Amhara Cultural & Art Center የአማራ ባህልና ኪነ-ጥበብ ማእከል

Amhara Cultural & Art Center የአማራ ባህልና ኪነ-ጥበብ ማእከል የአማራ ባህልና ኪነ-ጥበብ ማዕከል | MULUALEM AMHARA CULTURE & Art CENTER | Bahir dar Ethiopia

28/03/2026
✨ የጥብ_ጥማትዎን_በባሕር ዳር ይቁረጡ! ✨የባህሕር ዳርና አካባቢዋ ነዋሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ! የጥበብ ረሃብዎን የሚያረካ፣ በአዝማሪዎች ተሰጥኦና ለዛ በሳቅ የሚያጠግብ ድንቅ ትዕይንት ወ...
23/03/2026

✨ የጥብ_ጥማትዎን_በባሕር ዳር ይቁረጡ! ✨

የባህሕር ዳርና አካባቢዋ ነዋሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ! የጥበብ ረሃብዎን የሚያረካ፣ በአዝማሪዎች ተሰጥኦና ለዛ በሳቅ የሚያጠግብ ድንቅ ትዕይንት ወደ እናንተ መጥቷል።

✨ ✨ #የአዝማሪዎችን ጥበብ ከዘመናዊ #የቴአትር ጥበብ ጋር አዋህዶ የያዘ፣ ወዳጅ ዘመድ ሰብሰብ ብሎ ሊያየው የሚገባ ልዩ የጥበብ ድግስ ነው።

ቀን፦ መጋቢት / 2018 ዓ.ም
ቦታ፦ በሙሉዓለም አዳራሽ (ባህር ዳር)
ሰዓት፦ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ

የባህልና የሳቅ ጥምረት እንዳያመልጥዎ! ቀድመው ቦታዎን ይያዙ።

#ባህርዳር #ኢትዮጵያዊ #ቴአትር #እንዛታ

የአብክመ ባህልኪነ-ጥበብ እና ዝክረ ታሪክ ጽ/ቤት

ቤተሰብ ይሁኑ!
ዲጅታል ሚዲያ ገፆቻችንን ይቀላቀሉ።
👇👇👇
YouTube: https://www.youtube.com//videos
Telegram: https://t.me/mulualemculturalcenter
Face Book: https://www.facebook.com/mulualem.culture.5?mibextid=ZbWKwL
Instagram: https://www.instagram.com/mulualemculturalcenter/
Tiktok : tiktok.com/

19/01/2026
🔥ጎንደር ሙሽሪት - የቢኒ ጎይቶም ሞቅ ያለ ባህላዊ ሙዚቃ ተለቀቀ 👇
15/01/2026

🔥ጎንደር ሙሽሪት - የቢኒ ጎይቶም ሞቅ ያለ ባህላዊ ሙዚቃ ተለቀቀ 👇

Gonder Mushrit - Bini Goytom | ጎንደር ሙሽሪት - New Ethiopian Music 2026 (Official Video)Subscribe to Bini Goytom | And Turn ON Notifications To Stay Updated Wit...

21/12/2025

ሙሉአለም የአማራ ባህልና ኪነ-ጥበብ ማዕከል 2023ቱ የአለም አቀፍ የባህል ፊስቲቫል

Mulualem Amhara cultural & art center international folklore festival 2023

በአለምአቀፍ በተለያዩ ሀገራት የባህል ፌስቲቫል የሀገራችንን ባህልና እሴት  በማስተዋወቅ የኢትዮጵያን የባህል ዲፕሎማሲ ስራዎችን ስለሰራዉ የሙሉዓለም ባህል ማዕከል ምን ያህል ያዉቃሉ !?   ...
20/12/2025

በአለምአቀፍ በተለያዩ ሀገራት የባህል ፌስቲቫል የሀገራችንን ባህልና እሴት በማስተዋወቅ የኢትዮጵያን የባህል ዲፕሎማሲ ስራዎችን ስለሰራዉ የሙሉዓለም ባህል ማዕከል ምን ያህል ያዉቃሉ !?

