Revo Music

Revo Music Ethiopian music videos and concert videos

ጭራ ቀረሽ አስደናቂ የመድረክ ስራ
03/10/2025

ጭራ ቀረሽ አስደናቂ የመድረክ ስራ

🎶 Revo Addis – Your Ultimate Ethiopian Music Hub! 🎶Welcome to Revo Addis, the #1 destination for the best Ethiopian music, Amharic songs, Ethiopian hits, a...

17/09/2025

በ1988 በሀገር ፍቅር መድረክ የቀረበ አዝናኝ የ80ዎቹ ዳንስ ።

አርቲስቷ ማናት?

💥💥ባሳለፍነው ሳምንት በዩቲዩብ ከፍተኛ ተመልካችን ያገኙ የሳምንቱ ምርጥ አስር ሙዚቃዎች የሚከተሉት ናቸው የትኛው ሙዚቃ የበለጠ ተመቻቹ?  ምንጭ : yenevibe.com
15/09/2025

💥💥ባሳለፍነው ሳምንት በዩቲዩብ ከፍተኛ ተመልካችን ያገኙ የሳምንቱ ምርጥ አስር ሙዚቃዎች የሚከተሉት ናቸው
የትኛው ሙዚቃ የበለጠ ተመቻቹ?

ምንጭ : yenevibe.com

አረጋኽኝ ወራሽ በወጣትነቱ በሀገር ፍቅር ቴያትር ሙሉ ቪዲዮውን በዚህ ሊንክ ይከታተሉ 👇🏼
12/09/2025

አረጋኽኝ ወራሽ በወጣትነቱ በሀገር ፍቅር ቴያትር
ሙሉ ቪዲዮውን በዚህ ሊንክ ይከታተሉ 👇🏼

🎶 Revo Addis – Your Ultimate Ethiopian Music Hub! 🎶Welcome to Revo Addis, the #1 destination for the best Ethiopian music, Amharic songs, Ethiopian hits, a...

🌼 ከብረው - ይቆዩን 🌼እንኳን ከዘመን ዘመን አሸጋገራችሁ ሪቮ ሚውዚክ  አዲሱ አመት ከፍ የምትሉበት እንዲሆን ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል ።መልካም በዓል
10/09/2025

🌼 ከብረው - ይቆዩን 🌼

እንኳን ከዘመን ዘመን አሸጋገራችሁ

ሪቮ ሚውዚክ አዲሱ አመት ከፍ የምትሉበት እንዲሆን ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል ።
መልካም በዓል

ተፈራ ነጋሽ  | ምነው ቀዘቀዘ ቅራችን  - በ1988 በሀገር ፍቅር መድረክ 👇
05/09/2025

ተፈራ ነጋሽ | ምነው ቀዘቀዘ ቅራችን - በ1988 በሀገር ፍቅር መድረክ 👇

🎶 Revo Addis – Your Ultimate Ethiopian Music Hub! 🎶Welcome to Revo Addis, the #1 destination for the best Ethiopian music, Amharic songs, Ethiopian hits, a...

ኢትዮጵያን የታደገው ኮንሰርት ፡በሙዚቃ ታሪክ እጅግ ዝነኛ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሚባሉ ኮንሰርቶች መሀል አንዱ የሆነው The Live Aid concert ከአርባ አመታት በፊት በጁላይ 13 198...
03/09/2025

