially seem impossible.

🏆 Patience + Effort + Faith = Success
tube

25/09/2026
"አይ አንች"ሰዎች ባንተ ላይ ያላቸው ፍላጎት ሲቀንስ በግልፅ "አልፈልግህም" ለማለት ድፍረት ስለሚያጥራቸው በተለያዩ ምክንያቶች ስሜታቸውን ሊደብቁ ይሞክራሉ። አንድ ሰው አንተ ላይ ፍላጎት እ...
21/09/2026

"አይ አንች"
ሰዎች ባንተ ላይ ያላቸው ፍላጎት ሲቀንስ በግልፅ "አልፈልግህም" ለማለት ድፍረት ስለሚያጥራቸው በተለያዩ ምክንያቶች ስሜታቸውን ሊደብቁ ይሞክራሉ።

አንድ ሰው አንተ ላይ ፍላጎት እንደሌለው/እንዳጣ የምታውቅባቸው የሳይኮሎጂ መንገዶች ልንገርህ፦

ተነሳሽነት ማጣት (Lack of Effort) ፡ ሁልጊዜ መደወል፣ ቴክስት ማድረግም ሆነ ለመገናኘት ጥያቄ የምታነሳው አንተ ብቻ ከሆንክ ትልቁ ምልክት ነው። በእውነት ፍላጎት ያለው ሰው ጊዜ አጥቶ እንኳን ጊዜ ይፈጥራል እንጂ ግንኙነቱን በአንተ ትከሻ ላይ ብቻ አይጥለውም።

ተደጋጋሚ ሰበብ ማብዛት (Constant Excuses) ፡ ጊዜ አብራችሁ ለማሳለፍ ስትጠይቅ ሁልጊዜ "ስራ በዝቶብኛል"፣ "አልተመቸኝም" ወይም "ደክሞኛል" የሚሉ ሰበቦች ይበዛሉ። ቅድሚያ የሚሰጠው ሰው መሆንህ ስትቀር፣ ሰበብ የዕለት ተዕለት ልማዳቸው ይሆናል።
አጭር እና የደረቀ ምላሽ ፡ ቴክስት ስታደርግ ከብዙ ሰዓታት በኋላ አጭርና የደረቀ ምላሽ (ለምሳሌ "እሺ"፣ "አዎ") ብቻ የሚሰጡህ ከሆነ፤ እንዲሁም ውይይቱን ለማስቀጠል ምንም ጥረት የማያደርጉ ከሆነ ላንተ ያላቸው ትኩረት መሞቱን ያሳያል።

ስሜታዊ ርቀት እና ግዴለሽነት ፡ ስለ ውሎህ፣ ስለ ስሜትህ ወይም ስለ ህይወትህ ማወቅ አይፈልጉም። አብራችሁ ስትሆኑም ሀሳባቸው ሌላ ቦታ ነው፤ አንተን ከማዳመጥ ይልቅ ስልካቸው ላይ ያተኩራሉ፤ ደስታህም ሆነ ሀዘንህ ስሜት አይሰጣቸውም።

ሲግማ (Sigma) ከሆንክ የአንድን ሰው ፍላጎት ማጣት ስትረዳ አትለምንም፣ አትጨቀጭቅም እንዲሁም "ለምን ተቀየርክ/ሽ?" ብለህ አትጠይቅም። ዝም ብለህ የራስህን ዋጋ አውቀህ በፀጥታ ርቀትህን ትጠብቃለህ። ውድ ጊዜህንና ጉልበትህን ላንተ ቦታ በሌለው ሰው ላይ አታባክንም፤ ይልቁንም ትኩረትህን ራስህን ማሳደግ ላይ ታደርጋለህ!

