Palm Tube - ፓልም ትዩብ

Palm Tube - ፓልም ትዩብ ሚዛናዊ ሀሳብ...

 ...‼️ለፍርድ እንዲቀርብ ያጨነው፣ ለድርድር ቀርቦ ሲያወራን፤ስለ አንድነት ስንሰበክ፣ ልዩነትን እያወሳን፤ጡት አጥብተው ያሳደጉን፣ያልወለዱን እናቶችን፣ ፍቅራቸውን እየረሳን፤እንደ ጆሮ ቆራጭ...
24/10/2025

...‼️
ለፍርድ እንዲቀርብ ያጨነው፣ ለድርድር ቀርቦ ሲያወራን፤
ስለ አንድነት ስንሰበክ፣ ልዩነትን እያወሳን፤
ጡት አጥብተው ያሳደጉን፣
ያልወለዱን እናቶችን፣ ፍቅራቸውን እየረሳን፤
እንደ ጆሮ ቆራጭ ታሪክ፣
ጡት ቆራጩ የሚል ተረት፣ በልጆች ፊት እያነሳን፤
ጥላቻና ቂም ወለድን!
እርቅ ፈርተን፣ ፀብ ወደድን!
መረዳዳት ፈራን፣ እየተራረድን!
ፍቅር ፈራን!
እርቅ ጠላን እንዳንድን!
#ፈራን እምነት ፈራን...!
የለውጡ ሀይል ሲመጣ፣ በቃሉ ያሳመነንን፤
አንዱ አሳዳጅ አንዱ ተሳዳጅ፣ ከእንግዲህ አይሆንም ያለንን!
ዛሬ ላይ ሆነን ስናየው፣ ተረኛ ነኝ ባይ ሲያሳደን፤
አንደኛው በዚህ ሲያግተን፣ አንዱ ደግሞ በዚያ ሲያርደን፤
በሞትና በሞት መሃል፣ አንድ ህይወታችንን ጥደን፤
አንድ አምላክን እየጠራን!
እምነት ፈራን!
ወደ ህይወት ስንጠራ፣ ወደ እልቂት እያመራን!
መደመርን ፈራን!
አንድነትን ፈራን!
አብሮ መጓዝ ፈራን!
እውነት ፈራን!
ሰው መሆን ፈራን!
ዘር ማንዘሮች እየዘራን!
፣ ጥላቻችን እየመራን፤
ፈውስ ፈራን....
የመዳን ቃል የሚነግረን፣ ስለ ሟቾች እያወራን!!!

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Palm Tube - ፓልም ትዩብ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category