ኢትዮጵያን የታደገው ኮንሰርት

በሙዚቃ ታሪክ እጅግ ዝነኛ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሚባሉ ኮንሰርቶች መሀል አንዱ የሆነው The Live Aid concert ከአርባ አመታት በፊት በጁላይ 13 1985 ተካሂዶ ነበር
በ1977 ዓ.ም በሀገራችን ኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረውን ድርቅ መነሻ በማድረግ BBC የሰራውን ዘገባ ተከትሎ ለተጎጂ ወገኖች አስፈላጊውን ገንዘብ ለማሰባሰብ ያለመው ይህ ኮንሰርት ያኔ እጅግ ዝነኛ ሙዚቀኛ በነበሩት በቦብ ጌልዶፍ እና ሚጅ ዩሬ መሪነት የተካሄደ ሲሆን ረሀብን ሲጋፈጡ ለነበሩ ሚሊየኖች ህይወትን ማስቀጠል የቻለ የሙዚቃ ድግስ ነበር
የዚህ የሙዚቃ ድግስ ሀሳብ የመጣው ሁለቱ አርቲስቶች የብሪቲሽ እና የአይሪሽ ሙዚቀኞችን በማሰባሰብ Do They Know it’s Christmas የተሰኘውን ሙዚቃ Aid ሲሉ በሰየሙት ባንድ ማካይነት ለመስራት መንቀሳቀስ ከጀመሩ በኋላ ነበር
ይህ ነጠላ ዜማ ከተለቀቀ በኋላ በመላው አለም በሚሊየን የሚቆጠሩ አድማጮችን ማግኘት የቻለ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ በሙዚቃ ታሪክ ከተመለከትናቸው አስደናቂ ኮንሰርቶች መሀል ስሙ ከፊት የሚነሳው ኮንሰርት እንዲዘጋጅም ምክንያት ሆኗል
ይህን ኮንሰርት ለየት የሚያደርገው ዋነኛ ነገር በሁለት ስታዲየሞች በተመሳሳይ ሰዓት መደረጉ ነበር።ኮንሰርቱ ለንደን በሚገኘው ዌንብሌይ ስታዲየም እና በፊላደልፊያ በሚገኘው JFK ስታዲየሞች በመቶሺዎች ታድመውበት በአስደናቂ ሁኔታ ተከናውኗል
ይህንን ታሪካዊ ኮንሰርት በአጠቃላይ በ150 ሀገራት የሚገኙ 1.9 ቢሊየን ሰዎች በቀጥታ ስርጭት የተከታተሉት ሲሆን ይህም ቁጥር በሙዚቃ ኮንሰርት ታሪክ ሪከርድ ሆኖ መቀመጥ ችሏል
በወቅቱ በሙዚቃው ኢንደስትሪ ስማቸው ገናና የሆኑና በብዙዎች የሚወደዱ በርካታ አርቲስቶች የተሳተፉበት ይህ ኮንሰርት ከ125 ሚሊየን ዶላር በላይ ማሰባሰብ ችሎ ነበር ። ያ ገንዘብም በትግራይ ለነብረው አስከፊ የረሀብ ቀውስ ብዙ መፍትሄን ይዞ የመጣ ፀጋ ነበር
The Live Aid concert ከመዝናኛነቱም ባለፈ የአለም መንግስታት ፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች እና አለማቀፍ ተቋማት ለዚህ ችግር ትኩረት እና ምላሽ እንዲሰጡ የፈጠረው ተነሳሽነት ከገንዘቡም በላይ ትልቅ አቅም ሆኖ በታሪክ ይወሳል ።

ፀጋዬ እሸቱ | ተጓዥ ባይኔ ላይ - በ1988 በሀገር ፍቅር መድረክ 👇
29/08/2025

ፀጋዬ እሸቱ | ተጓዥ ባይኔ ላይ - በ1988 በሀገር ፍቅር መድረክ 👇

🎶 Revo Addis – Your Ultimate Ethiopian Music Hub! 🎶Welcome to Revo Addis, the #1 destination for the best Ethiopian music, Amharic songs, Ethiopian hits, a...

💎 ቦብ ማርሌ እና የጥይቱ ማስታወሻ⚡️ በ1976 ቦብ ማርሌ አንድ ትልቅ ኮንሰርት ላይ ስራዎቹን ለማቅረብ ተስማምቶ ታዳሚው ያንን ቀን በጉጉት እየጠበቀ እያለ ከኮንሰርቱ 2 ቀናት አስቀድሞ ያ...
27/08/2025

💎 ቦብ ማርሌ እና የጥይቱ ማስታወሻ

⚡️ በ1976 ቦብ ማርሌ አንድ ትልቅ ኮንሰርት ላይ ስራዎቹን ለማቅረብ ተስማምቶ ታዳሚው ያንን ቀን በጉጉት እየጠበቀ እያለ ከኮንሰርቱ 2 ቀናት አስቀድሞ ያልታወቁ ሰዎች ጥቃት ፈፅመውበት በጥይት ተመታ

⚡️ ታዲያ በኮንሰርቱ ቀን ብዙዎች በጉዳት ምክንያት ስራዎቹን አያቀርብም ብለው ቢገምቱም እሱ ግን ህመሙን ዋጥ አድርጎ በብዙ ሺህ ሰዎች ፊት ስራውን በብቃት አቀረበ

ከኮንሰርቱ በኋላ ጋዜጠኞች ለምን ያንን እንዳደረገ ሲጠይቁት እንዲህ አላቸው
“አለምን መጥፎ ለማድረግ የሚለፉ ሰዎች ያለ እረፍት እየሰሩ እኔ እንዴት ስራዬን አሳልፋለው”

⚡️ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ ⚡️🌼 አዲሱን አመት በአዲስ አልበም 🌼📌 2008 ላይ ከለቀቀችው ምስክር የተሰኘ አልበም በኋላ በአድናቂዎቿ አብዝታ የተናፈቀችው ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ ከ9 አመታት ጥበቃ...
26/08/2025