Banteyrega Mequanint

• የተዘነጋው የራብ እና የጠኔው ነገር …"…ከወራት በፊት ሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ትግሬ እና ጠለምት ጎንደር  ዐማራው በዝናብ እጥረት ምክንያት ገበሬው የቤት እንስሳቱና ሰዎችም ጭምር በራብ ...
13/09/2026

• የተዘነጋው የራብ እና የጠኔው ነገር …

"…ከወራት በፊት ሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ትግሬ እና ጠለምት ጎንደር ዐማራው በዝናብ እጥረት ምክንያት ገበሬው የቤት እንስሳቱና ሰዎችም ጭምር በራብ እና በጥም መሞታቸው ሲዘገብ፣ የተዘራው እህልም ከመሬት ብቅ ሳይል መድረቁ ሲነገር ነበር። ነገር ግን ጉዳዬ ብሎ በቁምነገር ስለ።መፍትሄው ያወራ ሰውም የለም ነበር።

"…ቀጥሎ አፋር ክልል በዝናብ መጥፋት ምክንያት እንስሳት ጭምር መሞት መጀመራቸውን ሲዘገብ እንዲሁ ዝምታ ነበር በሀገሪቱ የሰፈነው። ይኸው ዛሬም ለስንተኛ ጊዜ እንደሆነ አላውቅም አፋር በድርቅ መጠቃቱን የሀገር ውስጥ ጋዜጣው ሪፖርተር በፊት ለፊት ገጹ ይዞ ወጥቷል። አሁንም ለጉዳዩ አባ ከና ያለው የለም። ዜናው ሁሉ አቢይ አሕመድ፣ አዲስ አበባ፣ ሪዞርት ብቻ ነው። ኮሪደር ልማት፣ የወንዝ ዳር ልማት፣ ብሪክስ…

"…ይሄ ሁላ ሲሆን የኦሮሞ አክቲቪስቶች እና ቦለጢቀኞች ለብቻቸው ከዳር ቆመው ይሸልሉ፣ ይፎክሩ፣ የኦሮሞን ልማት፣ የእርሻውን ስፋት የስንዴ እርሻውን ልምላሜ ነበር በስፋት እያሳዩ የሚጎርሩት። እንዲያውም ሰሜን ዐማራና ትግራይ በኃጢአታቸው ምክንያት ዝናብ ያጡ እስኪመስል ድረስ ነበር ፕሮፓጋንዳቸውን ያጧጡፉት የነበረው። በእነሱ ቤት እነሱ ጻድቅ ሌላው ኃጥእ መሆኑ ነው። መስሎሃል።

"…ይኸው ዛሬ ከአዲስ አበባ አፍንጫ ስር በኦሮሚያ የተዘራው እህል ልምላሜው ሲያስፎክራቸው የነበሩትን አንገት አስደፍቶ እህሉ ለአበባም፣ ለፍም ሳይደርስ ክችች፣ ድርቅ፣ ጥውልግ ብሎ አክቲቪስቱም ማለቃቀስ ጀምሯል። ኦሮሚያ ክልል ዝዋይ አጠገብ፣ አዳሚ ቱሉ ኮምቦልቻ ወረዳ ነው። በየገጠሩ ገበሬው መጪውን ጊዜ ፈርቶ እያለቀሰ ነው። የከተማው ኗሪ እና ቲክቶከር፣ ካድሬው ግን ሚዲያ በእጁ ስላለ ጠግቦ፣ ልቡ ተደፍኖበት ጮቤ እየረገጠ ነው።

• ብቻ ነገርየው ከበድ ያለ ይመስላል።
ምንጭ ከዘመዴ

እንኳን በሰላም ወደ ነፃነት ተመለስክ! ክሪስ፣ የእግዚአብሔር እጅ ከአንተ ጋር ነበረች፤ ዛሬም በሰላም ከእስር መፈታትህ ትልቅ ደስታ ነው። “እግዚአብሔር የተሰበረውን ልብ ያድሳል፣ የደከመውን...
11/09/2026

እንኳን በሰላም ወደ ነፃነት ተመለስክ!

ክሪስ፣ የእግዚአብሔር እጅ ከአንተ ጋር ነበረች፤ ዛሬም በሰላም ከእስር መፈታትህ ትልቅ ደስታ ነው።

“እግዚአብሔር የተሰበረውን ልብ ያድሳል፣ የደከመውንም ያበረታል።”

ያለፈው ይቅርታ፣ የዛሬው ምስጋና፣ የነገውም ተስፋ ይሁንልህ።
ከዚህ በኋላ በሰላም፣ በጤና፣ በፍቅርና በበረከት የተሞላ አዲስ ምዕራፍ እንዲሆንልህ እመኛለሁ።

እንኳን ደህና መጣህ ክርስቲያን!
እግዚአብሔር ይጠብቅህ፣ ይምራህም!