| በህንድ፣ ሩሲያ፣ ቻይና ፣ ቱርክ የመሳሰሉት ሀገራት ሀገር በተካሄዱ ዓለምአቀፍ የባህል ፌስቲቫል ላይ ፤ ኢትዮጵያን ወክሎ በመሳተፍ የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪቃን ባህላችንን ማስተዋወቅ ፣ እሴታችንን በመግለጥ በቀጣይ ለቱሪዝም እንቅስቃሴ ቱሪስቶች እንዲጎበኙን የሚያስችሉ ብዙ ዕድሎች ለመፍጠር የሚቻልበትን ተግባር አከናውኗል ።

ከተለያዩ ሀገራት ከሁሉም አህጉራት ሀገራት ተሳታፊ በሆኑበት ፌስቲቫል ሲሆን የኢትዮጵያን ፀጋዎች ታሪካችንን ፣ጥበባችን፣ ቅርሶቻችንና የተፈጥሮ ሃብታችን አስተዋዉቋል።

በአለም አቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ ፌስቲቫሎች የአገራችንን ባህልና ኪነጥበብ ማስተዋወቅና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማድረግ ለቱሪዝም እንቅስቃሴ የሚጫወተዉ ሚና በቀላል የሚገለጽ አይደለም።

በቅርቡ ከህንድ የተመለሰዉ ይህ ተቋም በቅርቡ በባህል ዲፕሎማሲ ስራዎች እና በሀገር ዉስጥ ገጽታ ግንባታ ስራዎች የተለያዩ ሽልማቶችን ተቀዳጅቷል።

በህንድ የሚካሄደው ዓለምአቀፍ የባህል ፌስቲቫል ላይ የሚሳተፈው፤  የኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ልዑክ ነገ በረራውን ያደርጋል የዘንድሮ ዓለማቀፍ የባህል ፌስቲቫል ከህዳር 14 እስከ 22 ቀን 201...
22/11/2025

በህንድ የሚካሄደው ዓለምአቀፍ የባህል ፌስቲቫል ላይ የሚሳተፈው፤ የኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ልዑክ ነገ በረራውን ያደርጋል

የዘንድሮ ዓለማቀፍ የባህል ፌስቲቫል ከህዳር 14 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ/ም በህንድ በድምቀት ይካሄዳል።

እዚህ ደማቅ ዓለምአቀፍ የባህል ፌስቲቫል ላይ ደግሞ ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው የአማራ ባህልና ኪነጥበባት ልዑክ ሲሆን ነገ ወደ ህንድ በረራውን ያደርጋል ።

አቶ ገብረማርያም ይርጋ የአማራ ባህልና ኪነጥበባት ቡድን መሪ ፤ በሚካሄደው ደማቅ ዓለማቀፍ ፌስቲቫል ላይ የኢትዮጵያን ባህልና ኪነጥበብና እሴቶች የማስተዋወቅ ስራ ይሰራል ብለዋል።

በመድረኩ አገራችንን በባህልና ኪነጥበብ ከማስተዋወቅና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ከማድረግ ባሻገር፣ በባህል ዲፕሎማሲ ትዕይንቶች የኢትዮጵያን ልዕልና ሀገራዊ መቻልን ማሳየት፣ ከተለያዩ የአለም ሃገራት ከሚመጡ የባህልና ኪነ ጥበብ ልዑካን ቡድን ጋር የልምድ ልውውጥ እንደሚደረግ እንዲሁም ከተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት እና አገሮች ጋር ግንኙነት በማድረግ በኪነጥበቡ ዘርፍ እንደ ሃገር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው አቶ ገብረማርያም አብራርተዋል።

የአማራ ባህልና ኪነጥበባት ልዑክ በባህል ዲፕሎማሲ ስራዎች ለሀገር ክብር በትልቅ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ባሳለፍነው ዓመት በህንድ ፣ በሩሲያ፣ በቱርክ፣ በቻይና ሀገራት በተካሄዱ ዓለምአቀፍ ፌስቲቫሎች ኢትዮጵያን ብሎም አፍሪቃን ወክሎ በመሳተፍ እና የተለያዩ ሽልማቶችን መቀዳጀቱን ቡድን መሪው አስታውሰዋል።

በዚህ ጉዞ ፤ የቀድሞዉ ሙሉዓለም ባህል ማዕከል እና ከጎንደር ፋሲለደስ ኪነት ቡድን የተዉጣጡ 25 አባላትን ያቀፈ ቡድን እንደሚጏዝ የተገለፀ ሲሆን ለዚህ ጉዞ መሳካት የኢትዮጵያ አየርመንገድ 25% ቅናሽ ማድረጉን አቶ ገብረማርያም ይርጋ አሳዉቀዋል ።

እንኳን ለ ብርሃነ መስቀሉ  አደረሳችሁ !የኛ ዉሎ ደግሞ በቻይና ጓንዡ  የኤክስፖ ተሳትፎ በማድረግ ነበር ። እንዴት የሚደንቅ ዉሎ ነበር መሰላችኹ!።  ትናንት የሽለላና ፉከራን እሴት ክዋኔ ...
29/09/2025

እንኳን ለ ብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ !

የኛ ዉሎ ደግሞ በቻይና ጓንዡ የኤክስፖ ተሳትፎ በማድረግ ነበር ።
እንዴት የሚደንቅ ዉሎ ነበር መሰላችኹ!። ትናንት የሽለላና ፉከራን እሴት ክዋኔ ምን እንደሚመስል በዓለም መድረክ ለተሳታፊዎች ገለጻ አቅርበን ነበር። ይህ ክዋኔ ከ5_9 ተሳታፊዎችን በመያዝ በቀጣይ ወራት በፈረንጆች አዲስአመት በኃላ የቻይና የተለያዩ መድረኮች የሚጓዙ ይሆናል። ተሳታፊ ሀገራት የቀጣይ ስራዎቻቸዉን የማስተዋወቅ ስራ ሰርተዋል። በዛሬዉ ዉሏችን ስለ ኢትዮጵያችን ባህልና ጥበባት በኤክስፖ ተገንተን አስተዋዉቀናል። የተለያዩ አገራት ተሳታፊዎች እና ጎብኝዎች ከባህል ቡድናችን እና ድራማዊ ክዋኔ ለዛ ጋር በቀጣይ ለመታደም እንደጓጉ ገልጸዉልናል።

ይህ ጥበባዊ ፋይዳ ያለው ዘርፍ በወጉ ሳይዘገብና ሳይሰራበት የቆዬ ቢሆንም ይህን ድንቅ እሴት በማቅረብ ሀገራችንን ያስተዋወቅን ሲሆን ወደፊትም በልዩ ልዩ መልኩ ክዋኔው ግዙፍ የሰው ልጅ ጉዳይ የሆኑ አጀንዳዎች የሚተረኩበት እንዲሆን የምንሰራ ይሆናል።

ዛሬ የምንሰራው የነገ ታሪካችን ነዉ!

የሙሉዓለም ባህል ማዕከል  ቻይና እየተካሄደ በሚገኘዉ ዓለምአቀፍ ፌስቲቫል  ኤክዞቲክ ክዋኔ አቀረበ ።ጥቁር ሕዝቦች ከፋሽት ጋር ያደረጓቸው ጦርነቶች ብዛት የትየሌለ ነው።ከነዚህ ውስጥ የጥቁር...
28/09/2025

የሙሉዓለም ባህል ማዕከል ቻይና እየተካሄደ በሚገኘዉ ዓለምአቀፍ ፌስቲቫል ኤክዞቲክ ክዋኔ አቀረበ ።

ጥቁር ሕዝቦች ከፋሽት ጋር ያደረጓቸው ጦርነቶች ብዛት የትየሌለ ነው።
ከነዚህ ውስጥ የጥቁር ህዝቦች ሁሉ ነፃነት አሻራ የሆነው የ #አድዋ ድል ዋነኛው ነው።

"ኢትዮጵያዊያን የአድዋን ድል ለምን ተጎናፀፉ?" የሚለው አመክንዮ ሲፈታ በጦርነቶች ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያለ ልዩነት በህብረት መቆም ይጠቀሳል ።

#ኢትዮጵያዊያን በልዩ ልዩ መልኩ እንደዬ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ባህል ልዩ ልዩ ገፅታ ቢኖረውም በሁሉም አካባቢ ወኔን የሚቀሰቅሱና ጭቆና፣ ማህበራዊ ለውጥን፣ ልዩ ልዩ የደስታ ክብረ በዓላትን የሚያደምቁ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ብዝበዛዎች እልባት እንዲያገኙ የሚያነቃቁ እንደ ''ፉከራ፣ #ሽለላና #ቀረርቶ'' ያሉ ጥበባዊ ክዋኔዎች ትልቅ እሴቶቻችን ሆነው ኖረዋል።