⚡️ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ ⚡️

🌼 አዲሱን አመት በአዲስ አልበም 🌼

📌 2008 ላይ ከለቀቀችው ምስክር የተሰኘ አልበም በኋላ በአድናቂዎቿ አብዝታ የተናፈቀችው ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ ከ9 አመታት ጥበቃ በኋላ " ደህና ሰው " በተሰኘ አልበም ተከስታለች

📌 አልበሟ በዛሬው እለት ለአድማጭ ይደርሳል

ጋሽ መሀሙድ አህመድ በ1988 በሀገር ፍቅር ቴያትር ያቀረበውን ስራ ይመልከቱ 👇🏼👇🏼
22/08/2025

ጋሽ መሀሙድ አህመድ በ1988 በሀገር ፍቅር ቴያትር ያቀረበውን ስራ ይመልከቱ 👇🏼👇🏼

🎶 Revo Addis – Your Ultimate Ethiopian Music Hub! 🎶Welcome to Revo Addis, the #1 destination for the best Ethiopian music, Amharic songs, Ethiopian hits, a...

💎 ይህ ወጣት ሬስዞ ሴሬስ ይባላል በሀንጋሪ የሙዚቃ ታሪክ አሻራቸውን ካሳረፉ የሙዚቃ ደራሲዎች መሀል አንዱ ነው። ታዲያ በወጣትነት ዘመኑ አንዲት ፍቅረኛው ምንነቱን ባላወቀው ምክንያት በድንገ...
21/08/2025

💎 ይህ ወጣት ሬስዞ ሴሬስ ይባላል

በሀንጋሪ የሙዚቃ ታሪክ አሻራቸውን ካሳረፉ የሙዚቃ ደራሲዎች መሀል አንዱ ነው። ታዲያ በወጣትነት ዘመኑ አንዲት ፍቅረኛው ምንነቱን ባላወቀው ምክንያት በድንገት ትለየውና ከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ሲገባ Gloomy Sunday ወይም የጨለመ እሁድ የተሰኘ ዘፈንን ይደርሳል። ይህንን የዘፈን ድርሰት ጃቮር ለተባለ ለገጣሚ ጓደኛው ሲያሳየው በጣም ይወደውና ሀሳቡን ትንሽ ቀየር አድርጎ ሙዚቃውን ይሰራዋል

ይህ ሙዚቃ አንድ ፍቅረኛውን በሞት ያጣ ወጣት ህይወት ትርጉም አልባ ሆናበት በሰንበት ቀን የሞት መላክ መጥቶ ወደሷ እንዲወስደውና ዳግም ከሷ ጋር ለመገናኘት ሲያስብ የሚያስቃኝ ሙዚቃ ነበር
በሙዚቃው ግጥም ውስጥ
የሞት መላዕክ እያሽኮረመመው እንደሆነ ፣ ፈጣሪን ወደሷ ውሰደኝ ብሎ ቢጠይቀውም እምቢ እንዳለውና በራሱ መንገድ ሊመጣ እንደሆነ የሚያወሱ ስንኞች ተካተውበት ነበር

ታዲያ ይህ ሙዚቃ ዝናው ከፍ እያለ ሲመጣ በርካቶች ያደመጡ ሲሆን ሙዚቃው ላይ ያለው አጠቃላይ የጭለማ ስሜት እየገፋፋቸው ብዙዎች ራሳቸውን ማጥፋት ጀመሩ
ዘፈኑ ዝናው ወደ አውሮፓ ሀገራት ተሻግሮ በተለያዩ ቋንቋዎች ከተሰራ በኋላም ብዙዎች ራሳቸውን ያጠፉ ሲሆን ቢቢሲ በሚዲያው ላይ ይህ ሙዚቃ እንዳይተላለፍ አግዶትም ነበር

የሙዚቃው ደራሲ ሴሬስ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ ወደሙዚቃው አለም ለመመለስ ቢሞክርን ይህን የሙት መንፈስ የሚጠራ ዘፈን የሚፎካከር ዘፈን መስራት አልቻለም።
አሳዛኙ አጋጣሚ ደግሞ ሴሬስ ይህን ዘፈን እንዲፅፍ ምክንያት የሆነችው ፍቅረኛውን ዳግም ለማግኘት ቢሞክርም ሁሉም ነገር ረፍዶ ነበር። ፍቅረኛው ራሷን አጥፍታ የተገኘች ሲሆን አጠገቧ ያስቀመጠቸው ወረቀት ላይ የተፃፈው ፅሁፍ ደግሞ Gloomy Sunday የሚል ነበር

Address

Bole Behind Dembel Gazebo Building 5th Floor
Bole

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Revo Music posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to Revo Music:

Share