✨🎉 እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ! 🇪🇹❤️አዲሱ ዓመት…🌿 የሰላም ዓመት ይሁን፣❤️ የፍቅር ዓመት ይሁን፣🙏 የበረከት ዓመት ይሁን፣🌟 የህልሞቻችሁ እውን የሚሆኑበት ዓመት ይሁን!ያለፈውን በ...
10/09/2026

✨🎉 እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ! 🇪🇹❤️
አዲሱ ዓመት…
🌿 የሰላም ዓመት ይሁን፣
❤️ የፍቅር ዓመት ይሁን፣
🙏 የበረከት ዓመት ይሁን፣
🌟 የህልሞቻችሁ እውን የሚሆኑበት ዓመት ይሁን!
ያለፈውን በምስጋና፣
ዛሬን በደስታ፣
ነገን በተስፋ እንቀበል። 🥰✨
ለእኔ ውድ ቤተሰቦቼ፣ ጓደኞቼና ወዳጆቼ ሁሉ—
መልካም፣ ደስተኛና በረከት የተሞላ አዲስ ዓመት! 🎊❤️🇪🇹

ይነበብ ,ይነበብ (ምንጭ ከ ስለ እናት ገፅ ላይ የተወሰደ) «በጣም አሳዛኝ ታሪክ ስለሆነ ልብ ብለው ያንብቡት»ታሪኩ እውነተኛ ይሁን እንጂ የፊልም ባለሞያዎች ወደ ፊልም ቀይረውእንባ በሚያራጭ...
09/09/2026

ይነበብ ,ይነበብ
(ምንጭ ከ ስለ እናት ገፅ ላይ የተወሰደ) «በጣም አሳዛኝ ታሪክ ስለሆነ ልብ ብለው ያንብቡት»
ታሪኩ እውነተኛ ይሁን እንጂ የፊልም ባለሞያዎች ወደ ፊልም ቀይረው
እንባ በሚያራጭ መልኩ ሰርተውታል።
እኔም የታሪኩ ጭብጥ ስለ መሰጠኝና እናንተም እንደምትወዱት
ስላመንኩ ታሪኩን አጠር አጠር አርጌ አንዳንድ የራሴንም ሀሳብ
አክዬበት ላካፍላችሁ ወደድኩ።

ነገሩ እንዲህ ነው፦በሊባኖስ ሀገር ከሚገኘው በአንድ ትምህርት ቤት
ውስጥ መምህሯ ክፍል/ክላስ/ ገብታ ስታስተምር ከተማሪዎቹ አንዱ
ይነሳና "መምህር እቃ ተሰርቂያለሁ" ይላል።

