Kedamay dance art's group

Kedamay dance art's group Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kedamay dance art's group, Arts and entertainment, Ethiopian arbaminch town, Arba Minch'.

26/05/2026
10/04/2026

የጋሞ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ማዜ ሸቀኔ ለስቅለትና ትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ።

አርባ ምንጭ ሚያዝያ 02/2018 ዓ/ም (የጋሞ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ )

በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ወረሀ አብይ ጾም ምእመኑ በጾምና ጸሎት ተወስኖ የቆየበትና ይበልጥ ወደ አምላኩ የሚያቀርቡ በጎ ተግባራት በመከወን ያሳለፈበት መሆኑን ገልጸው ይህ ተግባር የሁልጊዜ ልምምድ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

በዓሉን ስናከብር እንደ እምነቱ አስተምሮ አቅም የሌላቸውንና ጧሪ አልባ የሆኑ ወገኖቻችንን በመርዳት ና በመደጋገፍ ባህል መሆን እንዳለበት አስታውቀዋል።

በመጨረሻም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮችና ለመላው የዞናችን ነዋሪዎች እንኳን ለስቅለትና ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ያሉ ሲሆን በዓሉ የሠለም የጤና የፍቅር እንዲሆን ተመኝተዋል።

02/03/2026

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምሴ አድማሱ ለ130ኛው የዐድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

​የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን በልዩነት ውስጥ ሆነው ለአንድ የጋራ ዓላማ ለሀገር ሉዓላዊነትና ክብር በአንድነት የቆሙበት የታሪክ አሻራ ነው።

ይህ ድል ዛሬ ላይ ለምንሠራው የልማት ሥራ ትልቅ ስንቅና ትምህርት የሚሰጠን ነው። የዓድዋ ጀግኖች በጦር ሜዳ የነበራቸውን ጽኑ ዐቅምና አሸናፊነት እኛ ዛሬ በልማት ሜዳ ልንደግመው ይገባል።

​በጋሞ ዞናችን የሚታየውን ሰፊ የልማት እንቅስቃሴ ከዓድዋ ድል መንፈስ ጋር በማስተሳሰር በዓድዋ ወቅት የታየው የማይበገረው የኢትዮጵያውያን ዐቅም፣ ዛሬ በዞናችን የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ፣ በቱሪዝም መስህቦቻችንን በማልማትና በኢንዱስትሪ ክፍለ ኢኮኖሚ ውስጥ በተግባር ሊገለጥ ይገባል።

​ የዓድዋ ጀግኖች ልዩነታቸውን ትተው ለሀገር እንደቆሙት ሁሉ፣ እኛም በዞናችን ያለውን የሰላምና የአንድነት እሴት ተጠቅመን የጀመርናቸውን ታላላቅ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ዳር ማድረስ ይኖርብናል።

ዐርበኝነት ማለት ከግል ጥቅም ይልቅ የሀገርንና የሕዝብን ክብር ማስቀደም፣ ለጋራ ብልጽግናም መሰለፍ ነው። በመሆኑም በዞናችን የተጀመረው የልማት ጉዞ ዳር እንዲደርስ፣ ለሰላማችን መታወክና ለዕድገታችን እንቅፋት የሚሆኑ ጉዳዮችን በጋራ በመምከር ልንታገላቸው ይገባል።

ጋሞ ዞንን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ያለንን የተፈጥሮ ጸጋና የሰው ኃይል ዐቅም አቀናጅተን በመጠቀም፣ የዓድዋን ድል በኢኮኖሚ ድል ልንደግመው ይገባል።

​በመጨረሻም የአመራሩና የብርቱ የሕዝባችን ተሳትፎ ተደምሮ ዞናችንን ወደላቀ ከፍታ እንደሚያሸጋግራት ሙሉ እምነቴ ነው።

ዶ/ር ደምሴ አድማሱ
የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

ጋሞ ዞን መ/ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የካቲት 22/2018 ዓ.ም

25/02/2026

‎የ2018 ዓ.ም የጋሞ ዞን እግር ኳስ ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር በሁለቱም ፆታ ሚያዚያ ወር አጋማሽ ላይ የሚካሄድ በመሆኑ ከወዲሁ ቅድመ-ዝግጅት እንድታደርጉ ስለማሳወቅ ይሆናል።

Address

Ethiopian Arbaminch Town
Arba Minch'
DUNGUZA

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kedamay dance art's group posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share