ትናንት ኢትዮጵያዊያንን ካለአንዳች ልዩነት አሰባስበው ጠላትን ድል ለመንሳት እንደተጠቀምንባቸዉ ሁሉ፤ በዛሬነት ጊዜያት ለሀገር ክብር በህብር መትመም፣ ሁለንተናዊ ሠላም ለማግኘት እንዲቻል ወኔ ቀስቅሰንባቸው ልንጠቀምባቸዉ እንደሚገባ በመግለጥ ስለ ሽለላና ፉከራ እንዲኹም ቀረርቶ በዓለም መድረክ አስተዋዉቀናል።

ይህ ጥበባዊ ፋይዳ ያለው ዘርፍ በወጉ ሳይዘገብና ሳይሰራበት የቆዬ ቢሆንም ይህን ድንቅ እሴት በማቅረብ ሀገራችንን ያስተዋወቅን ሲሆን ወደፊትም በልዩ ልዩ መልኩ ክዋኔው ግዙፍ የሰው ልጅ ጉዳይ የሆኑ አጀንዳዎች የሚተረኩበት እንዲሆን የምንሰራ ይሆናል።

በመሆኑም አፍሪካዊያንን የዚህ አይነት ኤክሶቲክ / Exotic / ክዋኔ የወል እሴቶቻችን፣ የትናንት የዛሬ እና ነገ በባህላዊ በሙዚቃና ልዩ ልዩ ትዕይንታዊ ክዋኔዎች አስተዋውቀንበታል።

እንደ የባህል ተሳታፊ ልዑክ እና የባህል ልውውጥ መድረክ ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችንን አስተዋዉቀናል። በተጨማሪ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለነበረዉ አስተዋጽዖ ምስጋና አቅርበናል ። በመርሃግብሩ "በክብር የሚበሩበት ተቋም" በሚል ስለ አየር መንገዱ ስለአገልግሎቱ አስተዋዉቀናል ።

ዛሬ የምንሰራው የነገ ታሪካችን ነዉ!

በቻይና  ጓንዡ ከተማ  በሚካሄደው  ዓለምአቀፍ የቲያትር ፌስቲቫል እና የጥበባት ኤክስፖ ላይ  ለመሳተፍ ወደ ቻይና  ያቀናዉ ልዑክ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት። በዚኹ ፌስቲቫል የኢትዮጵያን ባ...
26/09/2025

በቻይና ጓንዡ ከተማ በሚካሄደው ዓለምአቀፍ የቲያትር ፌስቲቫል እና የጥበባት ኤክስፖ ላይ ለመሳተፍ ወደ ቻይና ያቀናዉ ልዑክ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት።

በዚኹ ፌስቲቫል የኢትዮጵያን ባህልና ኪነጥበብና እሴቶች የማስተዋወቅ ስራ እና ኤክስፖ ተሳትፎ ለማድረግ ነዉ ወደ ስፍራዉ ያቀናዉ።

በቻይና ዓለማቀፍ መድረክ በቲያትር ፌስቲቫል እና ጥበባት ኤክስፖ ሲደርስ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን ከአምስት አህጉራትና ከ12 የተለያዩ ሀገራት ከመጡ ልዑኮች ጋር ትዉዉቅ መርሃግብር እና የክብር ግብዣ ተደርጎለታል።
በቀጣይ ቀናት አገራችንን ባህልና ኪነጥበብ ከማስተዋወቅና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ከማድረግ ባሻገር፣ በባህል ዲፕሎማሲ ተግባራት የኢትዮጵያን ልዕልና ሀገራዊ መቻልን ማሳየት፣
ከተለያዩ የአለም ሃገራት ከሚመጡ የባህልና ኪነ ጥበብ ልዑካን ቡድን ጋር የልምድ ልውውጥ ማድረግ በኪነጥበቡ ዘርፍ እንደ ሃገር ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር ጥረት እንደሚያደርጉ የአብክመ ባህል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረማርያም ገልፀዋል ። ለጉዞዉ መሳካት አስተዋጽኦ ለነበረዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በድጋሚ አመሥግነዋል ።

ዛሬ የምንሰራው የነገ ታሪካችን ነዉ!


Address

Bahar Dar Ghiorghis

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Cultural & Art Center የአማራ ባህልና ኪነ-ጥበብ ማእከል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category