መምህሯም በስርቆቱ እጅግ ተበሳጭታ የተሰረቀው እቃ ምን እንደሆነ
ካጣራች ቡኀላ ተማሪዎች ለፍተሻ እንዲዘጋጁ አደረገችና ፍተሻዋን
ቀጠለች።
፡
በፍተሻው ሰዓት ታዲያ አንዲት እድሜዋ 10 ኣመት እማይሞላ ተማሪ
ተራዋ ደርሶ ቦርሳዋን እንድትከፍት ስትጠየቅ አሻፈረኝ ትላለች።
፡
መምህሯም በንዴት ጡፋ ምራቋን ፊቷ ላይ ተፍታባት አንቺ ሌባ ኣንቺ ነሽ
የሰረቅሽው ፓሊስ ነው ምጠራልሽ እያለች ስትጮህ በአጋጣሚ በክፍሉ
በር ሲያልፋ የሰሙት የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር(ዳይሬክተር) ከተፍ
ይላሉ።
:
ይህን ጊዜ ልጅቷ የባሰ ድንጋጤና ፍርሃት እያንቀጠቀጣት እባክሽ ይቅር
በይኝ እኔ ሌባ አደለሁም ከፈለግሽ እንኪ ፈትሽኝ ግን እዚህ ተማሪዎች
ፊት አደለም እያለች መምህሯ እግር ስር ወድቃ ልመናዋን ቀጠለች።
:
መምህሯ ግን የተማሪዋን ስሜት ለአፍታ ቆም ብላ ለመረዳት ከመሞከር
የከፋ ስሜት ውስጥ ሆና እየደነፋች ነው።
፡
በዚህ ጊዜ በእድሜ ጠና ያሉት ሴት ዳይሬክተር ቆይስቲ መምህር ምን
እንደተፈጠረ ንገሪኝ ብለው ዳይሬክተሯ መምህሯንና ተማሪዋን ወደ ቢሮ
ወሰዷቸው።
፡
ከዛም ልጅቷን በተረጋጋ ሁኔታ እንድትቀመጥ ቢያደርጉም መምህሯ ግን
እስካሁን መረጋጋት አልቻለችም።
፡
ይሄኔ በመምህሯ ድርጊት ጥቂት ብስጭት ያላቸው ዳይሬክተሯ
መምህሯን ገላመጠው ዝም እንድትል ካደረጉ ቡኃላ ልጅቷን እረጋ
ብለው "ቦርሳው ውጥ ምንድነው ያለው" ብለው ጠየቋት።
፡
ልጅቷም "ቦርሳው ውስጥ ያለው ተማሪዎች በልተው የጣሉት ትርፍራፊ
ነው ያለው" አለች በህፍረት እየተሸማቀቀች።
፡
ዳይሬክተሯም በመገርምና ባለማመን ስሜት
"እንዴት እንዲህ ይሆናል" ሲሉ ጠየቋት።
፡
እሷም "ለወንድሞቼ ልወስድላቸው ብየ ነው" አለች አንገቷን ደፍታ
በሚያሳዝን ሁኔታ ቅስሟ ተሰብሮ።
፡
ይህን ጊዜ ዳይሬክተሯ ከመቀመጫቸው ተነስተው ተጠጓትና ፀጉሯን
እየደባበሱ "ኣይዞሽ የኔ ልጅ ተረጋግተሽ ስለ አባትሽና ስለ እናትሽ ንገሪኝ
አሏት።
፡
ይህች ኣንዲት ፍሬ ልጅ እንባዋ እየወረደ እንዲህ ኣለች " ኣባቴ
በሽፍርና ነበር እሚያስተዳድረን ቡኃላ ግን በሃሽሽ ተጠርጥሮ ወህኒ ቤት
ገባ። እናቴም ብትሆን ምንም ገቢ ያልነበራት ስትሆን ያባቴን መታሰር
ስትሰማ እራሷን ስታ ሆስፒታል ግባች።በዛው የተነሳ ሽባ ሁና
ቀረች።ታዲያ ሁለት ጨቅላ ወንድሞች ኣሉኝ ቤት ነው ጥያቸው
የመጣሁት ዘመድ ስለሌለን ዘወር ብሎ እሚያየን የለም።እሚላስ
እሚቀመስ የለንም።ታዲያ ይችን ፍርፋሪ ወስጄ ሂይወታቸውን ብታደጋት
ብዬ አሰብኩና ተማሪዎች አስተርፈው የጣሉትን ሳያዩኝ ለቃቅሜ ቦርሳየ
ውስጥ ኣስገባሁ።ይሄን ነው ያደረኩት።እናም እባካችሁ ለተማሪዎች
እንዳትነግሩብኝ።ትምህርቴንም ቢሆን አቋርጣለሁ።ብቻ አትናገሩብኝ
እያለች አንጀት በሚያላውስ ሁኔታ እንባዋን በአራት መንታ
እያዘነበች ችግሯን ምንም ሳትደብቅ በልጅ አንደበቷ እተኮላተፈች
ለማስረዳት ሞከረች!

08/09/2026

Yaya construction I know d/f critical point of construction by followed this yaya construction this page is mandatory for me thank you for giving your advise .

07/09/2026

አማርኛ ዓለማቀፍ ቋንቋ ሆኗል።

የአማርኛ ቋንቋ በዓለም አቀፍ ደረጃ በበርካታ ሀገራት በሚገኙ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የምርምር ተቋማት እና የቋንቋ ማዕከላት ውስጥ በጥናት፣ በምርምር እንዲሁም በዲግሪና በሰርተፊኬት ደረጃ ይሰጣል።

ለአብነት ለመጥቀስ ያህል፣

ጀርመን፡-
በሀምቡርግ ዩኒቨርሲቲ (University of Hamburg)፣ በፍራንክፈርት ዩኒቨርሲቲ እና በላይፕዚግ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ጥናት (Ethiopian Studies) እና በሴማዊ ቋንቋዎች ትምህርት ክፍል ሥር።

ሩሲያ፦
በሞስኮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ (Moscow State University - ISAA) እና በሴንት ፒተርስበርግ ስቴት ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ ጥናት ክፍሎች።

ጣሊያን፡-
በናፖሊ ዩኒቨርሲቲ (University of Naples "L'Orientale") እና በሮም ሳፒየንዛ ዩኒቨርሲቲ (Sapienza University of Rome)።

እንግሊዝ (ብሪታንያ)፡-
በለንደን ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ እና ምስራቅ ጥናት ትምህርት ቤት (SOAS - School of Oriental and African Studies)።

ፈረንሳይ፡-
በፓሪስ ከንቲባ የውጭ ቋንቋዎች እና ሥልጣኔዎች ተቋም (INALCO)።

ፖላንድ፡-
በዋርሶ ዩኒቨርሲቲ (University of Warsaw) በአፍሪካ ቋንቋዎችና ባህሎች ክፍል ውስጥ።

አሜሪካ (ዩናይትድ ስቴትስ)፡-

- በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ (Harvard University)

- በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ (Columbia University)

- በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ (Stanford University)

- በኢንዲያና ዩኒቨርሲቲ (Indiana University)

- በፎሎሪዳ ዩኒቨርሲቲ (University of Florida)

- በሚቺጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ (Michigan State University)

እስራኤል፡-
በቴል አቪቭ ዩኒቨርሲቲ እና በኢየሩሳሌም ዕብራይስጥ ዩኒቨርሲቲ (Hebrew University of Jerusalem)።

ጃፓን፡-
በኦሳካ ዩኒቨርሲቲ እና በቶኪዮ የውጭ ሀገራት ጥናት ዩኒቨርሲቲ (TUFS)።

ቻይና፡-
በቤጂንግ የውጭ ሀገራት ጥናት ዩኒቨርሲቲ (Beijing Foreign Studies University)።

ኬንያ፡-
በናይሮቢ ዩኒቨርሲቲ እና በሌሎች የቋንቋ ማዕከላት።

ጂቡቲ፡-
በጂቡቲ ዩኒቨርሲቲ እና በባህል ማዕከላት።

ደቡብ አፍሪካ፡-
በኬፕ ታውን ዩኒቨርሲቲ (በአፍሪካ ጥናቶች ሥር በተለያዩ ጊዜያት)።

አማርኛ ቋንቋ የኢትዮጵያ ከምትኮራባቸው የማይዳሰሱ ሀብቶች አንዱ ነው።

በሰሜን ጎንደር ጠለምት ወረዳ በደረሰ የመሬት መንሸራተት በትንሹ የአንድ ሰው ሕይወት አለፈ፤ ከ2,200 በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ።በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት (ደጃች ሜዳ) ወረዳ ግ...
01/09/2026

በሰሜን ጎንደር ጠለምት ወረዳ በደረሰ የመሬት መንሸራተት በትንሹ የአንድ ሰው ሕይወት አለፈ፤ ከ2,200 በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ።
በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት (ደጃች ሜዳ) ወረዳ ግልቤና ቀበሌ ምጥባራ በተባለ ቦታ ከነሐሴ 16 እስከ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በተከሰተ ተከታታይ የመሬት መንሸራተት የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን እና ከ2,242 በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ።
በአካባቢው በተከታታይ እየጣለ ባለው ኃይለኛ ዝናብ ምክንያት የመሬት መንሸራተቱ እየተባባሰ እንደሆነ ተነግሯል። ነዋሪዎቹ የደረሰው አደጋ እጅግ ከባድ በመሆኑ ነፍሳቸውን ብቻ ማትረፍ መቻላቸውን ተናግረዋል። በርካታ የቤት እንስሳት በመሬት ናዳ መቀበራቸውንም አመልክተዋል። እንደዚያም ሆኖ ግን አንድ የጠለምት ወረዳ ባለሥልጣን በአደጋው በ200 ሄክታር መሬት ላይ የሚገኝ ሰብል መውደሙን አረጋግጠዋል።

Address

Injibara

Telephone

+251915271286

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Moseb posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to Moseb:

Shortcuts

Share

Category